Get Mystery Box with random crypto!

ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን? ~ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:– 'የሰው ልጅ ሲሞት ስራ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን?
~
ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:–

"የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር።
① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣
② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣
③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም]

የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ?
① ከቻልን አጅሩ የማይቋረጥ ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ።
② ወይ ደግሞ እውቀትን በማሰራጨት ላይ ድርሻ ይኑረን። (ይህም በሁለት መልኩ ሊሆን ይችላል። ተምሮ በማስተማር። ያወቁትን በማካፈል። ወይም የዑለማዎችን እውቀት በማሰራጨት።)
③ ወይ ደግሞ ልጆቻችንን በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ።
ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው። ከነገ በፊት ዛሬ እንመልከት። ከነዚህ መስኮች ውስጥ የቱ ላይ አለን?
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor