Get Mystery Box with random crypto!

Getachew shiferaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ getachewshiferaw — Getachew shiferaw
የሰርጥ አድራሻ: @getachewshiferaw
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.30K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 135

2022-07-24 16:10:21 የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ የክልሉን ልዩ ኀይል አበረታቱ።

በባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ከክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ጋር በመኾን፤ በአፍዴር ዞን ቆህሌ ወረዳ በሁልሁል ንዑስ ቀበሌ ላይ ሰርጎ በገባው አሸባሪው አልሸባብ ቡድን ላይ በተደረገው ኦፕሬሽን ድል ያደረገውን የክልሉ ልዩ ኃይል አበረታተዋል።

ርእሰ መስተደዳድሩ በኦፕሬሽኑ ድል አድርጎ ለተመለሰው ሰራዊት ወደ ሀገሪቱ ድንበር ሽኝት አደርገዋል ።

በሽንኝት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሙበሽር ድባድ ራጌ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል አመራሮችና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራር አካላት ተገኝተዋል።
6.8K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 21:25:34
1.1K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 21:25:22 ሌሎችም ከሙስጦፌ ይማሩ!


አሸባሪው አልሻባብ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ጥቃት አድርሷል። ይሁንና የሶማሊ ክልል መንግስት ፈጣን እርምጃ ወስዶ አሸባሪውን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ላይ ይገኛል። አሸባሪ ላይ እንዲህ ያለ እርምጃ ነው የሚወሰደው። የሶማሊ ልዩ ኃይልና የክልሉ ልዩ ኃይል በራሱ አቅም የወሰደው እርምጃ የሚደነቅ ነው። ኦሮሚያ ውስጥ ንፁሃንን የሚጨፈጭፍ ኃይል ላይ በአጭር ቀናት እንዲህ ያለ እርምጃ ሲወሰድ አይስተዋልም። የእነ ሙስጦፌ እርምጃ ለሌሎች አርዓያ ሊሆን ይገባል።
1.1K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:10:32
5.9K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:10:18 በጀት የሌለው ወልቃይት ጠገዴ እየሰራው ያለ ልማት!


በጀት የተሰጠው ካድሬ በጀቱን እንክት አድርጎ እየበላው ከተሞች እንደ ሀይቅ ውሃ ያጥለቀለቃቸው ሆነዋል። ወልቃይት ጠገዴ ደግሞ በጀት ሳይመደብለትም ከሕዝብ ገንዘብ አሰባስቦም ልማት ይሰራል።


ይህን የወልቃይት ልማት ለማገዝ የምትፈልጉ የኮሚቴው የባንክ ቁጥር 1000 483 972 001 ነው።
5.9K viewsedited  17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 20:26:19 የትግሬ ወራሪ ወልቃይት ጠገዴ ላይ የፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ ምስክር ናቸው። ከስር ያለውን ቪዲዮ ተመልከቱት!



15.4K viewsedited  17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 18:40:00 ከአማራ ክልል ውጭ ይህን ጥያቄ ማን ሊያቀርብ ይችላል?


የትሕነግ ቃል አቀባይ ሰሞኑን በሰጠው ቃለመጠይቅ ስለወልቃይት ሴቲት ሁመራ የአማራ ክልል መንግስት ምን ያገባዋል ሲል ተደምጧል። ይህን የተናገረው ካለማወቅ ሳይሆን እውነታ ለመካድ ከመፈለግ እንጅ። እውነታው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሴቲት ሁመራ፣ ጠጋዴ፣ ራያ አለማጣ፣ ራያ ባላ፣ ራያ ወፍላ፣ አለማጣ፣ ከፊል አበርገሌ ወደ ትግራይ ክልል (በወቅቱ ክልል 1) የተካለሉት በሃይል ከመሆኑም በላይ የሽሽግግር መንግስቱን አዋጅ 7/1984 እንዲሁም የኢፌዲሪ ሕገመንግስት ስለክልሎች አወቃቀር አስመልክቶ አንቀጽ 46 (2) የተደነገገውን መርህ በጣሰ መንገድ በመሆኑ ነው።


ትህነግ ሕገወጥ ይዞታውን ለመጽናት ብዙዎች ገሏል፤ የዘር ማጽዳት ፈጽሟል፣ የሕዝብ ስብጥር ለመቀየር (demography reengineering) የሰፈራ ፕሮግራም አካሄዷል። የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 46 (2) በግልጽ እንዳስቀመጠው ‘ክልሎች የሚዋቀሩት ‘በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት' ነው።


ሆኖም ግን እነዚህ አካባቢዎች ወደ ትግራይ የተካለሉትበት መንገድ (ሕገመንግስቱ ከመጽደቁ በፊት በሃይል መሆኑ የማይካድ ቢሆንም) በአንቀጽ 46 (2) የተቀመጠውን ሕገመንግስታዊ መስፈርት በጣሰ መንገድ ነው። ይህ ሕገመንግስታዊ መስፈርት ባይጣስ ኖሮ እነዚህ አካባቢዎች በአማራ ክልል ይካለሉ ነበር። በአጭሩ እነዚህ አካባቢዎች ወደ ትግራይ ተካለው የነበሩበት መንገድ የሕገመንግስቱን አንቀጽ 46 (2) የጣሰ ነው (የሕገመንግስቱ አንቀጽ 46 የሽግግር መንግስቱን በአዋጅ 7/ 84 መርህ እንዳለ ነው ያስቀመጠው))።

እናም የአማራ ክልል መንግስት እያለ ያለው እነዚህ አካባቢዎች በአማራ ክልል መካለለ ሲገባቸው በትግራይ ክልል መካለላቸው ኢሕገመንግስታዊ ስለሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እነዚህ አካባቢዎች ወደ አማራ ክልል እንዲካለሉ በማድረግ ትህነግ በወቅቱ የነበረውን የሃይል የበላይነት ተጠቅሞ የፈጸመውን የሕገመንግስት ጥሰት ሊያርም ይገባል የሚል ነው። ታዲያ ይህን ጥያቄ ከአማራ ክልል መንግስት ውጭ ማን ሊያቀርብ ይችላል? ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ውጭ ይህ ጥያቄ ለማን ሊቀርብ ይችላል (ለነገሩ ትህነግ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅና አልሰጥም ብሏል)።

(ዶ/ር ዮናስ ተስፋ)
16.4K viewsedited  15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 14:29:06
7.5K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 14:29:02 ከሱዳን ወደ ትግራይ ሊላክ የነበረ ወታደራዊ መገናኛ ወልቃይት ጠገዴ ላይ ተይዟል።




በቃብትያ ሁመራ ባህከር ቀበሌ ዙሪያ ከሱዳን ወደ ጠላት ሊደርስ የነበረው ስድስት ወታደራዊ የሞተሮላ ሞባይሎችና መሰል ቁሳቁሶች በፀጥታ አካላት መያዙን የዞኑ የሰላምና ደህንነት ምክትል ሃላፊ አቶ ለምለሙ ባየህ ገልፀዋል። መረጃው ከዞኑ ብልፅግና ገፅ ላይ የተወሰደ ነው።
7.5K viewsedited  11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 22:57:19
3.6K views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ