Get Mystery Box with random crypto!

'ከሰደበኝ የነገረኝ' ~ ከነብያችን ﷺ ክብር ላይ መከላከል ግዴታችን ነው። በባለጌዎች ስራ መቆጣት | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

"ከሰደበኝ የነገረኝ"
~
ከነብያችን ﷺ ክብር ላይ መከላከል ግዴታችን ነው። በባለጌዎች ስራ መቆጣትም ተገቢ ነው። ግን እንዴት ነው የነዚህን ባለጌዎች ስራ ኮፒ ፔስት አድርጎ ማሰራጨት ከሳቸው ክብር መከላከል የሚሆነው? እንዴትስ አስችሏችሁ ነው የነሱን ፀያፍ ንግግር ባደባባይ ደግማችሁ የምትለጥፉት? ወላሂ ከልጁ ብልግና በላይ እንዲህ አይነቱ አካሄድ የበለጠ ያሸማቅቃል። እስኪ አስቡት አንድ ባ ለጌ እጅግ ነውረኛ በሆኑ ቃላት እናታችሁን ቢሳደብና ከዚያ አንዱ ወንድማችሁ ተነስቶ ከእናታችሁ እከላከላለሁ በሚል ስሌት ያንን ፀያፍ ስድብ በያቅጣጫው እያስተጋባ ላ'ገር ቢያዳርሰው ያስደስታችኋል? "ማሻአላህ እናታችንን የሚወድ ጀግና ነው" ብላችሁ ነው የምታሞካሹት? ወይስ በሞኝነቱ ነው የምትሳቀቁት? ከተሳዳቢው ብል ግና በላይኮ የሚያበግነው የዚህኛው ሞኝነት ነው። "ከሰደበኝ የነገረኝ" ሲባል ሰምታችሁ አታውቁም?
ብቻ እንዲህ አይደለም ከኢስላም መከላከል። እንዲህ አይደለም ነብዩን ﷺ መውደድ። ዐረቦች እንዲህ አይነት ውል የሳተ ጥረት ሲያዩ የሚሉት ድንቅ ብሂል አለ። "ሰዕድ ሆይ! ግመል እንዲህ አይደለም የሚነዳው" የሚል።
ነገሩ እንዲህ ነው። ማሊክ ብኑ መና የተሰኘ ይሄ ነው የሚባል ቦታ የሌለው ሰው ነበር። ሌላ ባይችል ግመል መጠበቅ ግን ይችላል። ጥሩ እረኛ ነው። ግመል ጥበቃ ክህሎት የሚፈልግ ሙያ ነው። አንድ አውቃለሁ ባይ ወንድም አለው። ሰዕድ የሚባል። ማሊክ አገባና የደስታውን ጊዜ በቤቱ ሊያሳልፍ ፈልጎ በግመል ጥበቃው ላይ እንዲተካው ወንድሙን ከጠየቀ በኋላ እንዴት አድርጎ መያዝ እንዳለበት ሊነግረው ቢል "ደግሞ ግመል ጥበቃ ሙያ ሆኖ ነወይ?" በሚል ሊሰማው አልፈቀደም። የሆነ ሰዓት ማሊክ ቢወጣ አቶ ሰዕድ ሆየ ዝንጥ ብሎ ለብሶ ወጥቶ ኖኖ ግመሎቹን ባግባቡ ወደ ውሃ ማውረድ አቅቶት፣ በያቅጣጫው ተበታትነውበት ከግራ ቀኝ ሲዋትት ያየዋል። በዚህን ጊዜ ነበር ማሊክ ይህንን ዘመን ተሻጋሪ ስንኝ በወንድሙ ላይ የጣለው።
أوْرَدَهَا سَعْدٌ وسَعْدٌ مُشْتَمِلْ ... مَاهكَذَا يا سعدُ تُورَدُ الإبل
ስለዚህ እንደ ሰዕድ አንሁን። ይሄ የሰሞኑ ዋልጌ የመጀመሪያ ባለጌ አይደለም። የመጨረሻም አይሆንምና ከስህተታችን ትምህርት እንውሰድ። መሰል ጥፋት ሲገጥመን ምን እናድርግ?
1ኛ፦ የባለጌዎችን ነውረኛ ተግባር ባደባባይ መለጠፍ፣ ደግሞ ማስተጋባት፣ አካውንታቸውን/ ገፃቸውን ማያያዝ እጅግ ሰቅጣጭ የሆነ ከአጥፊዎቹ የከፋ ድንቁ ርና ነውና ከዚህ እንቆጠብ።
2ኛ፦ ጠላት ኢስላምን ወይም ነብያችንን ﷺ የሚያንቋሽሽ ፊልም ሲለቅ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰራጭ የሚያደርጉት ሙስሊሞች ናቸው። ይሄ በጣም የሚያም እውነት ነው። "ብታዩትኮ በጣም ነው የሚዘገንነው"፣ "ኧረ የሚወራ አይደለም"፣ ወዘተ እየተባባሉ እየገቡ ያዩታል። እይታው በጨመረ ቁጥር ስርጭቱ፣ ተደራሽነቱ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። በእንዲህ አይነት ሞኝነት ሲበግኑ ያገራችን ሰዎች የሚሉት ነገር አለ። "የራሴን ሞኝ ግደልልኝ፣ የሰውን ሞኝ አኑርልኝ።" ወዳጅ የሚበግንባችሁ አትሁኑ።
መሰል ጥፋት ሲገጥመን ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ፣ ኮፒ ፔስት እያደረግን ስድቡን ሳናስተጋባ፣ "ትርጉሙ ምንድነው" እያልን ሞኞች እንዲተረጉሙት ሳናስታውስ፣ "እንትን ተጠቅማችሁ ተርጉሙት" እያልን መንገድ ሳናሳይ፣ የአጥፊዎቹን አካውንት ሳናስተዋውቅ ሃይማኖታችንን ወይም ነብያችንን ﷺ የተሳደበ አንድ ባለጌ ሰው እንዳለ በተመጠነ መልኩ እየጠቀስን መናገር በቂ ነው። ያለበለዚያ አጥፊው ከሚችለው መጠን በላይ ጥፋቱን እናሰራጨዋለን። ሰላም።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor