Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-10-05 14:38:19 ከአርብ መስከረም 25 እስከ ቅዳሜ በዓሉ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ የአዲስ አበባ መንገዶች!
#FastMereja
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶችን ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
***
መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ/ም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

በዓሉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ አዲስ ፖሊስ ገልፆል፡፡ በመሆኑም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቅ
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ
• ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
• ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
• ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ
• በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ
• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ
• ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ
• ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
• ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ
• ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ
• ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ
ከአርብ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-26- 43-59 ፣ 011- 5- 52- 63-02/03 ፣ 011-542-40-77፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987 ፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀም እንደሚችልና ለፀጥታ ስራው ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር በመላው የፀጥታ አካላት ስም አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን እያቀረበ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

@fastMereja
15.6K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-03 12:35:34 በሰሜን ጎንደር ዞን የተከሰተው ድርቅ እና እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ከዞኑም ከክልሉም አቅም በላይ ነው ሲል ዞኑ ተናገረ
#FastMereja
የሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በድርቅ ምክንያት እስካሁን 32 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ከ53 ሺህ በላይ እንስሳትም ሞተዋል። ድርቅ ከከፋባቸው ወረዳዎችም እና አካባቢዎች ዜጎች ቄያቸውን ለቀው እየተሰደዱ እንደሚገኙ ሸገር ኤፍ ኤም ዘገባ ያሳያል። ዞኑ ያለው ችግር ከዞንም ከክልልም አቅም በላይ እንደሆነ ገልጿል።

@fastmereja
13.7K views09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-25 13:04:58 ለሞተር ብስክሌተኞች፣ ለባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ

በአዲስ አበባ የምትገኙ የሞተር ብስክሌተኞች፣ የባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ ከዛሬ መስከረም 14/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 29/2016ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌትን፣ የባለ አራት እግርና የባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ያሳውቃል፡፡

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን፤ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው እየገለፀ፤ ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው ያሳስባል፡፡

@fastmereja
14.2K viewsedited  10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-22 17:33:31 በአዲስ አበባ ከተማ ሽንኩርት በኪሎ ከ95 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑ ሸማቾች ተናገሩ

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንድ ኪሎ ሽንኩር ከ95 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑን ነዋሪዎች ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ በየጊዜው በአትክልት ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ ከገቢያቸው ጋር ሊመጣጠን እንዳልቻለ እና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተናግረዋል።ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ የከተማ አስተዳደሩ ከአምራች አርሷ አደር ማህበራ እና ከክልሎች ጋር በመቀናጀት ለነዋሪው ሽንኩርት እያቀረበ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በዋነኛነት 72 የሚደርሱ የእሁድ ገበያ ቦታዎች እንዳሉ እና በከተማ ውስጥ የተገነቡ ወደ አገልግሎት እየገቡ ያሉ የአትክልትና የፍራፍሬ ማቅረቢያ ማዕከላት ውስጥም የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ባማከለ ሁኔታ እንዲሸጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።በዚህ ገበያ ላይ እንደየ ጥራቱ ደረጃው ሽንኩርት ከ47 ብር እስከ 62 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ሰውነት ከበአሉ ወዲህ ጭማሪ መኖሩን እኛም ታዝበናል ያሉ ሲሆን በመደበኛ ገበያ ውስጥ አላስፈላጊ እና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪዎች መታየታቸውን ገልፀዋል።ለዚህም የደላሎች ጣልቃ ገብነት ተገቢ ላልሆነው እና ምክንያታዊ አይደለም ለተባለው የዋጋ ጭማሪ ሚና አላቸው።

እንደ አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ይህ የዋጋ ጭማሪ ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቅ እና እንደ ቢሮም የገበያ ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን አቶ ሰውነት በእሁድ ገበያዎች ላይ ሽንኩርት ከ47 እስከ 62 ብር እየተሸጠ ነው ቢሉም ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ገበያዎች ላይ ባደረገው ምልከታ ከተገለፀው ዋጋ በላይ እንደሚሸጥ ከሸማቾች ሰምቷል።

Via: ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን

@Fastmereja
16.6K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-19 14:59:45 የ6 ልጆቿን አባትና የትዳር አጋሯን ለሁለተኛ ሚስቱ ያዳላል በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ሚስት በቁጥጥር ስር ዋለች።
#FastMereja
በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት እንስፒክተር አዳነ አለማየሁ እንደገለፁት በሚዛን አማን ቀበሌ ቀጠና 3 ልዩ ስፍራው ኮመታ ተብሎ በሚጠራበት መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት የ22 አመት ትዳር አጋሯንና የስድስት ልጆቿን አባትና ባለቤቷን በስለት አንገቱን በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር አድርጎ ባደረገው ቅድመ ምርመራ ለ22 አመታት በትዳር መቆየታቸውንና ሁለት ወንድና አራት ሴቶችን በጠቅላላው ስድስት ልጆችን መውለዳቸውንና ከሶስት አመታት በፊት ሌላ ትዳር መስርቶ ሁለተኛ ሚስት በማግባት ለሁለተኛ ሚስቱ በብዛት ያዳላል የሚል ቅሬታ መፈጠሩን በምርመራ ደርሻለሁ ያለው ፖሊስ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽቱን ሰክሮ በመምጣት በ50 ብር የገዛሁትን ጎመን በመርገጡ የተበሳጨችው ሚስት ጉሮሮውን በማነቅ መሬት ላይ በመጣል ጎመን በምትከትፈው ቢላዋ አንገቱን በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያል ማድረጓን ለመርማሪ ፖሊስ በሰጠችው ቃል መረጋገጡን ረዳት ኢንስፒክተር አዳነ አለማየሁ ገልፀዋል፡፡

ግለሰባ በፈፀመችው ግድያ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራባት ሲሆን የምርመራ መዝገቡ እንደተጠናቀቀ ክስ እንዲመሰረትባት ለዐቃቤ ህግ እንደሚላክ አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ወንጀል መፈፀም ቤተሰብ የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ህ/ሰቡ በስሜት ተነሳስቶ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘገባዉ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነዉ

@fastmereja
13.6K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-18 16:59:45
በጀርመን ስቱትጋርት ከተማ በኤርትራውያን የባሕል ፌስቲቫል፤ ኤርትራውያኑ እርስበእርስና ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ አምባጓሮ 26 ፖሊሶችን ጨምሮ በአስራዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ ሲል የጀርመን ድምፅ የሆነው ዶይቼ ቬለ ነው የዘገበው። በቅርቡ በእስራኤል ተመሳሳይ ነገር ተከስቶ ጠቅላይ ሚንስትር ጭምር አስቆጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።

@FastMereja
13.5K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-17 17:49:33
በጋምቤላ ክልል በዲማ ከተማ ፆታውን ሴት በማስመሰል የሴት ልብስ በመልበስ በሆቴል ስራ ሊቀጠር ያሰበ ወጣት በወረዳው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ፋስትመረጃ ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ሰምቷል።

@FastMereja
13.2K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-11 20:48:03 በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና ከፍተኛ ሽልማቶችን የያዘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ዛሬ ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ላይ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥተዋል ፡፡

በወጣው ዕጣ መሰረት ፡-
የ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1820259
የ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1656546
የ3ኛ ዕጣ 5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 2118779
የ4ኛ ዕጣ 3 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 0865504
የ5ኛ ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1020830
የ6ኛ ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1317686
የ7ኛ ዕጣ 500,000 ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1903473
እና ሌሎች ዕጣዎች የወጡ ሲሆን የማስተዛዘኛ ዕጣ ቁጥርም 6 በመሆን ወጥተዋል ፡፡

@fastmereja
15.0K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 11:16:07
አርቲስት አንዱአለም ጎሳ እና አርቲስት ጫላ ቡልቱሜ መካከል የነበረው በሽምግልና እርቅ መፈፀሙ ለፋስትመረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
@FastMereja
14.8K views08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 10:45:15
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለፁ።
@FastMereja
13.1K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ