Get Mystery Box with random crypto!

ሟቹ 'ጌታ!' ~ ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ሟቹ "ጌታ!"
~
ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል።
·
* ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት።
·
ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ።
·
ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው።

* "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ።
·
አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል።
·
* "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው።
– "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት።

* "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ።
– "አዎ" አሉት።
·
ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:–
"እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!"

የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።

መወለድ፣ ማደግ፣ መሞት ለፈጣሪ የማይመጥኑ የደካማ ፍጡሮች መታወቂያ ናቸው። እባካችሁ ያገሬ ሰዎች ቆም ብላችሁ አስቡ። "ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ" እያሉ "ተጨፈኑ እናሙኛችሁ" ሲሉ እጅ አትስጡ። "ሁሉን ምርምሩ። መልካሙን ያዙ።" በአባቶች የውርስ ጋቢ ተጠቅልላችሁ፣ በይሉኝታ ጆሯችሁን ደፍናችሁ፣ በምስጢረ ሥላሴ ትብታብ ታስራችሁ እንጂ ህሊናችሁን ፋታ ሰጥታችሁ በእርጋታ ብታዳምጡት የሚነግራችሁ ሐቅ አለ።
"ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ ይነግርሀል አንዳች እውነት" ይላል ገጣሚው።
·
ዳሰሳ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 12 ቁ 29 እስከ 34።
----------
"ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። #ከትእዛዛቱ_ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #ጌታ_አምላካችን #አንድ_ጌታ ነው፥" (የማርቆስ ወንጌል 12:29)
·
ማነው ይህን ያለው? እየሱስ እራሱ!! "ጌታ አምላካችን" ማለቱን አስምርበት። እየሱስ ፍጡር እንጂ ጌታ እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጥቅስ ነው። ይሄ ቀዳሚ ትእዛዝ ግን በክርስቲያኖች ተገፍቷል። እንቀጥል።

"አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።" (የማርቆስ ወንጌል 12:30)
·
ልብ በል! በዚህ መልኩ "ጌታህን ውደድ" እያለ የሚያስተምረው እየሱስ እራሱ ነው። ይህም እሱ አስተማሪ እንጂ ጌታ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። እንቀጥል።

"ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።

ጻፊውም። መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ #አንድ_ነው። #ከእርሱም_በቀር_ሌላ_የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤" (ማርቆስ 12:31–32)

እያስተዋልክ ነው?!
እውነት የምትፈልግ ከሆንክ "አምላክ አንድ ነው። ከርሱ በቀር ምንም የለም" ብለህ በልብህ ዝከር። በምላስህ አስተጋባ። በተግባር ኑር። ይሄ በኢስላም "ላ ኢላሀ ኢለላህ" ("ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም") ከሚለው ምስክርነት ጋር መሳ ነው። እንቀጥል።

"በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።" (ማርቆስ 12:33)

ይህን ነው የምልህ። ስላሴ፣ ቅብጥርሴ የሚባለውን ወደ ኋላህ አሽቀንጥረህ ጣልና ለመፅሐፋዊ መልእክቱ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ እደር። ሥላሴ ልብ ወለድ እንጂ እውነታ አይደለም። ሥላሴ ጤነኛ ጭንቅላት የማይፈታው እንቆቅልሽ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም። "ያልገባህ መንፈስ ቅዱስ ስላላደረብህ ነው" እያሉ አይሸውዱህ። ይሄ ምእመኑ እንዳይመረምር የሚያስተኙበት የእንቅልፍ ክኒን ነው። በክኒኑ እራሳቸውን ያስተኙበት። አንተ ግን ንቃ። ይህን ስታደርግ፣ ወደ አእምሮህ ስትመለስ "ለመንግስተ ሰማያት" ትቀርባለህ። አብረን እናንብብ።

"ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።" (ማርቆስ 12:34)

(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 11/2011)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor