Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-09-07 12:47:59 ከአርሰናል ደጋፊዎች ጋር ተወራርዶ 15 እንቁላል የዋጠው ኬንያዊ የዩናይትድ ደጋፊ ሆስፒታል ገባ

ኤልዶሬት በተባለችው የኬንያ ግዛት 15 የተቀቀለ እንቁላል የዋጠው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ መጨረሻ ሆስፒታል ሆኗል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብሎ የአርሰናል ደጋፊ ከሆኑ ጓደኞቹ ጋር ውርርድ የገባው ቶማስ ኪፑታኒ ኬምቦይ ዩናይትድ ከተሸነፈ 30 የተቀቀለ እንቁላል ለመብላት መወራረዱን የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ፅፈዋል።

ባለፈው እሑድ አርሰናል በኤሜሬትስ ስታድየም ማንቸስተር ዩናይትድ ሲያስተናግድ ነው ይህ የሆነው።

ዩናይትድ በጨዋታው 3-1 መረታቱን ተከትሎ አንድ ሙሉ ትሪ እንቁላል ለመዋጥ ቃል የገባው ኬምቦይ ከጨዋታው በኋላ ቃሉን መፈፀም ይጀምራል።

ማሕበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጩ ምስሎች ግለሰቡ ጓደኞቹ እያበረታቱት በየመሐሉ ውሃ እየጠጣ የተቀቀለ እንቁላል ሲውጥ ያሳያሉ።

ሲቲዝን የተሰኘው ሚድያ እንደዘገበው ኬምቦይ 15ኛው እንቁላል ላይ ሲደርስ ራሱን ስቶ ሲወድቅ ጓደኞቹ እየቀለደ መስሏቸው ሲሳሳቁ ነበር።

ግለሰቡ ራሱን ስቶ መውደቁን የተረዱት ጓደኞቹ ከወደቀበት አፋፍሰው ወደ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ።

የሲቲዝን ዘገባ እንደሚያሳየው ካፕኬኖ በተሰኘ ቅፅል ስሙ የሚታወቀው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ተመርምሮ የሆድ ድርቀት እንዳለበት ታውቋል።

ከሕመሙ እስኪያገግም ድረስ ሆስፒታል ቆይቶ ጤናው መለስ ሲል እንደወጣ የኬንያ መገናኛ ብዙኃን አስነብበዋል።

“መጀመሪያ በጣም ደስ ብሎኝ እንቁላሉን ስበላ ትዝ ይለኛል። ከዚያ ስነቃ ሆስፒታል ውስጥ ራሴን አገኘሁት። አሁን ጤናዬ ስለተመለሰ ደስተኛ ነኝ” ሲል ካፕኬንኮ ስታንዳርድ ለተሰኘው ጋዜጣ ተናግሯል።

እሑድ ዕለት በብዙዎች ዘንድ ሲጠበቅ የነበረው የአርሰናል እና የማንቸስተር ዩናይትድ ፍልሚያ በመድፈኞቹ የበላይነት ተጠናቋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በራሽፈርድ ጎል ጨዋታውን መምራት ቢችልም አርሰናል በፈጣን ምላሽ በኦዴጋርድ ጎል አቻ መሆን ችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ የገባው አሌሃንድሮ ጋርናቾ ቀያይ ሰይጣኖቹን መሪ የምታደርግ ኳስ ከመረብ ቢያገናኝም ቪኤአር ጎሉ ከጨዋታ ውጭ ነው ሲል ሽሮታል።

ከዚህ ክስተት በኋላ አርሰናል በዴክለን ራይስና በሄሱስ ጋብርኤል ጎሎች ዩናይትድን 3-1 መርታት ችሏል።

በሁለቱ የእንግሊዝ ክለቦች መካከል ያለው ፉክክር በተለይ በአህጉረ አፍሪካ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ነው።

ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው!

@fastmereja
14.3K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-01 18:08:26 ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ ለመጠየቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች
#FastMereja
ባለፉት ቀናት  በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በመግባት ከእምነቷ ውጭ የሆነ መዝሙር የዘመረች ወጣት  የፈጸመችው ተግባር ጥፋት መሆኑን አምና በፈጸመችው ጥፋት  በመጸጸት በቅድስት ቤተ ክርሰቲያን አውደ ምህረት ተገኝታ ይቅርታ መጠየቋን ተከትሎ ልጅ ያሬድ የተባለ ግለሰብ እንኳን የኃይማኖት ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ቀርቶ እምነት የለሽ በሚባሉት ሀገራት የማይደረግ የድፍረት ስድብና አጋንታዊ የሆነ ጸያፍ ቃላትን በመጠቀም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በማህበራዊ ድህረ ገጹ ላይ በተደጋጋሚ  ያስተላለፈውን መልዕክት ተመልክተነዋል።

በዚህ ድፍረት የተሞላበት  ድርጊትም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን አዝነዋል፣አልቅሰዋል፣ በድርጊቱ ክፉኛ በመበሳጨትም ከፍትህ አደባባይ ፍርድ  እንደሚጠብቁ  በተለያየ መልኩ እያሳወቁ ናቸው።

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን መስቀል ሁሌ መሸከም የየዕለት  ተግባሯ ቢሆንም ከሚሊዮን በላይ ተከታይ ያላትንና  ላለፉት ሁለት ሺህ ዘመናት ሀገርን በፍቅርና በስነምግባር ጥላ ሥር ሰብስባ ያኖረች ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ እየታወቀ  በእንዲህ አይነት በወረዳና ተሰምቶ በማያውቅ ድፍረት  ቤተክርስቲያንን በመስደብ ሕዝበክርስቲያኑን ለማሳዘን መሞከር እጅግ አደገኛ ተግባር ነው።

ቤተክርስቲያንም ይህን  ጸያፍ ተግባር የፈጸመና  የተሳደበን ግለሰብ በዝምታ ማለፍ  ስለማይገባት  ጉዳዩን በህግ መምርያ በኩል በመከታተል ተገቢውን ሁሉ  የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እየገለጸች በህግ መምሪያችንና በህግ ባለሙያዎቻችን አማካኝነት አስፈላጊውን ሁሉ እስክታደርግ  ድረስ ምዕመናን ከቅድስት ቤተክርስቲያን የተማሩትን ትዕግስትና ትህትናን መሰረት ባደረገ አግባብ  በፍጹም ክርስቲያናዊ ጨዋነት እንድትጠብቁና በጉዳዩ ዙሪያ ከጸጥታ ከአካላት ጋር በትብብርና በአንድነት  በመጠቆም እንድትተባሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

@fastmereja
16.8K views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-01 11:57:51 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለጸጥታ አመራሮች ሹመት ሰጠ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከነሐሴ 22/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሹመት የተሰጣቸው የጸጥታ አመራሮች

1. ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን ወልዴ የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

2. ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ ገ/መስቀል የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

3. ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ ገዳሙ የአብክመ ማረሚያ ቤቶች አገ/ኮሚሽን ኮሚሽነር

4. ዶ.ር እሸቱ የሱፍ አየለ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

5. ደጀኔ ልመንህ በዛብህ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

6. በሪሁን መንግሥቱ ከበደ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

7. ዳኛው በለጠ ጎኔ የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ

8. ገደቤ ኃይሉ በላይ የአብክመ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ

9. ኮሚሽነር ውበቱ አለነ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ

10.ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሰው ኃይል አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ

11. ም/ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሎጀስቲክስ ዘርፍ ኃላፊ ኾነው ተሹመዋል።

ዘገባው የአሚኮ ነው!

@FastMereja
13.3K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 20:16:06 በአማራ ክልል፤ የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው “በግለሰብ በተፈጸመባቸው ጥቃት” ተገደሉ

በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በተከፈተባቸው ተኩስ ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። ለወረዳዋ ፖሊስ አዛዦች ህልፈት ምክንያት የሆነውን ተኩስ ከፍቷል የተባለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ጥቃት የተፈጸመባቸው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 26፤ 2015 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ጋሻዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የፖሊስ አዛዦቹ ላይ ተኩስ የተከፈተባቸው፤ በዛሬው ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰጠ ያለውን “የስምንተኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና እየተጓዙ በነበረበት ወቅት” መሆኑን የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊው አስረድተዋል።

ሁለቱ የፖሊስ አዛዦች “ግልገሌ” የተባለች ቀበሌ ላይ ሲደርሱ “መንገድ ላይ ሲጠብቃቸው ነበር” በተባለ ግለሰብ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አቶ ጌታሁን ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት በጥይት የተመቱት የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ዘውዱ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሹፌራቸው “እግሩ ላይ ተመትቶ” ጉዳት እንደደረሰበት ኃላፊው አክለዋል።

ዘገባው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው!!

@fastmereja
3.5K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 19:05:45
ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና ውርጃን የሚያወግዝ ሰልፍ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ
#FastMereja
በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ 22 የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን የተወጣጡ ሰልፈኞች ከኃይማኖት እና ከባህል ያፈነገጡ ተግባራትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል። ግብረሰዶማዊነትን፣ ወርጃን፣ ነብስ ማጥፋትን፣ ምንዝርና እና ሱሰኝነትን እንቃወማለን የሚሉ መፈክሮች በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተንፀባርቋል።

ምስል ደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን

@fastmereja
4.6K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 18:23:52
ፈንድቃ እንዲቆይ ፍቃድ ተሰጠው
#FastMereja
ይፈርሳል የተባለው ፈንድቃ የባህል ቤት ዛሬ ከባለቤቱ አርቲስት መላኩ በላይ እንድገለፀው "የአዲስ አበባ ከንቲባ ድምጻችንን ሰምተው ፈንድቃን እንድናቆይ ፍቃድ እንደሰጡን ላበስራችሁ ፈልጋለሁ" ብሏል።

@fastmereja
4.6K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 18:04:53
12ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ የአሸናፊዎች እጣ ወጣ!

በ1ኛ እጣ 3 ሚሊየን ብር እና ሌሎችም እጣዎች እድለኞች ይፋ ሆነዋል ሎተሪውን ከቆረጡ በ605 ላይ የተላከልዎን የዕጣ ቁጥር ይመልከቱ

@fastmereja
4.3K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 17:58:53
ስኳርን በማቅለጥ እና ሌላ በዕድ ነገር በመጨመር ንፁህ ማር በማስመሰል ይሸጥ ይነበረ ግለሰብ በሕግ ቁጥጥር ዋለ።

በወልድያ ከተማ አስተዳደር በዕቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በ02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ትንፋዝ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር ስኳር ከማር ጋር በማቅለጥ ይሸጥ የነበረ ግለሰብ፤ በህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ትናንት ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር መዋሉን የክፍለ-ከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት የሥራ ባልደረባ የሆኑት ረዳት ኢንስፔክተር ጌታቸው ይፍሩ አስታቀዋል።

ግለሰቡ ቤተ ተከራይቶ አራት ሰዎችን ቀጥሮ ስኳሩን ከማሩ ጋር በፈላ ውሃ እያቀለጠ በመቀላቀል ላይ ሳለ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለጹት ረዳት እንስፔክተሩ ግለሰቡ ካቀለጠ በኋላ ለካፌ ባለቤቶች ለፈጢራ ምግብ እና ለሌሎችም የምግብ አገልግሎት በንፁህ ማር ስም ከወለድያ እስከ አላማጣና ሌሎች አካባቢዎችም በመዘዋወር ሲሸጥ መኖሩን የእምነት ቃል ሰጥቷል ብለዋል።

ኢንስፔክተር አያይዘውም አሁን ላይ እጅ ከፍንጅ የያዝነው ውሃ፣ ስኳርና ማር ሲሆን፤ የሚያቀልጥበት ቤትም ከወለሉ እስከ ጥራው በቆሻሻ የተሞላ መሆኑን ገልጸው ለጊዜው እኛ በዓይናችን ማየት ያልቻልነው ሌላም የተጨመረ ባዕድ ነገር ካለ ከጤና ተቋማት ጋር በመሆን የምርመራ ሥራው በላቡራቶሪ እንዲደገፍ እያደረግን ነው ብለዋለ።

በመጨረሻም ረ/ኢንስፔክተር ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው የወንጅል ክስ የመመስረት ሂደት መጀሙሩን ገልጸው፤ ሕብረተሰቡ እንዲህ ዓይነት ድርጌቶችን በቅርበት ለሚገኝ የፖሊስ ተቋም በመጠቆም የራስንም የበርካታ ሕዝብንም ከጤና እክል የመታደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ዘገባው የወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው!!

@fastmereja
4.6K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 22:42:45 በባሕር ዳር እና አካባቢው ገበያዎች አንድ ኩንታል ጤፍ እስከ 10 ሺሕ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ሸማቾች እና ነጋዴዎች ተናገሩ

በባሕር ዳር እና አካባቢው ገበያዎች አንድ ኩንታል ጤፍ እስከ 10 ሺሕ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ሸማቾችና ነጋዴዎች ተናገሩ። ባለፉት ጥቂት ወራት በጤፍ ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የሸማቾችን አቅም እየተፈታተነ ነው። የማዳበሪያ እጥረት በገበሬዎች ዘንድ የፈጠረው ሥጋት እና የመንግሥት የቁጥጥር ማነስ ለዋጋ ጭማሪው እንደ ገፊ ምክንያት ይቀርባሉ

የምግብ እህል ዋጋ በእጅጉ እየጨመረ በመሄዱ ነዋሪዎች ኑሯቸውን ባግባቡ መምራት መቸገራቸውን ገልጠዋል፣ አንድ ኩንታል ጤፍ ባህር ዳር ላይ እስከ 10ሺህ ብር እየተሸጠ ነው፣ ሸማቾችም ሆኑ ነጋዴች ለምግብ ዋጋ መጨመር ከማዳበሪያ እጥረት ጋር በተያያዘ ነው ይላሉ፣ በቀጣይ ዓመት ምርት ላይኖር ይችላል ከሚል ስጋት አርሶ አደሩ ምርቱን ወደ ገበያ ማውጣት ባለመቻሉ የጤፍ ዋጋ ንሯል ብለዋል፣ አንድ አርሶአደር በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ዋጋ መናሩ ለምግብ እህል መወደድ ሌላው ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢው ነዋሪዎች ሰሞኑን ለዶይቼ ቬሌ እንዳመለከቱት፣ በስፋት በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት ለምግብነት የሚያገለግለው ጤፍ ባለፉት 3 ወራት ብቻ እጥፍ በሚባል ደረጃ በመጨመሩ ኑሮን በአግባቡ ለመምራት ተቸግረዋል፡፡

ወ/ሮ ላዋይሽ አደመ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ በባህር ዳር ከተማ አንዱ በሆነው የጤፍ ገበያ ጤፍ ሲሸምቱ አግኝተናቸው ነበር፣ አንድ ኩንታል ጤፍ ካለፈው ወር በ3000 ብር ጭማሪ እንዳሳየ ነግረውናል፣ ምክንት ያሉትንም አብራርተዋል፡፡

ዘገባው የዶይቼ ቬሌ ነው!!

@fastmereja
7.2K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 14:12:12
ከንቲባው ከአዞ ጋር ጋብቻ ፈፀመ "እርስ በርሳችን እንዋደዳለን" ብሏል
#FastMereja

በደቡባዊ ሜክሲኮ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ሳን ፔድሮ ሁአሜሉላ ከንቲባ አንዲት ሴት አዞ ለዘመናት በዘለቀው የአምልኮ ሥርዓት መሰረት ትዳር መሥርተዋል ይህም ለህዝባቸው መልካም ዕድል ለማምጣት ነው።

"እርስ በርሳችን ስለምንዋደድ ሃላፊነት እቀበላለሁ፣ ያለፍቅር ትዳር መመሥረት አይቻልም›› ብሏል በጋብቻ ስነ ስርዓቱ ወቅት

መልካም ጋብቻ

@fastmereja
8.6K views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ