Get Mystery Box with random crypto!

አኺል ከሪም! ~ ሰለፎች ቢድዐ እና ሙብተዲዕ ላይ ብርቱዎች ነበሩ። ይህ ማለት ባልተረጋገጠ ወሬ ሰ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

አኺል ከሪም!
~
ሰለፎች ቢድዐ እና ሙብተዲዕ ላይ ብርቱዎች ነበሩ። ይህ ማለት ባልተረጋገጠ ወሬ ሰዎችን ይከሱ ነበር፣ በእውር ድንብር ተብዲዕ ያደርጉ ነበር ማለት አይደለም። ሰዎችን ከሱና ለማስወጣት አትቸኩል ስትባል አይክፋህ። የዚህ መልእክቱ ለቢድዐም ለሙብቱዲዕም ጥብቅና እንቁም የሚል አይደለም። እንደዚያ አድርገህ ብትረዳ ራስህን ነው የምትጎዳው።
ቢድዐ እና ሙብተዲዕ ላይ ጠንካራ መሆን ይገባል። ለዚህም የሰለፎችን ብርቱ ማሰጠንቀቂያዎች ማሰራጨት ሁነኛ አማራጭ ነው። ይህንን ስናደርግ ግን ሌላ መልክ ያለው ቡድንተኝነት፣ ጥላቻን መሰረት ያደረገ ፍረጃና ዘመቻ፣ የሰዎችን ንግግር ሆነ ብሎ ገልብጦ እየተረጎሙ ወከባ ማብዛት አይገባም። ይሄ ከሰለፎች አካሄድ ያፈነገጠ ግና በሰለፎች ስም እየተፈፀመ ያለ የስነ ምግባር ዝቅጠት ነው። የራሳችንን የረከሰ ስነ ምግባር ወደ ሰለፎች ከማስጠጋት መቆጠብ አለብን። ከአጥፊዎች ጥፋት ባልተናነሰ የኛ ባህሪ ራሱ ሰዎችን ከሱና እያስበረገገ ነው። መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን ለማረም ሌላ ፅንፍ መርገጥ አያስፈልግም።
በሌላ ጫፍ ለትክክለኛው ኢስላማዊ ዐቂዳ ዋጋ የማይሰጥ፣ ሺርክና ቢድዐ የማይጎረብጠው፣ የቢድዐ አጫፋሪዎች መነካት ምቾት የሚነሳው አካል እንዳለ ይታወቃል። ይህንን ብኩን አካሄድ የምናኮላሸው ራሳችን ጤነኛ አካሄድ ሲኖረን ነው። በዙሪያው ካለ ህዝብ የተኳረፈ፣ እርስ በርስ በመዘራጠጥ የሚታወቅ፣ መስለሐና መፍሰዳ የማይገባው፣ አልፎ አልፎ ሌሎችን ለመክሰስ መረማመጃ ለማድረግ ያክል ብቻ ከሚያነሳቸው የቢድዐ አንጃዎች በበለጠ የተሻለ ለሚቀርቡት የከፋ ጥላቻ ያረገዘ፣ አብይ መታወቂያው ሃሰተኛ ክስና ፍርደ ገምድል ውንጀላ የሆነ ስብስብ የክፋት አካሄዱን በሰለፎች ስም ሲያቀርብ ያሳፍራል። እውነት ለመናገር ብዙዎቻችን ጣት ከምንሰነዝርባቸው አካላት ባልተናነሰ ወይም በባሰ ተበክለናል። ራሳችንን አንዘንጋ። መልእክቱ ለራሴም ጭምር ነው።
በመጨረሻም አደራ! ያልተፃፈ እንዳታነብ! ራስህን ነው የምትጎዳው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor