Get Mystery Box with random crypto!

አላማጣ አዳሩን ንፁሃንን ሲገድል፣ በርካቶችን ሲያፈናቅል ያደረው ኃይል የደቡብ አፍሪካው ስምምነት | Getachew shiferaw

አላማጣ አዳሩን ንፁሃንን ሲገድል፣ በርካቶችን ሲያፈናቅል ያደረው ኃይል የደቡብ አፍሪካው ስምምነት በተፈረመ በወር ውስጥ ትጥቅ መፍታት የነበረበት ነው። አብይ አህመድ ትጥቅ እንዳይፈታ አደረገው!

ተፈናቃይ ስለመመለስ ኮሚቴ አዋቅሮ ያለ ፀጥታ ኃይል፣ ያለ ትህነግ መዋቅር ይመለሳል ብሎ መግለጫ በሰጠ በሳምንቱ የትህነግን ታጣቂ ንፁሃንን እየገደለ እንዲገባ ማገዝ ብቻ ሳይሆን መከላከያ የትህነግ ወረራ የተከላከሉትን አማራዎች ገደለ።

የትህነግ ሰዎች በይፋ በአብይ አህመድ ድጋፍ ነው የገባነው ብለዋል። የትህነግ ታጣቂ ባለፉት ቀናት ጦርነት ከፍቶ ንፁሃንን ሲገድል ነው የሰነበተው። በአጭሩ አብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ በአማራ ላይ ይህ ወረራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ የሰጡ ናቸው።

ንፁሃን የተገደሉት፣ የተፈናቀሉት፣ የተዘረፉት በአብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ ትዕዛዝ፣ በብልፅግና እና ትህነግ/ህወሓት የጓዳ ውል ነው።

በተረፈ ትህነግ ወዳጅ ይሆናል ብላችሁ የምታስቡ ካላችሁ እርማችሁን አውጡ። ትህነግ ከብልፅግና ጋር ነው የሚሰራው። በጋራ ነው የወረሩን። አማራን ለመውረር ሲመክሩ ከርመው ንፁሃንን እያፈናቀሉ፣ እየገደሉ ነው። ነገ በጋራ ፋኖ ላይም ቢሆን መዝመታቸው የማይቀር ነው!