Get Mystery Box with random crypto!

ለእየሱስ ባሪያዎች! ~ የመሲህ ባሮች ሆይ - አንድ ጥያቄ አለን የተረዳው ካለ - መልሱን እንሻለን | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ለእየሱስ ባሪያዎች!
~
የመሲህ ባሮች ሆይ - አንድ ጥያቄ አለን
የተረዳው ካለ - መልሱን እንሻለን
ጌታ ግፍ አቅቶት - ሰዎች ከገደሉት
አለቀ አከተመ - የታል አምላክነት?!
ሰዎች የሰሩትን - በሱ ላይ ሲያደርሱ
ጌታ ግብራቸውን - ፈቅዶ ነው በራሱ?
እንዲያ ከሆነማ - ምንኛ ታደሉ?!
ፍቅሩን ይቸራሉ - ፈቃዱን ሲሞሉ።
ባደረሱት ሁሉ - አልፎ ከተከፋ
እንግዲህ ምን ይባል?
ሀይሉ ከኮሰሰ - ሀይላቸው ከሰፋ?!
ግን እንጠይቃለን - ለመልስ አትንፈጉ
ማለባበስ ይቅር - ይመለስ በወጉ
ፈጣሪዋን አጥታ - ዐለም ስትዋትት
ሰው ወደ ማን ነበር - የሚያስበው ፀሎት?
ፍጡር ፈጣሪውን - ካፈር ሲያደባየው
ሰባቱን ሰማያት - ማነበር ያቆየው?
ምስማር ተቸንክሮ - ሲያሸልብ ፈጣሪ
ዓለም ቀርታ ነበር - ያለ አስተናባሪ?
የሰማይ መላእክት - ምንኛ ለገሙ?!
እጁ ተቸንክሮ - ዋይታውን ሲሰሙ?
እንጨቱም ታምር ነው - አቅሙ መቋቋሙ
አምላክ ያክል ነገር - ችሎ መሸከሙ
ስለቱስ ጭቃኔው - ብረቱ ምስማሩ
አካሉን ሰንጥቆ - ስቃይ ማሳደሩ
ጉድ በሉ እሄን ጌታ - በአይሁድ የሚረታ
ማጅራቱን ታንቆ - ታስሮ የሚመታ
ኋላስ ራሱ ነቃ - ከሞት አንሰራራ
ወይስ ጌታ አገኘ - ህይወት የሚዘራ?!
ጉድ በሉ ለቀብር - ጌታ አቅፎ ለያዘ
የባሰም ሆድ አለ - አምላክ ያረገዘ
ዘጠኝ ወር ታሽጎ - ሲኖር በጨለማ
ሐይድ እየተጋተ - ደም እየተጠማ
ብልት ቀዶ ወጣ - አቡሻ ህፃኑ
አፉን ለጡት ከፍቶ - አቤት ማሳዘኑ!
አስቡ እሄን አምላክ - ሲጠጣ ሲበላ
ከዚያም ያስገባውን - ሲያስወጣ በሌላ
ጌታዬ ከፍ አለ - ከነሳራ ቅጥፈት
ሁሉም ይጠየቃል - ለቀባጠረበት
የመስቀል ባሮች ሆይ! - ግራ ገባኝ እኔ
ያሽቀነጠረው ሰው - ፅድቅ ነው ኩነኔ
ማቃጠል ሰባብሮ - ፈቃጁን ጨምሮ
ህሊና ከዚህ ውጭ - ይፈርዳል አምርሮ?
አምላክ አቅም አንሶት - ለተጠፈረበት
ሰብሮ እንደማቃጠል - ጭራሹን አምሎኮት?!
እውነትም እርጉም ነው - ለምንስ ይዘንጋ?
በመሳለም ሳይሆን - በእግር ይሰጥ ዋጋ!
ለተዋረደበት - ጌታህ ከነነፍሱ
አንተ ካመለክከው - የሱ ነህ የነሱ?
‘ጌታን ስላዘለ’ - ከሆነ አክብሮቱ
አስተዋሽ ቅርፃቅርፅ - ቢሆን እንጂ እንጨቱ
መስቀሉ ከጠፋ - ሺ ስንት አመታቱ?!
እንዲያ ከሆነማ - ሂሳቡ ቀመሩ
ለመስገድ አትቦዝን - ለየመቃብሩ
ያስታውሳልና - ነገረ ስርኣቱ
"ጌታህ" ካፈር በታች - ለነበረበቱ።
የመሲህ ባሪያ ሆይ! - ንቃ ተረጋጋ
ይሄ ነው እውነታው - ካ'ልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡

የኢብኑል ቀዪም አልጀውዚያህ “አዑባደል መሲሒ ለና ሱኣሉን” ድንቅ ግጥም ግርድፍ ትርጉም፡፡ ግጥሙን “ኢጋሠቱል ለህፋን ኪታክ ገፅ: 2/290 ላይ ያገኙታል፡፡ የግጥሙን አሪፍ የቪዲዮ ቅንብር ደግሞ ከፍቺው ጋር ከስር ይመልከቱ፡፡

ኢብኑ ሙነወር
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M