Get Mystery Box with random crypto!

በተለይ ለኦሮሞ እና ለአማራ ሙስሊሞች ~ ወንድሞችና እህቶች! እባካችሁ አላህን ፍሩ! ብዙዎቻችሁ ፖ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

በተለይ ለኦሮሞ እና ለአማራ ሙስሊሞች
~
ወንድሞችና እህቶች! እባካችሁ አላህን ፍሩ! ብዙዎቻችሁ ፖለቲከኛ አፋችሁን ከፍታችሁ እየተከተላችሁ እጅግ ፀያፍ የሆነ ዘረኝነት ውስጥ ወድቃችኋል። ፖለቲካ ውስጥ ከመስመጣችሁ የተነሳ የሙስሊም ደም ከምንም የማትቆጥሩበት ደረጃ ላይ ደርሳችኋል። ፖለቲካ በወለደው ጥላቻ የተነሳ ከሃገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ብዙ ሙስሊም እየተጎዳ ነው።
ዱዓቶች አላህን ፍሩ ይህንን ጉዳይ ችላ አትበሉ። የኦሮሞ ሙስሊም የአማራ ወገኑ ህይወት የማያስጨንቀው፣ የአማራ ሙስሊም የኦሮሞ ወንድሙ ህይወት ደንታ የማይሰጠው ደረጃ የደረስነው ለኢስላም የሰጠነው ቦታ ከዘር የረከሰ በመሆኑ የተነሳ ነው።
የመጅሊስ ሰዎች አላህን ፍሩ። የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ባለው በዚህ ጥንብ ዘረኝነት ላይ ባግባቡ ስሩ። የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ማለት መዘዙ ለሁሉም ከባድ ነው። ኢስላማዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የፖለቲከኞችን ይሁንታ አትጠብቁ። ኦሮሚያ ውስጥ ሙስሊሞች ሲጨፈ ^ ጨፉ ከማንም ቀድሞ ሊጮህላቸው የሚገባው ኦሮሞው ሙስሊም ነው መሆን ያለበት። አማራ ክልል ላይ ሙስሊሞች ሲጨፈ ^ ጨፉ አማራው ሙስሊም ነው ከማንም ቀድሞ ሊጮህላቸው የሚገባው። እኛ ለእኛ ካልተቆረቆርን የሙስሊም ወገናችን ህመም ካላመመን ማን ይቆርቆርልን? ደግሞም እንወቅ! በምናጋግለው ፈተና ውስጥ እስካለን ድረስ እጃችን ቀጥታ ባይገባበት እንኳ በሚጠፋው ነፍስ ሁሉ ከአላህ ዘንድ ተጠያቂዎች ነው የምንሆነው። አላህን እንፍራ! አላህን እንፍራ! በዚህ የዘረኝነት በሽታ ከማንም በላይ እየተጎዳን ያለነው እኛው ነን።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor