Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-11-24 16:19:10 በባንኮች ላይ ዘረፋ የፈፀሙ የጥበቃ ሰራተኞችና ግብራበሮቻቸው ተቀጡ
#FastMereja
በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እና በወጋገን ባንክ ላይ ዘረፋ የፈፀሙ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች እና ሰባት ግብራበሮቻቸው በእስራት ተቀጡ፡፡

አለሙ አሰፋ የተባለው ተከሳሽ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጃክሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በከልቻ ቅርንጨፍ ውስጥ በጥበቃ ስራ ተቀጥሮ እያገለገለ ነበር፡፡

ተከሳሹ መስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም የምሽት ተረኛ የሆነው የስራ ባልደረባውን "ዛሬ እኔ ልሸፍንልህ አንተ ወደ ቤት ሂድ" ብሎ እንዲሄድ ካደረገ በኋላ ይርጋለም አድማሱ ከተባለው ግብረ አበሩ ጋር በመሆን በፌሮ ብረት ካዝና በመስበር 2ሺህ 414 የአሜሪካ ዶላር እና ከ2 ሚሊዮን 280 ሺህ በላይ ብር ዘርፈው በበመውሰድ ተሰውረው ቆይተዋል፡፡

በሌላ በኩል ገበየሁ ምስጋና የተባለ የወጋገን ባንክ የረር ቅርንጨፍ የጥበቃ ሠራተኛ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ውስጥ በተፈፀመው ወንጀል ተሳትፎ ከነበረው ይርጋለም አድማሱ እና ከሌሎች አራት ግለሰቦች ጋር በመተባበር ሃምሌ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ የዘረፋ ወንጀል ፈፅመዋል፡፡

ተከሳሾቹ በዕለቱ በባንኩ የጥበቃ ስራ ላይ የነበረው ታሪኩ መንገሻ የተባለውን ግለሰብ እጅና እግሩን በማሰር የውንብድና ወንጀል ከፈፀሙበት በኋላ 419 ሺህ ብር ዘርፈው ወስደዋል፡፡

ፖሊስ የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት ከደረሰው በኋላ መረጃዎችን በማሰባሰብ እና ያልተቋረጠ ክትትል በማድረግ በተለያየ ደረጃ ተጠያቂነት ያለባቸውን በአጠቃላይ ዘጠኝ ግለሰቦችን ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ጭምር በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል፡፡

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ቦሌ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ይርጋለም አድማሱ በሁለቱም ባንኮች ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች በመሳተፉ በ14 ዓመት ከ 3 ወር እስራት እንዲቀጣ ሲወስን ገበየሁ ምስጋናው በ 8 ዓመት፣ እዮብ ተመስገን፣ አለሙ አሰፋ፣ እና ሀይለማርያም መለሠ እያንዳንዳቸው በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ እንዲሁም ተሾመ ደምለው በ 4 ዓመት ፣ አቤል ንጉሴ በአንድ ዓመት እስራት እና በ1 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ የወሰነ ሲሆን በመሸሸግ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸውና ለጊዜው ያልተያዙት ጥላሁን ወልዴ እና ጌታሁን ተፈራ የተባሉ ተከሳሾች በሌሉበት እያንዳንዳቸው በ 1 ዓመት ከ6 ወር እስራት እና በ2ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ።

ሁለቱ የባንኮቹ የጥበቃ ሰራተኞች ሲቀጠሩ በቂ ዋስትና እና ሰነድ ያልነበራቸው መሆኑ የምርመራ እና የክትትል ስራውን አስቸጋሪ አድርጎት እንደቆየ የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት የጥበቃ ሠረተኞችን ሲቀጥሩ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

@fastmereja
12.7K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-19 07:35:31 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ
#FastMereja
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል። የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ በተመለከት ከደንበኞቻችን ባገኘው ግብረ መልስ መሠረት በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ድጋሚ የክፍያ ማሻሻያዎች አድርጓል።

በድጋሚ ማሻሻያ የተደረገባቸው አገልግሎቶች እና የተሻሻለው ክፍያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡

1. በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ነው፤
2. በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ነፃ ናቸው፤
3. በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 10,000 - ብር 5
• ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 - ብር 10
• ከብር 100,001 በላይ - ብር 10 ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ)

4. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሌላ ደንበኛ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 50,000 - ነፃ
• ከብር 50,001 እስከ ብር 100,000 - ብር 5
• ከብር 100,001 እስከ ብር 200,000 - ብር 10
• ከብር 200,001 እስከ ብር 300,000 - ብር 15
• ከብር 300,001 በላይ - ብር 20

5. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ (RTGS) ብር 50 የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤
6. ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤
7. ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤
8. በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል፡

• ከብር 50 በታች - ነፃ
• ከብር 51 እስከ ብር 500 - ብር 6.45
• ከብር 501 እስከ ብር 2,000 - ብር 7.60
• ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 - ብር 8.18
• ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 - ብር 9.33
• ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 - ብር 10.48
• ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 - ብር 11.63
• ከብር 6,001 በላይ - የሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ

@fastmereja
13.1K views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-17 14:50:27 “በትራፊክ አደጋ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ዜጋ እስከ 2000 ብር ድረስ በነፃ የመታከም መብት አለው” የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት

በአዋጅ ቁጥር 70/99 2005 መሰረት ኢንሹራንስ ባለውም ሆነ በሌለው ተሽከርካሪ የአካል ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ በግልም ሆነ በመንግሥት የጤና ተቋም እስከ 2000 ብር ድረስ ነፃና አስቸኳይ ህክምና የማግኘት መብት እንዳለው የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ድህረ ትራፊክ አደጋ ዴስክ ኃላፊ ኢክራም የሱፍ ለአራዳ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በአዋጁ መሰረት ኢንሹራንስ ባላቸው ተሽከርካሪዎች ጉዳት ከደረሰ ኢንሹራንስ የገቡበት ተቋም እስከ 40 ሺህ ብር ድረስ ለአካል ጉዳትና ሞት ለደረሰባቸው ዜጎች ካሳ የመክፈል ግዴታ አለበት።

ተሽከርካሪው የ3ኛ ወገን መድህን ሽፋን ከሌለውና አሽከርካሪው ገጭቶ ካመለጠ አደጋ የደረሰበትን ወይም ህይወቱ ያለፈን ሰው የመድን ሽፋን የመስጠት ኃላፊነት የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ነው።

አሁን ያለው የመድን ሽፋን በቂ ባለመሆኑ የነፃ ህክምና እና የካሳ ክፍያ አዋጁ ተከልሶ ምክርቤቱ እስኪያፀድቀው እየተጠበቀ እንደሆነ አራዳ ሰምቷል።

Via: አራዳ ኤፍ ኤም

@fastmereja
12.8K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-01 17:19:06 በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ሽንት መሽናት 200 ብር መቅጣት ሊጀመር ነው ተባለ!
#FastMereja
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቅርቡ ያወጣው ደንብ ቁጥር 150/2015 ምን ይከለክላል? ሲል ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ይህን ዘገባ ይዞ ወጥቷል፣ ሶፍት፥ወረቀት፥ የአቶብስ ትኬት ፥ የታሸገ ውሃ መያዣ ፕላስቲክ ጥሎ የተገኘ እንደሆነ 200 ብር መቀጮ ይከፍላል። የጣለውን እንዲያጸዳ ይገደዳል።

በመዲናዋ መንገዶች ላይ ሽንት ሲሸና የተገኘ ደግሞ 200 ብር እንዲከፍል ይደረጋል። ሰርግና መሰል ህዝባዊ ፕሮግራሞች አዘጋጅቶ ካጠናቀቀ በሗላ ስፍራውን በተገኒው ሁኔታ ያላጸዳ 5ሺ ብር ይቀጣል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እስካሁን ደንቡን ማስተዋወቅ እና ማስተማር ላይ ቆይቻለው። አሁን ግን ወደ እርምጃ መሄዴ ነው ብሏል።

@fastmereja
14.6K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 18:57:06 ኢትዮጵያ ወደ ህዋ የላከቻቸው ሳተላይቶች ስራ አቆሙ
#FastMereja
ኢትዮጵያ የተለያዩ ሳይንሳዊ ስራዎችን ለመከወን ያግዟታል ተብለው ወደ ህዋ የመጠቁ ሁለቱ ሳተላይቶች ስራ አቁመዋል ተባለ። የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚወገዱበት ጊዜ ስለደረሰ ሌሎች ሳተላይቶች ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ ለማስወገድ እየተሰራ መሆኑ ተገልፇል።

አዲስ ሳታላይት አልምቶ ለማምጠቅም እየተሰራ መሆኑን የኢንኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ተናግሯል። ከዚህ ቀደም ወደ ሳተላይት የመጠቁት ምን ፋይዳ አስገኙ የሚለው እንዳልተገለፀ ነው ሸገር ሬዲዮ የዘገበው።

@fastmereja
13.7K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-18 14:30:44 ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) ማረሚያ ቤት እንዲወርድ ታዘዘ
#FastMereja
ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ባልቻ በቅጽል ሥሙ (ልጅ ያሬድ) በቀረበበት ተደራራቢ ክስ ማረሚያ ቤት እንዲወርድ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ የፀረ-ሽብርና የሕገ-መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ተላልፏል።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሪክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ባልቻ በቅጽል ሥሙ( ልጅ ያሬድ) በተባለ ግለሰብ ላይ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቧል።

በተለይም በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም በማጉደፍ፣ ጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ነጥቦች ይገኙበታል።

ክሱ ከደረሰው በኋላ ተከሳሹ ያቀረበውን የዋስትና ጥያቄው ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል አዟል።

ይሁንና ተከሳሹ ችሎት በቀረበበት ጊዜ ዐቃቤ ሕግ ለቤተክርስቲያን ክብር፣ ለማህበረሰቡ ስነልቦና፣ እሴትና ባህል ሲባል በክሱ ላይ የቀረቡ ዝርዝር ነጥቦች እንዳይታተም በሚዲያ እንዳይቀርብ እንዲሁም ችሎቱ በዝግ እንዲሆን አቤቱታ አቅርቧል።

አቤቱታውን የመረመረው ፍርድ ቤቱም የማህበረሰቡን ክብርና ስነልቦናን ከግምት ውስጥ በማስገባት የክሱ ዝርዝር ጉዳይ በሚዲያ እንዳይሰራጭ ችሎቱ በዝግ እንዲሆን ብይን መስጠቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ልጅ ያሬድ በቅርቡ ለማህበራዊ ትስስር ገፅ ተከታዮቹ ባጋራው የቲክቶክ ቪዲዮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክብር የሚነካ እና የእምነቱ ተከታዮችን ያስቆጣ ተግባር መፈጸሙን ተከትሎ፤ በርካቶች "በሕግ መጠየቅ አለበት" የሚል ሃሳባቸውን ሲያንፀባርቁ እንደነበር ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ በቲክቶክ ቪዲዮ ባጋራው ሕገ ወጥ ይዘት ያለው መልዕክት ሳቢያ፤ ነሃሴ 27/2015 በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወቃል ሲል አዲስ ማለዳ ነው ያስነበበው።

@fastmereja
15.0K views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-17 15:33:28 ሰው አግተው ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ የአዲስ አበባ የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሠረተ።

የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያለአግባብ በመገልገል ሰው አግተው ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ የአዲስ አበባ የፖሊስ አባላት ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ።

ክሱን ያቀረበባቸው የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ነው።

ክስ የተመሰረተባቸው አጠቃላይ አራት ሲሆኑ፥ ሶስት ተከሳሾች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት እንዲሁም አንድ ተከሳሽ በግል ስራ ይተዳደራል የተባለ ግለሰብ ነው።

ተከሳሾቹ 1ኛ ረ/ሳ ሰለሞን ባህሩ ከበደ፣ 2ኛ ም/ሳ ሲሳይ ተገኝ እንግዳው፣ 3ኛ ም/ሳ ተስፋዬ መኳንንት ላቀው እና 4ኛ በግል ስራ ይተዳደራል የተባለው ዮናታን ሳሙኤል ሙሉብርሃን ናቸው።

ተከሳሾቹ አንደኛ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1/ሀ እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 1/ሀ እንዲሁም ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ በሚል ነው።

በዚህም የክስ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው ተከሳሾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የክትትል እና ኦፕሬሽን ኦፊሰር የስራ መደብ ሲሰሩ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ በመስከረም 02 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 12፡30 ሲሆን፥ በኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ክልል ልዩ ቦታው ሆላንድ ኤምባሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሶ ተሽከርካሪ ይዞ ሲጓዝ የነበረውንና በስራ አጋጣሚ የሚያውቁትን ግለሰብን እንዲቆምላቸው እና ትብብር እንዲያደርግላቸው ማድረጋቸው በክሱ ተጠቅሷል።

በዚህ መልኩ ሌላ መኪናን ማለትም የግል ተበዳይ የሆነ ግለሰብ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-A36466 አ/አበባ መኪና ሲያሽከረክር የነበረ ግለሰብ ታርጋን ለይተው መያዛቸውንና ግለሰቡ በህግ ተፈላጊ እንደሆነ አድርገው በመግለጽ መኪናውን ተከታትሎ እንዲያስቆምላቸው መጠየቃቸው በክሱ ተዘርዝሯል።

ከዚህ በኋላ የግል ተበዳይ ተከታትለው ተሽከርካሪውን ካስቆሙት በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የግል ተበዳይ መኪና ውስጥ ያለፈቃድ በመግባት መኪናውን ወዳልታወቀ ቦታ እንዲያሸከረክር በማስገደድና ለወላጅ አባቱ ስልክ በማስደወል 1ኛ ተከሳሽ የተበዳይን አባት ለግዜው ባልተያዘ ግብረ አበራቸው ስም ወደ ተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 10 ሚሊዮን ብር ካላስገባ ልጁን እንደሚገድሉት በመግለጽ የማስፈራራት የወንጀል ተግባር መፈጸማቸው ተጠቅሷል በክሱ።

በተለይም ገንዘቡን እስከሚያገኙ ድረስ ተበዳዩን አግተው በማቆየት ከተበዳይ አባት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ በሞባይል ባንኪንግ ሲሰተም 100 ሺህ ብር እንዲገባ ማስደረጋቸውና ገንዘቡም መግባቱን ሲያረጋግጡ ተበዳዩን የለቀቁት በመሆኑ በክሱ ተገልጿል።

በተጨማሪም 1ኛ ተከሳሽ ያለህን ገንዘብ አምጣ በማለት ከግል ተበዳይ 6 ሺህ ብር ተቀብሎ ለ2ኛ ተከሳሽ መስጠቱን ተከትሎ ተከሳሾች በተደረገባቸው ክትትል ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ጊዜ ከ2ኛ ተከሳሽ ኪስ ውስጥ ከግል ተበዳይ የወሰደው 6 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ መገኘቱን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል።

3ኛ ተከሳሽን በሚመለከት የግል ተበዳይን ባስቆሙበት ጊዜ ከግል ተበዳይ ጋር በመኪና ውስጥ የነበሩ ሁለት ግለሰቦችን መኪናው ውስጥ በመግባት እንዳይንቀሳቀሱ አግቶ በማቆት በተበዳይ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ህገወጥ ድርጊት እንዳያስቆሙ የተከላከለ እና ለ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ሽፋን የሰጠ መሆኑ ተጠቅሶ በክሱ ላይ ተዘርዝሯል።

በአጠቃላይ ተከሳሾች በመላ ሃሳባቸው በወንጀል ድርጊቱ ሙሉ ተካፋይ በመሆን የተሰጣቸውን ሃላፊነት በግልጽ ተግባር ያለአግባብ በመገልገል 3 ግለሰቦችን በማገት 106 ሺህ ብር አስፈራርተው በመውሰድ ጉዳት ያደረሱ በመሆኑ በፈጸሙት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

በሁለተኛ ክስ ደግሞ በሁሉም ተከሳሾች ላይ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 1/ ሀ እና በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ፣ ለ እና ሐ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል ተብሎ ክስ ቀርቦባቸዋል።

በዚህም የክስ ዝርዝር ላይ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመገልገል የሚያገኙትን ገንዘብ ህገወጥ ምንጭ ለመደበቅ እና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ ከግል ተበዳይ አባት የወሰዱትን ገንዘብ ዮናታን ሳሙኤል በተባለ ግብረአበራቸው ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ እንዲያስገባ በመግለጽ በአካውንቱ በሞባይል ባንኪንግ 100 ሺህ ብር እንዲገባ ማድረጋቸው በክሱ ተጠቅሷል፡፡

4ኛ ተከሳሽ ደግሞ ገንዘቡ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ በስሙ ተከፍቶ ገቢ ከሆነለት ከ100 ሺህ ብር ውስጥ 40 ሺህ ብር ከባንክ በጥሬ 10 ሺህ ብር ደግሞ በኤቲኤም ወጪ በማድረግ 20 ሺህ ብሩን በስሙ በአዋሽ ባንክ ወደ ተከፈተ ሂሳብ ማስተላለፉና 30 ሺህ ብር ደግሞ በስሙ በህብረት ባንክ በተከፈተ ሂሳብ ካስተላለፈ በኋላ ሙሉውን ገንዘብ ወጪ አድርጎ የተረከበ መሆኑ መጠቀሱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በዛው ጊዜ ሙሉውን ገንዘብ በካሽ ወጪ በማድረግ ህገወጥ ተግባር የተገኘውን ገንዘብ የተረከበ በመሆኑ ባጠቃላይ በተከሳሾቹ ላይ ዐቃቤ ሕግ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

ተከሳሾቹ ሶስቱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን፥ የዋስትና ጥያቄ ላይ ክርክር ለማድረግና የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ከነገ በስቲያ ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል ሲል ፋና ነው የዘገበው።
13.3K views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 21:49:43 በሞተር ብስክሌት፣ በባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ነገ ይነሳል፡፡
#FastMereja
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በሞተር ብስክሌተኞች፣ በባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከነገ ማክሰኞ መስከረም 29/2016ዓ.ም ጀምሮ ያነሳ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳወቀ።

ሆኖም ፍቃዱ የሚመለከታቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው ሲሆኑ፤ የሞተር ሳይክሎችም በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ህጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ (GPS) ያስገጠሙትን ብቻ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።

ከትራንስፖርት ቢሮው ህጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ ገልፇል።

@fastmereja
14.6K views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 19:25:21 በትግራይ ክልል 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ

በትግራይ ክልል ከነገ ጀምሮ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በኤጀንሲው የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ፍስሃ እንደገለጹት፥ ተፈታኝ ተማሪዎቹ በመቐለ፣ በአክሱም፣ በአዲግራትና በራያ ዩኒቨርሲቲዎች ለአርባ አምስት ቀናት የማጠናከርያ ትምህርት ተሰጥቷቸዋል።

ከተፈታኞቹም 6 ሺህ 513 ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስና 3 ሺህ አንድ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። ከመካከላቸውም 3 ሺህ 941 ሴቶች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

ዘገባው የኢቢሲ ነው!!
@FastMereja
12.7K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 12:47:07 በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺህ ገደማ ተማሪዎች መካከል፤ ወደ ዩኒቨርስቲ የማለፊያ ነጥብ ያመጡት ተፈታኞች ብዛት 27,267 ተማሪዎች አሊያም 3.2 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቦታል።

@FastMereja
13.2K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ