Get Mystery Box with random crypto!

ሶላት የተወ ሰው የሚኖረውን ብይን (ሑክም) በተመለከተ ከጥንት ጀምሮ በዑለማእ መካከል የሃሳብ ልዩ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ሶላት የተወ ሰው የሚኖረውን ብይን (ሑክም) በተመለከተ ከጥንት ጀምሮ በዑለማእ መካከል የሃሳብ ልዩነት አለ።
1፦ ከፊሎቹ ከኢስላም ይወጣል ሲሉ
2፦ ሌሎቹ ደግሞ ወንጀለኛ ቢሆንም ከኢስላም አይወጣም ብለዋል።
በሁለቱም አቋሞች በኩል ታላላቅ ዑለማኦች አሉ። አቅሙ ያለው ሰው መረጃዎቹን ፈትሾና አበጥሮ ከሁለቱ አቋሞች ውስጥ ሚዛን የሚደፋውን መውሰድ ይጠበቅበታል። ከዚህ አልፎ ጉዳዩን በሌላኛው በኩል ያሉትን ዓሊሞች በቢድዐ ለመወንጀል ማዋል ግን ተገቢ አይደለም። ይሁን እንጂ አንዳንዶች "ሶላት የተወ ሰው ከኢስላም አይወጣም" የሚሉ ዓሊሞችን በኢርጃእ ሲወነጅሉ ይታያሉ። ይሄ የተሳሳተ አካሄድ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor