Get Mystery Box with random crypto!

አመድ በዱቄት ይስቃል ~ እምነታቸው እንዳለ በተረት፣ በአስቂኝ ኹራፋት እና አጉል እምነት የተሞላ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

አመድ በዱቄት ይስቃል
~
እምነታቸው እንዳለ በተረት፣ በአስቂኝ ኹራፋት እና አጉል እምነት የተሞላ እንደሆነ አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። "ፃድቅስ አየሁ ተክለ ሃይማኖት፣ ባንድ እግሩ ቆሞ ሰባት ዓመት" እያሉ እየቀደሱ፣ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ 9 አመት ዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ለኢትዮጵያ ጸለዩ ብለው መፅሐፈ ገድል የፃፉ፣ ግራኝ የወረወራቸው፣ ግራኝ ፈረሱን ያሰረባቸው እያሉ ግዙፍ ቋጥኞችን የሚያሳዩ፣ ቡና መጠጣት፣ ተምር የእስላም ነው እያሉ አሳፋሪ ትንታኔ የሚሰጡ፣ ማርያም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን መቀመጫ ለጎመችለት ብለው መፅሐፍ የፃፉ፣ ማህበራዊ ሚዲያውን በመሪ ጌታዎች የመተት ማስታወቂያ ያጥለቀለቁ ... እነዚህ ናቸውኮ ኢስላምን በአጉል እምነት ሊከሱ የሚነሱት? ልካቸውንማ ሊያውቁ ይገባል። ቆማ'ጣን ቆ'ማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል።
ደግሞኮ ይሄ በተረትና መሰረት የለሽ ኮተቶች ማመን 'ሳይንስ' አምላኪ የሆኑት ሳይቀሩ የሚታወቁበት ነው። ያያያዝኳቸው ፅሁፎች የብሪታኒዋ ንግስት የሞተች ጊዜ የወጡ የታዋቂዎቹ CNN, The New York Times እና Daily Mail ዘገባዎች ናቸው። ለንግስቲቱ የመንግስተ ሰማያት በር ተከፈተ፣ ለሷ ሃዘን ቀስተ ደመና በሰማይ ታየ እያሉ ነው የዘገቡት።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor