Get Mystery Box with random crypto!

የሰላም ስምምነት የተፈራረመውም፣ ሰላም አስፍነናል ብሎ ድግስ የከረመውም 'የፌደራል' ብልፅግና ነ | Getachew shiferaw

የሰላም ስምምነት የተፈራረመውም፣ ሰላም አስፍነናል ብሎ ድግስ የከረመውም "የፌደራል" ብልፅግና ነው። ጦርነት ሲከፈት መጀመሪያ መግለጫ መስጠት ያለበት እሱ ነው። ለድግሱ ከፊት ከርሞ፣ ለጓዳ ስምምነት ሲባል ናዝሬት ጠርቶ አስተናግዶ አሁን አማራ ክልል የጎን መግለጫ አሰጥቶ ዝም ሊል አይችልም።

የአማራን ግዛቶች አሳልፎ ለመስጠት "የኢትዮጵያ መሬቶች ናቸው። ፌደራል ያስተዳድራቸዋል" ይላል። ወረራ ሲፈፀም "ራሳችሁ መግለጫ አውጡ" ብሎ ይሸሻል። እውነታው አላማቸው አማራው ማስወጋት ስለሆነ ነው! ስምምነቱ ሲጣስ መግለጫ መስጠት ያለበት የፌደራሉ አገዛዝ ነው! ስትጨባበጥ ከርመህ፣ ትጥቅ እንዳይፈታ አድርገህ አሁን አማራን ሲወጋ ክልሉ መግለጫ ያውጣ ልትል አትችልም።

ሰላም እየፈጠርን ነው ብለህ ለዓለም እንዳወራኸው ሁሉ፣ ሲጣስም ለዓለም መንገር ያለብህ ራስህ ነህ። የሰላም ጊዜ ከፊት፣ ሲጣስ በጎን መግለጫ አይሆንም።