Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ ሽንኩርት በኪሎ ከ95 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑ ሸማቾች ተናገሩ በአዲስ አ | FastMereja.com

በአዲስ አበባ ከተማ ሽንኩርት በኪሎ ከ95 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑ ሸማቾች ተናገሩ

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንድ ኪሎ ሽንኩር ከ95 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑን ነዋሪዎች ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ በየጊዜው በአትክልት ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ ከገቢያቸው ጋር ሊመጣጠን እንዳልቻለ እና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተናግረዋል።ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ የከተማ አስተዳደሩ ከአምራች አርሷ አደር ማህበራ እና ከክልሎች ጋር በመቀናጀት ለነዋሪው ሽንኩርት እያቀረበ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በዋነኛነት 72 የሚደርሱ የእሁድ ገበያ ቦታዎች እንዳሉ እና በከተማ ውስጥ የተገነቡ ወደ አገልግሎት እየገቡ ያሉ የአትክልትና የፍራፍሬ ማቅረቢያ ማዕከላት ውስጥም የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ባማከለ ሁኔታ እንዲሸጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።በዚህ ገበያ ላይ እንደየ ጥራቱ ደረጃው ሽንኩርት ከ47 ብር እስከ 62 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ሰውነት ከበአሉ ወዲህ ጭማሪ መኖሩን እኛም ታዝበናል ያሉ ሲሆን በመደበኛ ገበያ ውስጥ አላስፈላጊ እና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪዎች መታየታቸውን ገልፀዋል።ለዚህም የደላሎች ጣልቃ ገብነት ተገቢ ላልሆነው እና ምክንያታዊ አይደለም ለተባለው የዋጋ ጭማሪ ሚና አላቸው።

እንደ አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ይህ የዋጋ ጭማሪ ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቅ እና እንደ ቢሮም የገበያ ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን አቶ ሰውነት በእሁድ ገበያዎች ላይ ሽንኩርት ከ47 እስከ 62 ብር እየተሸጠ ነው ቢሉም ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ገበያዎች ላይ ባደረገው ምልከታ ከተገለፀው ዋጋ በላይ እንደሚሸጥ ከሸማቾች ሰምቷል።

Via: ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን

@Fastmereja