Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.49K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 134

2022-07-21 18:40:00 ከአማራ ክልል ውጭ ይህን ጥያቄ ማን ሊያቀርብ ይችላል?


የትሕነግ ቃል አቀባይ ሰሞኑን በሰጠው ቃለመጠይቅ ስለወልቃይት ሴቲት ሁመራ የአማራ ክልል መንግስት ምን ያገባዋል ሲል ተደምጧል። ይህን የተናገረው ካለማወቅ ሳይሆን እውነታ ለመካድ ከመፈለግ እንጅ። እውነታው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሴቲት ሁመራ፣ ጠጋዴ፣ ራያ አለማጣ፣ ራያ ባላ፣ ራያ ወፍላ፣ አለማጣ፣ ከፊል አበርገሌ ወደ ትግራይ ክልል (በወቅቱ ክልል 1) የተካለሉት በሃይል ከመሆኑም በላይ የሽሽግግር መንግስቱን አዋጅ 7/1984 እንዲሁም የኢፌዲሪ ሕገመንግስት ስለክልሎች አወቃቀር አስመልክቶ አንቀጽ 46 (2) የተደነገገውን መርህ በጣሰ መንገድ በመሆኑ ነው።


ትህነግ ሕገወጥ ይዞታውን ለመጽናት ብዙዎች ገሏል፤ የዘር ማጽዳት ፈጽሟል፣ የሕዝብ ስብጥር ለመቀየር (demography reengineering) የሰፈራ ፕሮግራም አካሄዷል። የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 46 (2) በግልጽ እንዳስቀመጠው ‘ክልሎች የሚዋቀሩት ‘በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት' ነው።


ሆኖም ግን እነዚህ አካባቢዎች ወደ ትግራይ የተካለሉትበት መንገድ (ሕገመንግስቱ ከመጽደቁ በፊት በሃይል መሆኑ የማይካድ ቢሆንም) በአንቀጽ 46 (2) የተቀመጠውን ሕገመንግስታዊ መስፈርት በጣሰ መንገድ ነው። ይህ ሕገመንግስታዊ መስፈርት ባይጣስ ኖሮ እነዚህ አካባቢዎች በአማራ ክልል ይካለሉ ነበር። በአጭሩ እነዚህ አካባቢዎች ወደ ትግራይ ተካለው የነበሩበት መንገድ የሕገመንግስቱን አንቀጽ 46 (2) የጣሰ ነው (የሕገመንግስቱ አንቀጽ 46 የሽግግር መንግስቱን በአዋጅ 7/ 84 መርህ እንዳለ ነው ያስቀመጠው))።

እናም የአማራ ክልል መንግስት እያለ ያለው እነዚህ አካባቢዎች በአማራ ክልል መካለለ ሲገባቸው በትግራይ ክልል መካለላቸው ኢሕገመንግስታዊ ስለሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እነዚህ አካባቢዎች ወደ አማራ ክልል እንዲካለሉ በማድረግ ትህነግ በወቅቱ የነበረውን የሃይል የበላይነት ተጠቅሞ የፈጸመውን የሕገመንግስት ጥሰት ሊያርም ይገባል የሚል ነው። ታዲያ ይህን ጥያቄ ከአማራ ክልል መንግስት ውጭ ማን ሊያቀርብ ይችላል? ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ውጭ ይህ ጥያቄ ለማን ሊቀርብ ይችላል (ለነገሩ ትህነግ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅና አልሰጥም ብሏል)።

(ዶ/ር ዮናስ ተስፋ)
16.4K viewsedited  15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 14:29:06
7.5K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 14:29:02 ከሱዳን ወደ ትግራይ ሊላክ የነበረ ወታደራዊ መገናኛ ወልቃይት ጠገዴ ላይ ተይዟል።




በቃብትያ ሁመራ ባህከር ቀበሌ ዙሪያ ከሱዳን ወደ ጠላት ሊደርስ የነበረው ስድስት ወታደራዊ የሞተሮላ ሞባይሎችና መሰል ቁሳቁሶች በፀጥታ አካላት መያዙን የዞኑ የሰላምና ደህንነት ምክትል ሃላፊ አቶ ለምለሙ ባየህ ገልፀዋል። መረጃው ከዞኑ ብልፅግና ገፅ ላይ የተወሰደ ነው።
7.5K viewsedited  11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 22:57:19
3.6K views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 22:56:57 በዚህ አገር የማንሰማው ጉድ የለም!

አቃቤ ሕግ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋትና መብት እንዳይፈቀድለት አቅርቦታል ብሎ ቪኦኤ የዘገበው የዓቃቤ ሕግ መከራከሪያ አስደንጋጭ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ዋስትና አግኝቶ ቢወጣ እርምጃ እንወስድበታለን ማለታቸው ተዘግቧል።
3.6K views19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:19:58
11.6K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:19:50 በትግሬ ወራሪ ሰፈር ፉከራው ደርቷል! ሁለቱም ትናንት የተደረጉ ንግግሮች ናቸው። በሚዲያ ወጥተው እንወራቸዋለን እያሉ ነው።
11.5K viewsedited  14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 12:03:40
8.8K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 12:03:33 በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊ ነኝ ይል የነበረው ቴድሮስ ፀጋዬ አሁን የጃልማሮ አድናቂ፣ የአገረ ትግራይ ምስረታ ኮሚቴ ሆኗል።


ሁሉም እያደር ግልፅ ይሆናል።


ጨፍጫፊውን፣ አሸባሪውን የሚደግፍ፣ መገንጠልን የሚያበረታታው ሰው በሌላ ጊዜ ተገልብጦ ስለ ኢትዮጵያ ሲያወራ ታገኙታላችሁ። ውሸቱን ነው።
8.8K viewsedited  09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 08:16:56
8.2K views05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ