Get Mystery Box with random crypto!

ለሞተር ብስክሌተኞች፣ ለባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ በአዲስ አ | FastMereja.com

ለሞተር ብስክሌተኞች፣ ለባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ

በአዲስ አበባ የምትገኙ የሞተር ብስክሌተኞች፣ የባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ ከዛሬ መስከረም 14/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 29/2016ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌትን፣ የባለ አራት እግርና የባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ያሳውቃል፡፡

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን፤ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው እየገለፀ፤ ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው ያሳስባል፡፡

@fastmereja