Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ getachewshiferaw — Getachew shiferaw
የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.30K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 129

2022-09-01 17:32:56 ወርቄዎች ይመስክሩ!

ወርቄዎች ከትህነግ ጋር እያደረጉት ያለው ውጊያ ሶስት ቀን አስቆጥሯል። ባለፈው አመት የራያ ወርቄ ቀበሌ ፋኖዎች ባደረጉት ተጋድሎ ይህን ቀበሌ ትህነግ አልደፈረውም። ዘንድሮ ደግሞ ለበቀል መጥቷል። ታደሰ ወረደ ከፋኖ ጋር ጠብ የለንም ቢልም ጠብ ብቻ ሳይሆን ቂም በቀል እንዳለባቸው ራያ ወርቄ ላይ ያደረጉት ዘመቻ ምስክር ነው። ፋኖ ለትህነግ መድሃኒቱ እንደሆነም ወርቄዎች ምስክር ናቸው። ሶስት ቀን ሙሉ በሰው መአበል የሚመጣውን የትህነግ ኃይል አይቀጡ ቅጣት እየቀጡት ይገኛሉ።
14.0K viewsedited  14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:09:38 አሸባሪው ትህነግ ትናንት በተለቀቀ አንድ መግለጫው ፋኖዎች ጋር ጠብ የለንም ብሎ ቀልዷል። የሸዋ ፋኖ ደግሞ "እሷን ስትገረፍ ታወራታለህ" ብሎ ወልዲያ ገብቷል።
16.7K views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:54:07
19.9K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:53:51 የወልቃይት ጠገዴ ጀግኖች አሸባሪውን ለመፋለም እንዲህ ተምመዋል!
19.4K views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:23:46
20.7K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:23:21 አሜሪካ ምን ነክቷት ነው?

ኢትዮጵያውያን ለአሜሪካ ያላቸው እይታ መልካም ነበር። ኢትዮጵያውያን የአሜሪካውያንን የመንግስት ስርዓታቸውን ያደንቃሉ። ፊልማቸውን ይወዳሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ካፌና ሆቴል እንኳን በአሜሪካ ከተሞች ስም ነው የሚጠራው። ከሳዳም ጋር ያደረጉትን ጦርነት ወቅት የገጠር ከተማ እየተምርኩ ነበር። ያኔ ቴሌቪዥን በየቤቱ አልነበረም። ሻይ ቤት ሄደን ነበር የምናየው። ያን ጦርነት ታዲያ እንደ እግር ኳስ ነበር የምንመለከተው። ቀጥታ ስርጭት አይደለም። ምሽት ላይ ከየቦታው የመጣው በርካታ ሰው ወንበር አጥቶ ቆሞ ይመለከታል። ጋዜጠኛው አሜሪካ ድል እየቀናት እንደሆነ ሲናገር የሚደግፈው ቡድን ጎል እንዳገባ ወጣቱ ይጨፍራል። በለው ይላል። ያ ወጣት የአሜሪካን ፖሊሲ በደንብ ባያውቅም ተፅዕኖው ግን ነበር። ቀደም ሲል የነበረው መልካም ግንኙነት ገጠር ሳይቀር ደርሷል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ግራ ዘመሙ ትውልድ እንኳን ስለ አሜሪካ የከፋ አቋም ያስያዘው አይመስልም።

ዩኒቨርሲቲ ሲሻሊዝም እየተማርንም፣ አሜሪካ የምታደርጋቸውን እያወቅንም አሜሪካን የሶሻሊስቶቹ ጀብደኞች እንድንጠላት አላደረጉንም ነበር። የኦባማ ምርጫ ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ቀጥታ ስርጭቱ ታይቷል። ኢትዮጵያውያን የመኪናቸውን ስም ሳይቀር ኦባማ ብለው ቀይረውታል። ጥቁር ስለሆነ ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያውያን የጥቁሩ ዓለም ግንባር ቀደም አርበኛ እንደሆኑ ያውቃሉ። የአሜሪካ እሴት ነው የሚሉትንም ስለሚያደንቁ ነው።

አሜሪካ በጦርነት እንዴት አንድነቷን እንደጠበቀች ስለሚታወቅ ኢትዮጵያውያን ሞዴል ያደርጓታል። ብዙ ኢትዮጵያውያን የተስፋ ምድር አድርገው ይመለከቷት ነበር። ደሕና ገንዘብ ስለሚሰሩባት ብቻ ግን አይደለም። ሴራም ይኑረው፣ ለጥቅሟ የፈለገችውንም ታድርግ አሜሪካ የምትከበርባቸው እሴቶች ነበሩ። የአገር አንድነት ላይ አደጋ የደቀነን አሸባሪ በዚህ ደረጃ ወርዳ ትደግፋለች ብሎ መገመት ከባድ ኖሯል።

ያች ጦርነቷን እንደ እግር ኳስ በምሽት ሌላ ቦታ አይተን "በይው አሜሪካ!" ያልናት አገር የአሸባሪው ትህነግ ተራ አክቲቪስት ስትሆን እንደማየት የሚገርም ነገር የለም።

ዛሬ የተፈጠረው እንደዚህ ነው። የትህነግ ሰዎች በጌታቸው በኩል ጦርነት ተከፈተብን ከማለታቸው በፊት ይደግፉናል ወዳሏቸው ሰዎች ሪፖርት አደረጉ። ባለፉት ሳምንታት ትህነግ ወረራ ሲፈፅምብን ምንም ያላሉት የአሜሪካ ሰዎች፣ ትናንት ጀምሮ ትህነግ ሪፖርት ባደረገላቸው መሰረት መጀመርያ እነሱ ለይምሰል ጦርነት ይቁም ወዘተ አሉ። ከእነ አሜሪካ ቀጥለው እነ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጠዋት ተወረርን አሉ። ተመጋጋቢ ነው። የአሜሪካ ኤምባሲ የለጠፈውና ጌታቸው ረዳ የለጠፈው ልዩነታቸው የደቂቃ ነው። እነ ጌታቸው መጀመርያ አሜሪካኖቹ ቢለጥፉት ይሻላል ብለው፣ የአሜሪካኖቹን ተቀጥለው ነው ተወረርን የሚሉት።

አሜሪካ የኢትዮጵያውያንን ድጋፏን እንዲህ አፈር ድሜ አብልታ ለአንድ ጎሬ ውስጥ ለመደበቅ የሚዘጋጅን አሸባሪ የምትደግፈው ምን እያሰበች ነው? እንዴት እያሰበች ነው? ፖለቲካ ይወቅ አይወቅ በዚህ ወቅት አሜሪካ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ አሉታዊ አስተዋፅኦ እያደረገች ነው ብሎ የሚያስበው ሰው ብዙ ነው። አሜሪካ ግን ምን ነክቷት ነው?
20.6K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 23:07:33 ድራማ የማይሰለቸው ትህነግ ኬሚካል የጦር መሳርያ ተጠቅመው አጠቁኝ የሚል ድራማ እየሰራ እንደሆነ ታውቋል። በጦርነት ያስፈጃቸውን ወጣቶች አስከሬን ወስዶ ሊለበልብ ይሆናል። አሊያም ሌላ አማራጭ ይጠቀማል።

መሬት ላይ ያለውም የዲፕሎማሲውም ሲከብደው ድራማውንም የጦርነቱ አካል ማድረጉ የተለመደ ነው።

ለዚህ ጦርነት ከአደንዛዥ እፅ ጀምሮ ያልተጠቀመው ነገር የለም። ወጣቶቹ እንዲደፍሩለት አንገታቸው ላይም ከሱዳን የመጣ መተት ነው ብሎ ያስርላቸው ነበር። አሁን ደግሞ ሌላ ስልት ቀየሰ ማለት ነው።

ሲጨንቀው ገና በመብረቅ አስመቱኝ ይላል።
9.4K viewsedited  20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:08:30
16.8K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:08:22 ወልዲያ፣ ሌላኛዋ ማርሽ ቀያሪ!

ትህነግ ባለፈው አመት የተለያዩ ቦታዎች ተመትቶ ተዳክሞ ነበር። በአፋር ተመትቷል። ደባርቅ ላይ ተመትቷል። ጋይንት ላይ ተመትቷል። ደብረሲና ላይ ተመትቷል። ጋሸና ላይ ተመትቷል። ወልዲያ ሌላኛዋ ማርሽ ቀያሪ ነች።

ትህነግ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ አግተልትሎ እንደመጣ ነው መጀመርያ ቆቦ፣ ከዛም እስከ ወልዲያ ባለው መስመር በርካታ ኃይሉን ያጣው። ህወሃት ወልዲያን እይዛለሁ እንዳለበት ሁሉ ደብረታቦርና ደባርቅን ለማያዝ ጥሯል። ካራ ምሽግን ከዛም ደብረብርሃንን ለመያዝ ጥሯል። በእነዚህ ሁኔታዎች ያላደረገው ሙከራ አልነበረም። በአንዱ ሲመታ በሌላው ይሸሻል። በአንደኛው ተመለሰ ሲባል በሌላው ይመጣል። የሰሞኑ ወልዲያን ለመያዝ ያደረገው ትንቅንቅ ደብረታቦርን፣ ደባርቅንና ደብረብርሃንን ለመያዝ መጥቶ ተቀጥቅጦ ከተመለሰበት ጋር ተመሳሳይ ነው።


እንዲያውም የወልዲያው ረዥም ጊዜ አግኝቶ የሰለጠነ ነው። በጥምር ኃይሉና በደጀኑ ሕዝባችን መስዋዕትነት አላማው ተጨናግፏል። ይህ ግን በቂ አይደለም። በተደራጀ መልኩ ከተመታ ወደ ራያና ወልዲያ መስመር የመጣው ኀይል መመታቱ አሸባሪውን ቅስሙን ይሰብረዋል። ወልዲያን አላስነካም ያሉ ጀግኖቻችንን አግዘን ይህን አሸባሪ በሚገባ መቅጣት ከቻልን ኩራታችን ወልዲያ ሌላኛዋ የትግሉ ማርሽ ቀያሪ ትሆናለች። ሸዋ፣ ጋይንት፣ ጋሸና እና ወቅን ላይ የተመታው ትህነግ መግቢያ እንዳጣው ሁሉ አሁን ተረባርበን ወደ ወልዲያ አሰፍስፎ መጥቶ የነበረውን ማስቀረት ከቻልን የትህነግ ወሽመጥ ይቆረጣል።

መልካም አጋጣሚው ደግሞ የዋግሹም ልጆች ትህነግ የከፈተብንን ወረራ በሚገባ እየመከቱ፣ መልሶ ማጥቃት እያደረጉ በመሆኑ ወደ ራያና ወልዲያ የሄደው ኃይል ትንፋሽ እንዲያጥረው ይሆናል።
16.9K viewsedited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:54:42
16.7K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ