Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ትህነግ ህፃናትን በግዳጅ ቀርፆ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ነው! አሸባሪው ትህነግ ህ | Getachew shiferaw

አሸባሪው ትህነግ ህፃናትን በግዳጅ ቀርፆ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ነው!

አሸባሪው ትህነግ ህፃናትን ወደጦር ሜዳ በመማገድ ነቀፌታ እየገጠመው ነው። ለዚህ መልስ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በወረራቸው ከተሞች ያገኛቸውን ህፃናትና በየገጠሩ እረኞችን እያፈነ እየወሰደ ቀርፆ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየሰራባቸው ይገኛል።

ህፃናቱን ፋኖ አባብሎ ወደጦርነት ያስገባቸው አስመስሎ አቅርቧል። ይህ ነውረኛ ስለፋኖ ስለማያውቅ ነው። መጀመርያ ነገር አማራ ክልል ውስጥ በየጊዜው የሰለጠነ በርካታ ፋኖ አለ። ምንም የማያውቁ ህፃናትን የሚያስገባበት መንገድ የለም። ሲቀጥልም ፋኖ የሚያምናቸውን፣ የሚያውቃቸውን ሰዎች ነው ከቡድኑ የሚያስገባው። አይደለም ህፃናትን የሚጠራጠረውን ጎረምሳም አያስከትልም። ከዚህ ባሻገር ለትህነግ ግሪሳ የሚበቃ በርካታ ኃይል ነው ያለው። መጀመርያ አካባቢ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ይቆይ እኔ እበቃቸዋለሁ ብሎ ተፋልሟቸዋል። ፋኖና ልዩ ኃይሉ መከላከያ ሰራዊቱ ብቻውን መስዋዕትነት አይከፍልም ብለው ገቡ እንጅ መከላከያ ሰራዊቱ ለዚህ ግሪሳ እኔ አላንስም ብሎ ነበር። አማራም ቢሆን የሰራዊት ችግር የለበትም። አርሶ አደሩም፣ ሚሊሻውም፣ ልዩ ኃይሉም ሲዘምት ባለፈው አይተውታል። እንደነሱ አምስት ሚሊዮን እየመሰላቸው ይሸወዳሉ። ትህነግ በየስፍራው ያሰለፈው የሀሰት መረጃ የሚያሰራጭና የስነ ልቦና ጦርነቱ ከኋላ እየወጋ ባያስቸግር፣ የውጭ ጠላቶቹ በመረጃና በሰሀት ፕሮፖጋንዳ በማሸበር ባያግዙት የአማራ አንዱ ክፍለ ሀገር ብቻ ለትህነግ በቂ ነው።


በየከተማውና በገጠር ህፃናትን እያገተ በግድ ቀርፆ የፋኖ አባላት ናቸው እያለ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያስተላልፈው ትህነግ፣ ፋኖ ሲሄድበትማ ገደል እንደሚገባ ያውቃል። ገና በስም ፋኖ መጣብኝ ብሎ ተከዜ ወንዝ እየገባ የሰነበተው ፋኖ የህፃን ስብስብ ስለሆነ አይደለም።