Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ getachewshiferaw — Getachew shiferaw
የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.30K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 127

2022-09-04 08:34:19
12.8K views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 08:33:42 አሸባሪው ትህነግ ህፃናትን በግዳጅ ቀርፆ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ነው!

አሸባሪው ትህነግ ህፃናትን ወደጦር ሜዳ በመማገድ ነቀፌታ እየገጠመው ነው። ለዚህ መልስ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በወረራቸው ከተሞች ያገኛቸውን ህፃናትና በየገጠሩ እረኞችን እያፈነ እየወሰደ ቀርፆ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየሰራባቸው ይገኛል።

ህፃናቱን ፋኖ አባብሎ ወደጦርነት ያስገባቸው አስመስሎ አቅርቧል። ይህ ነውረኛ ስለፋኖ ስለማያውቅ ነው። መጀመርያ ነገር አማራ ክልል ውስጥ በየጊዜው የሰለጠነ በርካታ ፋኖ አለ። ምንም የማያውቁ ህፃናትን የሚያስገባበት መንገድ የለም። ሲቀጥልም ፋኖ የሚያምናቸውን፣ የሚያውቃቸውን ሰዎች ነው ከቡድኑ የሚያስገባው። አይደለም ህፃናትን የሚጠራጠረውን ጎረምሳም አያስከትልም። ከዚህ ባሻገር ለትህነግ ግሪሳ የሚበቃ በርካታ ኃይል ነው ያለው። መጀመርያ አካባቢ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ይቆይ እኔ እበቃቸዋለሁ ብሎ ተፋልሟቸዋል። ፋኖና ልዩ ኃይሉ መከላከያ ሰራዊቱ ብቻውን መስዋዕትነት አይከፍልም ብለው ገቡ እንጅ መከላከያ ሰራዊቱ ለዚህ ግሪሳ እኔ አላንስም ብሎ ነበር። አማራም ቢሆን የሰራዊት ችግር የለበትም። አርሶ አደሩም፣ ሚሊሻውም፣ ልዩ ኃይሉም ሲዘምት ባለፈው አይተውታል። እንደነሱ አምስት ሚሊዮን እየመሰላቸው ይሸወዳሉ። ትህነግ በየስፍራው ያሰለፈው የሀሰት መረጃ የሚያሰራጭና የስነ ልቦና ጦርነቱ ከኋላ እየወጋ ባያስቸግር፣ የውጭ ጠላቶቹ በመረጃና በሰሀት ፕሮፖጋንዳ በማሸበር ባያግዙት የአማራ አንዱ ክፍለ ሀገር ብቻ ለትህነግ በቂ ነው።


በየከተማውና በገጠር ህፃናትን እያገተ በግድ ቀርፆ የፋኖ አባላት ናቸው እያለ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያስተላልፈው ትህነግ፣ ፋኖ ሲሄድበትማ ገደል እንደሚገባ ያውቃል። ገና በስም ፋኖ መጣብኝ ብሎ ተከዜ ወንዝ እየገባ የሰነበተው ፋኖ የህፃን ስብስብ ስለሆነ አይደለም።
13.1K viewsedited  05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 17:28:21
15.7K views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 17:27:43 አካም! አካም! ጅርቱ!

(ይሄንም የማታምኑ ብፁሃን ትኖራላችሁኮ)

ኤርሚያስ በኦሮሞነቴ ተጠቃሁ ብሏችኋል! የኦህዴድ ብልፅግና አመራሮችም ይቆሙልኛል ብሏችኋል። ደጋፊ ነኝ የምትል እኔ ላይ እንዳትነፋረቅ ቪዲዮውን ተመልከት!

ኤርሚያስ ለገሰ ትናንት በወጣው መረጃ ላይ መልስ ሰጥቷል። የሰጠው መልስ በተለይ ለአንዳንድ ደጋፊዎቹ አስደንጋጭ ነው። አላስረዝመውም። አጠር ላድርገው!

1) የኦህዴድ ብልፅግና ሰዎች አግኝተውኝ እኛ የለንበትም ብለውኛል ብሏል። በለው! በለው! ሽመልስን ነው? ታከለ ኡማን ነው? አብይ አህመድን ነው? እነማንን ይሆን ከኦህዴድ ብልፅግና ውስጥ የሚያገኘው? ኧረ የዘንድሮው መስከረምስ ሳይጠባ ጉድ ሊሰማ ነው። ኦህዴድ አንዱን ሲያፍን ለሌላው ጥብቅና ሲቆም! አቤት ተረኝነት!

2) ያጠቃኝ የአማራ ብልፅግና ነው። የአማራ ወኪል ነኝ የሚሉ የሚያጠቁኝ በኦሮሞነቴ ነው ብሏችኋል። (ትርጉም ነው)። ለምን እዝቅኤል ጋቢሳ፣ ፀጋዬ አራርሳ፣ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ ላይ ትኩረት ተደረገ ብሏችኋል። የሌሎቹን ስም እስከአያታቸው አልጠራም። እስከአያቱ የጠራው የራሱን ብቻ ነው። በግልፅ በኦሮሞነቴ ነው የተጠቃሁት ብሏል። የኦሮሞ ልጆች ተመርጠን ተጠቃን ብሏችኋል። ያዝ እንግዲህ!

3) የኦህዴድ ብልፅግና ሰዎችን ማድረግ ያለባችሁን አድርጉ ብያቸዋለሁ ብሏል። ጉድ ነው መቸም! ኤርሚያስ ዋናውን ስልጣን የያዙትን የኦህዴድ ብልፅግና አመራሮች መካከል ማድረግ ያለባችሁን አድርጉ ብሎ የሚያዛቸው እነማንን ነው? ሽመልስን ነው? ታዬን ነው? ኧረ ጎበዝ አልቆልናል። ለኤርሚያስ ሲባል ማድረግ ያለባቸውን የሚያደርጉለት የኦህዴድ ብልፅግና አመራሮች እነማን ናቸው? ቆይ ቆይ! ነገሩ ራሱ ምን ጉድ ነው? ምንሸ ነው አለ የአዲስ አበባ ሰው

4) የኦህዴድ ብልፅግና አመራሮች ይሄ ለእኛም ስድብ ነው ብለውኛል። ለእኛም ስድብ ነው ሲሉኝ ለእኛም ስድብ ነው ብላችሁ ፃፉ ብያቸዋለሁ ብሏል። በኤርሚያስ ላይ የሆነ ነገር ተደረገ ብለው እኛ ተሰደብን የሚሉ የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮች ከተገኘ ኤርሚያስ ከየት ጎራ ነው አንተው? ወነግ ነው? ኦሮሙማ ነው? አካም አካም ነው? ጅርቱ ነው? ጉድና ጅራት ወደኋላ ይመጣል ነው? ምንድን ነው?

ቪዲዮው ላይ ሳይቀነስ፣ ሳይጨመር፣ ሳይቆረጥ አለላችሁ።

ነገሩ ምንድን ነው? አካም! አካም! ጅርቱ! ፈያዳ! የኤርሚያስ ደጋፊ ቪዲዮውን አይተህ ፈንዳ!

አቤት! አቤት! ወዮ! ወዮ! አፋኙ ኦህዴድ አዳኝ ሆኖ ሲመጣ! ኧረ ምን አቅለበለበኝ በማርያም! ኦህዴድን ኤርሚያስ አዞት!

እየመጣሽ ተኝ ቀኑ ቅዳሜ ነው አለ ሰውዬው

ነገ ደግሞ እሁድ ነው በጠዋት በስመአብ…በስመአብ……ኧረ በስመአብ………ብላችሁ ቤተ ክርስትያን ተሳለሙ!

እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ! በዚህ አያያዛችንስ አትምረንም! መስከረም ከመምጣቱ በፊት አንተው ፈጣሪ ና! መስከረም ምን ያደርጋል?
15.8K viewsedited  14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 16:01:41
17.2K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 16:01:27 ትህነግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ የፈፀመበት የማይካድራ ህዝብ ለጥምር ጦሩ በዚህ መልኩ ስንቅ እያዘጋጀ ነው። ጨፍጫፊውን ትህነግን ይታገላል። ለሚጠብቀው ጥምር ጦር ደጀን ይሆናል።
16.6K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 14:27:24
18.0K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 14:27:19 ወጉማ ተይዟልኮ! ይልቅስ ሄደህ አስሬን ቁጠር በለው!


ትናንት ብሉምበርግ የሚባል ሚዲያ ለትህነግ ተስፋ የሚሆን አንድ ዜና ሰርቶ ነበር። ኢትዮጵያ በሰላም አስከባሪነት የላከቻቸው የትግራይ ተወላጅ መኮንኖች ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም ብለው ወደ ሱዳን አቅንተው ነበር። 528 ናቸው። ሁሉም ሰሞኑን ውጊያ በተደረገበት አካባቢ ስልጠና እየሰጡ ነበር። ብሉምበርግ ታዲያ ከትህነግ በተሰጠው የውሸት መረጃ መሰረት እነዚህ መኮንኖች የሚመሩት የትህነግ ታጣቂ ሁመራን ሊይዝ እንደሆነ አድርጎ አውርቶ ነበር። ውሸት ቁርሳቸው፣ ምሳቸው፣ ራታቸውም ነው።

እውነታው ሌላ ሆነ። ጥምር ጦሩ ገና በመጀመርያው ቀን የት ልግባ አስባላቸው። በሁለት ቀን ሁሉም ምሽግ ተሰባብሮ የተረፉት ወደ ሱዳን እግሬ አውጭኝ ሲሉ አብዛኛውን ጥይትና ቀሪውን የተከዜ ውሃ በላው።

ተበታትኖ የሚገኘውን የትህነግ ኃይል ጥምር ጦሩ የማፅዳት ስራ እየሰራ ይገኛል። እንደምንም ወደ ሱዳን የተሻገረው የትህነግ ታጣቂ አሻባ የተባለ ቦታ ላይ የሱዳን ወታደሮች መሳሪያህን አራግፍ እያለው ነው። ሱደን የከረመው የትህነግ ኃይል ሲፎክር ስለከረመ አሁን እግሬ አውጭኝ ሲል ሱዳኖቹ እንዴት ይታዘቡታል?

ከሱዳን አቅጣጫ የመጣው የትህነግ ኃይል ሁመራን እይዛለሁ ብሎ አስወርቶ በጥምር ጦሩ አሳሩን ሲበላ ከፍተኛ አዛዦቹን ጭምር አጥቷል። በዚህ ውጊያ ኮ/ል መኮነን ኃይሉ የተባለ የትህነግ ክ/ጦር አዛዥን ጨምሮ በሺህ የሚቆጥር ሬሳውን ጭኖ ለመሸሽ ሞክሯል። በርካታ ታጣቂ ሲሮጥ ተከዜ ሲወስደው፣ በውጊያ የሞቱበትን ግን በጀልባ እየጫነ ወደ ሱዳን ለመሻገር ጥሯል። ነፍስ ያለውን ወንዝ ላይ ጨምሮ ሙት ተሸክሞ ይሄዳል። ትህነግ በብሉምበርግ ያሰራው ደግሞ በጀግኖቻችን መስዋዕነት ህልም ሆኖ ቀርቷል። ወግ ብቻ!
17.9K viewsedited  11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 12:01:55
18.8K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 12:01:03 ትህነግ በሀሰት ትምህርት ቤት ወዘተ ተመታብኝ ይላል። ድሮኗ ግን የምትመታውን ለይታ ታውቃለች።
18.7K viewsedited  09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ