Get Mystery Box with random crypto!

ማጭበርበሪያ! ደብረፅዮን የሚመራው ትህነግ/ህወሓት የወልቃይት፣ ራያ፣ ጠለምትና አበርገሌ ወረዳና | Getachew shiferaw

ማጭበርበሪያ!

ደብረፅዮን የሚመራው ትህነግ/ህወሓት የወልቃይት፣ ራያ፣ ጠለምትና አበርገሌ ወረዳና ቀበሌ አስተዳደሮችን መልምሎ ትግራይ ውስጥ ፅ/ቤት ከፍቶላቸዋል። ከስር እንደሚታየው በአማራ ግዛቶች ስም የፌስቡክ ገፅ ከፍተው የሚያስተዳድራቸው ትህነግ/ህወሓት እንደሆነ አድርገው፣ ሽሬና መቀሌ የወረዳና የቀበሌ እንዲሁም ከተማ አደረጃጀቶች እንደሆኑ አድርጎ ባነር አሳትሞ እየሰበሰበ፣ በአካባቢዎቹ ስም ህገወጥ ማህተም ቀርፆ ደብዳቤ እየፃፈ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ደግሞ "ተፈናቃዮች ይመለሱ" ይላል።

ሰሞኑን በነበረው ስብሰባ ሞንጆሪኖና የትህነግ ጀኔራሎች ትህነግ/ህወሓት ያለምንም ልዩነት የተስማማበትን እስከነ መዋቅሩ መመለስ አቋም እንዲያራምዱ ተደርጎ፣ እነ ደብረፅዮን ከዚህ ሀሳብ የሚለዩ መስለው ቀርበዋል። ጌታቸው ረዳም ሆነ ደብረፅዮን በዚህ ጉዳይ ከጀኔራሎቹ ጋር ልዩነት የላቸውም። የቤት ስራ ነው የተከፋፈሉት። በውይይት የተወሰኑት እንዲሳተፉ ቀሪው የተለየ አቋም የያዘ መስሎ በተግባር እንዲሰራ ነው። በዚህ ማጭበርበሪያ መሰረት ከብልፅግና ጋር እየተሰበሰቡ ነው። ብልፅግና የአማራን ርስቶች በዚህ ሂደት አሳልፎ ለመስጠት እየሰራ ነው።