Get Mystery Box with random crypto!

የ6 ልጆቿን አባትና የትዳር አጋሯን ለሁለተኛ ሚስቱ ያዳላል በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ሚስ | FastMereja.com

የ6 ልጆቿን አባትና የትዳር አጋሯን ለሁለተኛ ሚስቱ ያዳላል በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ሚስት በቁጥጥር ስር ዋለች።
#FastMereja
በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት እንስፒክተር አዳነ አለማየሁ እንደገለፁት በሚዛን አማን ቀበሌ ቀጠና 3 ልዩ ስፍራው ኮመታ ተብሎ በሚጠራበት መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት የ22 አመት ትዳር አጋሯንና የስድስት ልጆቿን አባትና ባለቤቷን በስለት አንገቱን በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር አድርጎ ባደረገው ቅድመ ምርመራ ለ22 አመታት በትዳር መቆየታቸውንና ሁለት ወንድና አራት ሴቶችን በጠቅላላው ስድስት ልጆችን መውለዳቸውንና ከሶስት አመታት በፊት ሌላ ትዳር መስርቶ ሁለተኛ ሚስት በማግባት ለሁለተኛ ሚስቱ በብዛት ያዳላል የሚል ቅሬታ መፈጠሩን በምርመራ ደርሻለሁ ያለው ፖሊስ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽቱን ሰክሮ በመምጣት በ50 ብር የገዛሁትን ጎመን በመርገጡ የተበሳጨችው ሚስት ጉሮሮውን በማነቅ መሬት ላይ በመጣል ጎመን በምትከትፈው ቢላዋ አንገቱን በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያል ማድረጓን ለመርማሪ ፖሊስ በሰጠችው ቃል መረጋገጡን ረዳት ኢንስፒክተር አዳነ አለማየሁ ገልፀዋል፡፡

ግለሰባ በፈፀመችው ግድያ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራባት ሲሆን የምርመራ መዝገቡ እንደተጠናቀቀ ክስ እንዲመሰረትባት ለዐቃቤ ህግ እንደሚላክ አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ወንጀል መፈፀም ቤተሰብ የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ህ/ሰቡ በስሜት ተነሳስቶ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘገባዉ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነዉ

@fastmereja