Get Mystery Box with random crypto!

የተፈለገው ይሄ ነው! ትህነግ ወደራያና ወልቃይት ተፈናቃይን አልመልስም ብሏል። ከእነ ሙሉ መዋቅሬ | Getachew shiferaw

የተፈለገው ይሄ ነው!

ትህነግ ወደራያና ወልቃይት ተፈናቃይን አልመልስም ብሏል። ከእነ ሙሉ መዋቅሬ ነው የምመለሰው ብሎ እየሰራ ነው። ብልፅግና ሰሞኑን ያለ በጀት ከህዝብ ገንዘብ ሰብስበው ልማት የሚሰሩትን አስተዳደሮች አፈርሳለሁ ያለ ሲሆን ትህነግ እስከ ቀበሌ ድረስ አመራር፣ የፓርቲ መዋቅር፣ ፀጥታ አደራጅቶ እየጠበቀ ነው። ትግራይ ውስጥ ቁጭ ብለው የራያና ወልቃይት እስከ ቀበሌ ድረስ መዋቅር ተብለው ተዘጋጅተው መግለጫ እየሰጡ፣ መታወቂያ እያደሉ፣ በማህተም ደብዳቤ እየፃፉ ይገኛሉ። ብልፅግና ይህን ያውቃል።

የተፈለገው የህዝብ አስተዳደርን አፍርሶ ለትህነግ ማስረከብ ነው። የመጀመሪያው ትህነግ የሁመራ ፅ/ቤት ብሎ ያደራጀው መዋቅር የሚጠቀምበት ገፅ ማስረጃ ሲሆን ሁለተኛው የአላማጣ ከንቲባ ብሎ ማህተም አስቀርፆ ደብዳቤ የሚፅፍበት ነው። ሁሉም ወረዳዎች፣ ቀበሌዎች፣ ከተሞች መሰል መዋቅር አዘጋጅቶ ህጋዊ አስመስሎ እየሰራው ነው።

"ተፈናቃይ ይመለስ" ማለቱን ተከትሎ ደግሞ "ኬር ኢትዮጵያ" በሚባል ድርጅት ድጋፍ በርካታ መታወቂያ ተዘጋጅቷል። ራያና ወልቃይትን የማያውቀውን ጨምሮ በርካታ ህዝብ መታወቂያ ተሰጥቶት እናሰፍራለን እያሉ ነው።

አንድም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ግዴታውን ሳይወጣ፣ በስምምነቱ መሰረት በአማራ ክልል እንዲቆዩ የተደነገገላቸውን አካባቢዎች አሳልፎ ለመስጠት በተሰራው ደባ የልብ ልብ የተሰማው ትህነግ ለአካባቢዎቹ በህገወጥ ማህተምና ደረሰኝ የሚጠቀም ሙሉ መዋቅር አዘጋጅቷል። ብልፅግና ይህን ያውቃል። ወንጀል ግን አይመስለውም። የህዝብ አስተዳደር የሚያፈርሱት ግን ለዚህ ህገወጥ ቡድን አሳልፎ ለመስጠት ነው!