Get Mystery Box with random crypto!

የጠለምት አማራ ማንነት በከበረ መስዋዕትነታችን በዘላቂ ድል ይቋጫል! (ከጠለምት አማራ ማንነትና | Getachew shiferaw

የጠለምት አማራ ማንነት በከበረ መስዋዕትነታችን በዘላቂ ድል ይቋጫል!

(ከጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)


በታሪክ፣ በሕግና በሞራል አግባብ ጠለምትና አካባቢው የበጌምድር ስሜን ጎንደር ክፍለ ሃገር ክፋይ ማንነት (አካል) ነው፡፡
“ጠለምት” ከነባሩ ጠለምትና አድርቃይ ወረዳዎች በተውጣጡ 25 ቀበሌዎች የተመሰረተ፣ 3 ወረዳዎችን (ማይጠምሪ ዙሪያ፣ ዲማ እና ማይጠምሪ ከተማን) ያካትታል፡፡ ይህ ቀጠና እንደ ወልቃይትና ጠገዴ ሁሉ በ1984 ዓ.ም በወረራ ተወስዶ የቆየ የጎንደር አማራ ግዛት ነው፡፡ ሕወሓት በ1968ቱ ማኒፌስቶው ጠለምትን የትግራይ አካል አድርጎ ቢያሰፍርም፤ ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ ነው፣ ተከዜ ወንዝን በመሻገር ቀጠናውን ለጦር ቤዝነት ያዋለው፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ 2015 ዓ.ም መጀመሪያ ድረስ የጠለምት አካባቢ በሕወሓት አገዛዝ ሲሰቃይ ቆይቷል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት የጸደቀው በ1987 ዓ.ም ሲሆን፤ ሕወሓት እነዚህን አካባቢዎች ወደ ትግራይ ያካለላቸው ግን ከ1984 ዓ.ም በፊት ስለመሆኑ ነው፡፡ እኛ የጠለምት አማራዎች ያለሕግ እና ያለሕዝብ ይሁንታ በጉልበት ነበር ወደትግራይ ክልል በጭፍለቃ የተካለልነው፡፡

ከጠለምትና ከአድርቃይ ተቆርሰው በተወሰዱ ግዛቶች ውስጥ ህወሓት ብዛት ያላቸው ሰፋሪዎችን ባለማስፈሩ በአካባቢው ያለው የሥነ-ሕዝብ ስብጥሩም ሆነ የሥነ-ልቦናው ሁኔታ አማራነት የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ሕወሓት ጠለምትን እና አካባቢውን ለመውረር የፈለገበት ምክንያት አንደኛ አካባቢው ለወታደራዊ ስትራቴጅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጠለምትና አካባቢው ያለው የተፈጥሮ ሀብት እጀግ ብዙ ከመሆኑ ጋር ይያያዛል፡፡ የቦታው አቀማመጥም ለቱሪስት መስህብነት ያለው ፋይዳ፣ የልዩ ማዕድናት መገኛ፣ የደን፣እምነ-በረድና የእጣን ሙጫ ምርት፣ የእንስሳት ሀብቱ ብዛት የጠለምት በረከተ-ፀጋዎች ናቸው፡፡ በማዕድን ዘርፍ በተለይ የወርቅ ክምችቱ እጅግ ብዙ በመሆኑ ህወሓት ጠለምትን ሲያደማ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ ለትግራዩ ሳባ የእምነ-በረድ ፋብሪካም ማዕድኑ የሚሄደው ከጠለምት መሬት ነው፡፡

በአጠቃላይ፣ ትግራይ አብዛኛውን የማዕድን ሀብቷን የምታፍሰው ከጠለምት ቀጠና እንደነበረ መላው የአማራ ሕዝብ፣ ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲያውቁልን እንወዳለን፡፡ የአማራ ሕዝብና አመራሩ፣ ይህን እውነታ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ የትግራይ ሰዎች ከዐድዋ፣ አክሱምና መቀሌ ድረስ መጥተው፣ የጠለምትን ሁለንተናዊ እምቅ ሀብትና ጥቅም ተገንዝበው በወረራ መዝለቃቸው ባይጠፋቸውም ‹ጠለምት ወይም ሞት!› ብለው ከ30 ዐመታት በላይ ሲጠቀሙበት፤ ባለ ርስቱ ጎንደሬ፣ ባለቤቱ አማራ አካባቢውን ባለማወቅ ያላግባብ ጥቅሙን አሳልፎ ሰጥቶ ከርሟል፡፡ አሁን ግን መላ አማራ ነቅቷል፤ የማንነት ትግሉ ተወናይ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡
የጠለምትን የማንነት ትግል ገና ከጅምሩ ለማደናቀፍ ሕወሓት ከቅጥረኛ ወኪሎቹ ጋር ሆኖ ሰርቷል፡፡ በ1985 ሕዝቡ 80 ሽማግሌዎችን መርጦ ቅሬታውን ለአማራ ክልላዊ መንግሥት ለማቅረብ መወሰኑን ተከትሎ፣ ከመሃላቸው አራት ሽማግሌዎች በወቅቱ የክልሉ ፕሬዚዳንት ለነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ አቤቱታቸውን አድርሰዋል፡፡ አቶ አዲሱም አቤቱታ አቅራቢዎቹን የ80ዎቹን ወኪሎች ስም ዝርዝር እንዲሰጧቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለትግራይ አስተዳደር አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ የትግራይ አስተዳደርም ለመጀመሪያ ጊዜ አቤቱታውን ለአማራ ክልል መንግሥት ያቀረቡትን አራት ተወካዮች አስሮ በመውሰድ ረሸኗቸዋል፡፡ በሂደትም፣ ቀሪዎቹን 76 ተወካዮች አንድ ባንድ እየለቀሙ አጠፍቷቸዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ጠለምት መሬት ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የአማራነት ጥያቄ አንስቶ ፍትሕን መጠየቅ ከባድና የማይታሰብ በመሆኑ፤ ሌላ የትግል አማራጭ መፈለግ የግድ ሆነ፡፡

በዚህ አስገዳጅ እውነታ የተነሳ የመጀመሪያው የከፋኝ (ፋኖ) ተጋድሎ በጠለምት ተጀመረ፡፡ ጠለምት ውስጥ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ የአማራነት ጥያቄን ማንሳት የማይቻል መሆኑን ተከትሎ፤ በርካታ ተወላጆች ጫካ ገብተው ተፋልመዋል፡፡ በአርማ ደጋ በረሃ ውለው ማደሩን ተያያዙት፡፡ የጠለምት ፋኖዎች ሕወሓትን አብዝተው ፈተነው፣ እረፍት ነስተውታል፣ በወቅቱ ትግሉ የሚጠይቀውን ከባድ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ወራሪው ኃይል የጠለምት መሬት የእግር እሳት እስከሚሆንበት ድረስ ዋጋ አስከፍለውታል፡፡

በዚህ ትግል ሂደት ውስጥ ሕወሓት የቻለውን ገደለ፤ አንዳዶቹን የነጻነት ታጋዮች ደግሞ በምህረት ስም እንዲገቡ አድርጎ ረሸነ፡፡ በዚህ የፋኖነት ዘመን በርካታ ጀግኖች የሕወሓትን ታጋዮች ጥለው ወድቀዋል፡፡ በወቅቱ ‹ሕወሓትን ስለማናምን በምህረት አንገባም› ብለው የቀሩት ፋኖዎች እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አድራሻቸውን ሰውረው ገባ-ወጣ ያለ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው፣ ከጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም ጀምሮ አገራችን ከሕወሓት ጋር በገባችበት ጦርነትም ንቁ ተሳታፊ በመሆን፣ በጠለምት ግንባር የታሪክ አደራቸውን አስቀጥለዋል፡፡
በአጠቃላይ ትግሉ በሁለት ትውልዶች ቅብብል አሁን ያለበት ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፤ የቀደሙት ሰማዕታት ‹ትግላችሁ ከንቱ አልቀረም› ብለን ዘላቂ ድላችን በከበረ መስዋዕትነታችን ለማረጋገጥ ዛሬም ቃላችን እናድሳለን፡፡
በመሆኑም፡-

1) ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጀሮ የነፈገው የዘር ማጽዳት ወንጀል በጠለምት የአማራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል የተፈጸሙ የዘር ማጽዳት ወንጀሎች አንዴ ተጀምረው በተወሰነ የጊዜ ገደብ የተጠናቀቁ ቢሆንም፣ በጠለምት ሕዝብ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል ግን በአይነትም ሆነ በድርጊት የተለየ ነው፡፡ ለሠላሳ ዓመታት ያለ ማቋራጥ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ እኛን የማጽዳት ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በሺህዎች የሚቆጠሩ አማሮች በማንነታቸው ተገድለዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖቻችን ወዳልታወቁ ስፍራዎች ታፍነው ተወስደው በእስር ሲማቅቁ ኑረዋል፤ ብዙዎችም ባሉበት አልፈዋል፡፡ በጥቅሉ በሠላሳ ዓመቱ የወያኔ አፓርታይዳዊ ዘመን በተለየ ሁኔታ በከተሞች በርካታ የጠለምት አማራ ከእርስቱ ተፈናቅሎ እንዲሰደድ ተደርጓል፡፡

ዛሬ የዘመናት ትግላችን ሂደትና የሁለት ትውልዶች ቅብብል መስዋዕትነታችን የጠለምት አማራ የተነጠቀ ማንነቱን ማስመለስ ችሏል፡፡ እኛ የጠለምት አማራዎች ያስመለስነው ማንነት እንጅ የነጠቅነው መሬት የለም!! የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም፤ የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም!! ማንነታችን አማራ ድንበራችን ተከዜ ነው!!

2) የሕወሓት አፓርታይዳዊ አገዛዝ ከተዘረጋ ጀምሮ በጠለምት የአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል ታውጆ ተፈጻሚ ተደርጓል፡፡ በዋልድባ ገዳም ይህ ነው የማይባል ግፍና መከራ ደርሷል፡፡ መነኮሳት በብሔራቸው ምክንያት ሞት ታውጆባቸው ተሳድደዋል፤ ተፈናቅለዋል፡፡ በተገኙበት ታፍነው ተወስደዋል፡፡ በእኛ በኩል በዓለማቀፍ መመዘኛዎች ስንመለከተው በጠለምት የአማራ ሕዝብ ላይ ዓለም ያልሰማው የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞበታል፡፡ ለዚህም ወንጀለኞች በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲጠየቁ እንጠይቃለን!! የግፉዓን ጠበቃ ለመሆን በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የምትሰሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት፣ በጠለምት የአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል የፈጸሙ የሕወሓት አመራሮች ለፍርድ እንዲቀርቡ በምናደርገው ጥረት ከጎናችን ሁናችሁ ሰብዓዊ