Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ንብረት ወደ መቀሌ እየተጫነ ነው! በትህነግ ከተወረረው ራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ንፁሃን | Getachew shiferaw

የአማራ ንብረት ወደ መቀሌ እየተጫነ ነው!

በትህነግ ከተወረረው ራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ንፁሃንን አነጋግሮ ሰሜን ወሎ ዞን መረጃ አጋርቷል። ከእነዚህ መካከል፦

1) የትህነግ ታጣቂ በወረራ በያዛቸው የራያ ባላ፣ የራያ አላማጣ፣ የወፍላ ወረዳ እንዲሁም የአላማጣ እና የኮረም ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የመንግስት እና የሃይማኖት ተቋማቶች ንብረት በመቅደድ፣በማቃጠልና ወደ መሃል ትግራይ ሲጭን ሰንብቷል።

ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው በቆቦ ከተማ ተፈናቅለው ለሚገኙት ተፈናቃዮች የምግብ ዱቄት ይዘው የመጡት የአስተዳደሩ ተወካዮች ይህ ድጋፍ ለዚህ ህዝብ የሚመጥንና የሚገባ ሆኖ ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ ባዷችንን ከምንመጣ በማሰብ ሲሆን፣ የደሴ እና የኮምቦልቻ ህዝብ አምሳያው የሆነው የራያ እና የወፍላ ሕዝብ ወደ ቀየው እንዲመለስ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

2) የአርሶ አደሩን የአትክልትና የፍራፍሬ ውጤቶች የሚጫነው ተጭኖ ያልቻሉትን ማውደማቸውንና ማፈናቀላቸው ታውቋታውቋል።

3) ቤት ለቤት በመፈተሽ ወጣቶችን ባለፈው ጦርነት ተሳትፏል በሚል ግድያ እየፈፀሙ ስለሆነም ተጨማሪ መረጃዎች ወጥተዋል።

ትህነግ/ህወሓት ራያን መሬቱን እንጅ ህዝቡ የትግራይ እንዳልሆነ እንደማይክደው የሰሞኑ ክስተት ማሳያ ነው። ከራያ የህዝብ ንብረትን ዘፈው እያጓጓዙ ያሉት ወደ ራሳቸው ግዛት ወደ ትግራይ ነው። ራያ ግዛታቸው ስላልሆነ የሚዘረፍና የሚጨፈጨፍ ጠላታቸው አድርገው የፈረጁት ነው።