Get Mystery Box with random crypto!

ውግንና እንድታሳዩን እንጠይቃለን! 3) በወራሪው ሕወሓት አገዛዝ ስር የነበረው የጠለምት አማራ ባ | Getachew shiferaw

ውግንና እንድታሳዩን እንጠይቃለን!

3) በወራሪው ሕወሓት አገዛዝ ስር የነበረው የጠለምት አማራ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ከባድ የሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዷል፡፡ አያሌ ወገኖቹ በጅምላ ተገድለውበታል፡፡ በማንነቱ ሞትን የማስተናገድ መራር ዕጣ ፈንታ በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ገብቷል፡፡ እንዲሳደድና እንዲፈናቀል ተደርጓል፡፡ ሃብትና ንብረቱንም ተዘርፏል፡፡ ለዚህም በዓለማቀፍ ተሞክሮዎች መሰረት ለደረሰብን ግፍና በደል ካሣ እንጠይቃለን፡፡ የምንጠይቀው ካሣ ለሰላሳ ዓመታት በዘለቀው የሕወሓት የአፓርታይድ የአፈና አገዛዝ ያጣናቸውን በሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ሕይወት ባይመልስልንም፣ ለደረሰብን ግፍና በደል እውቅናው ቁስላችንን ያሽረዋልና፣ የፍትሕና የካሳ ጥያቄችን ገፍተን እንቀጥላለን፡፡

4) በሕወሓት የግፍ አገዛዝ ተማርረውና በእርሱ አስገዳጅነት ከጠለምት እና አካባቢው የፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደቀደመ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የማድረጉ ስራ የፌዴራሉ መንግሥት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ሊሰራው የሚገባ ቁልፍ ተግባሩ እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡ የጠለምትን ሕዝብ በጀት በመከልከልም ሆነ የልማት ድጋፎችን በመንፈግ ለዘመናት የታገለለትን አማራዊ ማንነት ጥያቄ ማስጣል አይቻልምና የፌዴራል መንግሥት የመደበኛና የካፒታል በጀታችንን እንዲለቅልን እንጠይቃለን፡፡

5) እኛ የጠለምት አማራዎች አስተዳደራዊ ነጻነታችንን በተመለከተ ትላንትም ሆነ ዛሬ ቃላችን አንድ ነው፡፡ ወደኋላ ላንመለስ ነጻ ወጥተናል፡፡ ስለማንነታችንም ከእኛ በላይ ምስክር ሊሰጥ የሚችል አንዳች አካል የለም፡፡ ከእንግዲህ ከትግራይ ሊመጣ የሚያስብ የትኛውም አካል የእኛን አማራዊ ማንነትና አስተዳደር አምኖ ተቀብሎ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከወንጀል ነጻ መሆኑን ሳናረጋግጥ የምናስተናግደው አንዳችም እንግዳ አይኖርም፡፡ ለእንግዶች እንጂ ለወንጀለኞች ቦታ የለንም!!

6) ተፈጥሯዊ ድንበራችን የሆነውን ተከዜ ወንዝን በጋራ የምንጋራው የትግራይ ወንድም ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች በጠለምትና አካባቢው በሠላምና በነጻነት መኖር ይችላሉ፡፡ ሕግና ሥርዓትን አክብረው ለሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ጠለምትና አካባቢው ክፍት ነው፡፡ ነገር ግን እኛ የጠለምት አማራዎች፣ ማንነታችን አማራ በመሆኑ አስተዳደራዊ ክልላችን የማንነታችን አካል ከሆነው የአማራ ክልል ጋር ሁኖ በሕግ እንዲጸናልን የፌዴሬሽን ምክር ቤትን አጥብቀን እንጠይቀለን፡፡

7) የጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄን መላው ፍትሕና ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይጋሩታል፤ ጥያቄውንም ጥያቄቸው አድርገውታል ብለን እናምናለን፡፡ የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች የጠለምት አማራ እየጠየቀ ያለው፣ ‹ማንነቴ አማራ ነው፤ ማንነቴም በአስተዳደራዊ ነጻነት ይከበርልኝ› የሚል መሆኑ ታውቆ ያደረ ነውና ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!

8/ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለአጭር ጊዜም ቢሆን አንፃራዊ ሰላም አግኝቶ የነበረው የራያ ህዝብ ለአራተኛ ጊዜ በተደረገበት ወረራ በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል ንብረታቸው ተዘርፋል ወድሟል በርካታ የሰብአዊ ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛል። በዚህ የወራረ ተግባር በጠለምት 3 ቀበሌዎች በወራር ይዞ ከመገኘቱም በተጨማሪ ሌሎች አካባቢወችንም ለመውረር ትንኮሳወችን እያደረገ ይገኛል።
ይህ የወረራ ተግባር እየተፈፀመ ያለው ደግሞ የህወሐት የታጠቁ ሐይሎች በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ትጥቃቸየውን አለመፍታታቸው ነው።
ይህ ትንኮሳ ህዝብ ተረጋግቶ ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንዳይዘጋች ከፍተኛ ስጋት ደግኖ ይገኛል። ስለሆነም መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድቶ የወራሪውን ተንኮሳ እንዲያስቆም በጠለምት አማራ የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሜቴ ስም እንጠይቃለን።

የጠለምት አማራ ማንነት ትግል በከበረ መስዋዕትነታችን በዘላቂ ድል ይቋጫል!

ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕት

የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ

ሚያዚያ 13/2016 ዓ.ም.

ማይጠምሪ-ጎንደር

ኢትዮጵያ