Get Mystery Box with random crypto!

'ፎርማት' ተደርጎ ተከራዬ! እኔ አይደለሁም ያልኩት። አለቃው ነው። እንደ አመታዊ የፋይናንስ ሪፖ | Getachew shiferaw

"ፎርማት" ተደርጎ ተከራዬ!

እኔ አይደለሁም ያልኩት። አለቃው ነው። እንደ አመታዊ የፋይናንስ ሪፖርት ቁጠሩት። ኤርሚያስ ለገሰ መከራየቱን አለቃው ቴድሮስ ፀጋዬ በቀጥታ ስርጭት ተናግሯል። እነ ቴድሮስም ከሌላ ቀምተው ነበር የተከራዩት። አሁን ባለጊዜ ጨምሮ ወሰደው።

ትህነግ ኤርሚያስን በቴድሮስ በኩል ነበር የሚያዘው። አሁን አለቃው በብስጭት "ፎርማት ተደርጎ ተከራይቷል" ብሏል። ያው እነ ቴድሮስ (አንዱ የትህነግ ክንፍ) ኪራዩን መክፈል ስላልቻሉ ሌላ ተከራየው። የፖለቲካ ገበያው ሲሞቅ ዋጋ አስወደደ።

በእርግጥ ቴድሮስ ይህን ያለው በድሮው ዕዝ ስለማይሰራለት እንጅ ኤርሚያስ በሌሎች ቡድኖች በኩል ለትህነግ እየሰራ ነው። ደሞዝ ጨምሩኝ ብሎ ካልሆነ ከዛ ሰፈር ያለው የረዥም ጊዜ ውል ነው። ግን ፖለቲካው ተለዋዋጭ ስለሆኑ ሁለት ቦታ ተቀጥሯል። ፖለቲካው ሲገለባበጥም ቋሚ ገቢ ይኖረዋል። እየተገለባበጠ መስራት ነው።

ከወራት በፊት እንደፃፍኩት ኤርሚያስ ሬድዮ ነው። ባትሪ ያለው እስከመጨረሻው ከፍቶ ያስጮኸዋል። እስካሁን ይህን ራዲዮ ከፋች የነበረው ቴድሮስ አሁን በሌላ ሰው እጅ ነው ብሏል። የማስታወቂያ ከሰጡት በመሃል በመሃል ይዘፍንላቸዋል። የተሻለ የሚከፍለው ከሆነ ልዩ ዞንም፣ ልዩ ወረዳም የፈለገ ይከራየዋል። የሀሰተኛ ፖስተሮችም ቢሆን ካገኙት ማሪያምን እየሰደበ ፕሮግራም ከመስራት ወደኋላ አይልም።

ኤርሚያስ በቀጥታ ስርጭት ተሸጠ ተለወጠ ሲባል ደፍሮ የድሮ አለቃውን አይናገርም። ምክንያቱም በርካታ መረጃ ተይዞበታል።