2022-09-06 19:44:46
ጠይቋቸው! ትኮሩበታላችሁ!
በማሕበራዊ ሚዲያ የሚተዋወቁ ወጣቶች ሆስፒታል የሚገኙ ጀግኖችን ገንዘብ አሰባስበው ጎንደር ሆስፒታል ሄደው ጠይቀዋል። አብልተዋቸዋል። ክፍት ጫማና ሌሎች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች አድርሰዋል። እናመሰግናለን!
ጀግኖችን ጠይቋቸው። በዛውም ገራሚ ጀብዱ ያጫውቷችኋል። ለዚህ ሕዝብ ቢቻል ሁለት ሶስት ጊዜ እሞትለታለሁ ብለው ልባችሁን ያሞቁታል። ቲሸርቶች፣ የእርድ እንሰሳ፣ አጥሚት፣ ክፍት ጫማ፣ ቁምጣ ወዘተ ይዘው ሊጠይቁ የሄዱ ሰዎች ልባቸው በደስታ ተሞልቶ ሲመለሱ አይቻለሁ። የምትችሉ ጠይቋቸው። ለአገር ሲሉ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ከተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል የመጡ ናቸው። እንደ እናት፣ እንደ ወንድም፣ እንደ ዘመድ ጠይቋቸው። ትኩሩበታላችሁ።
13.4K viewsedited 16:44