Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ጥንቃቄ፣ ስለ መረጋጋት፣ ስለ ማረጋገጥ፣ ... ስናወራ የቢድዐ አንጃዎችን እንለፍ፣ እንተላለፍ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ስለ ጥንቃቄ፣ ስለ መረጋጋት፣ ስለ ማረጋገጥ፣ ... ስናወራ የቢድዐ አንጃዎችን እንለፍ፣ እንተላለፍ እያልን አድርገው የሚያስቡ ወገኖች አሉ። እንደዚያ እየመሰላቸው በአንድ በኩል "ተደመራችሁ" የሚሉ አሉ። በሌላ ማዶም "በሰላችሁ" የሚሉ አሉ። ቢድዐን አቃፊ የሆነን "መብሰል።" በዚህ መልኩ የሚመጡት ሁለቱም ልክ አይደሉም።
እርግጥ ነው ሰው ከእድሜም፣ ከልምድም፣ ከእውቀትም የሆነች ያክል በጨመረ ቁጥር መብሰል ሊኖረው ይገባል። መብሰል እንዲኖረውም መጣር አለበት። አካሄዱ ላይ መታረም ያለበት ነገር እንዳለ ካስተዋለም "ካፈርኩ አይመልሰኝ" ማለት ለማንም አይጠቅምም።
የሆነ ሆኖ በመብሰል ስም በሺርክና ቢድዐ ላይ መለሳለስ አይገባም። ቢድዐ ላይ በመጠንከር እና ለሱና በመቆርቆር ስም እንደ ተናካሽ ውሻ ያለፈ ያገደመው ላይ ሁሉ ልንጮህም አይገባም። አካሄዳችንን እንፈትሽ። መታረም ያለበት ካለ የሰዎች ሃሳብ ሳያስጨንቀን እናስተካክል። የትኩረታችን ማዕከል ህዝብ ይሁን። ሰፊውን ወገናችንን መጥቀም። ከሺርክና ከቢድዐ እንዲወጣ ሳያሰልሱ መስራት። ዲኑን እንዲገነዘብ መረባረብ። አዎ ለተሻለ ውጤት የተናጠል ጥረት ሳይሆን የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል። ርብርቡ ካላዋጣ ወይም ከዚያ ይልቅ የጎንዮሽ መጓተትን የሚያስቀድም ከበዛ ስለማንም ሳይጨነቁ የራስን ድርሻ ለመወጣት መጣር ነው። አላህ ማስተዋሉን ያድለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor