Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-07-02 12:22:32
በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሣማ ቀበሌ ሰኔ 24/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ላይ ከአዳማ ወደ አረርቲ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ ህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ በአደጋው 3 ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 12 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል። ተጎጅዎች በአረርቲ ሆስፒታል እየታከሙ ሲሆን ለአደጋው ፍጥነት መንስኤ እንደነበር የአማራ ፖሊስ ዘገባ ያመላክታል።

@FastMereja
8.3K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 14:37:52
በሲኖ ትራክ በሁለት የተለያየ ቦታ የሰው ህይወት አለፈ!
#FastMereja
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያየ አካባቢ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከቀኑ 5:37 ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰሜን ሆቴል ፊትፊት “ሲኖ ትራክ” እየተባለ የሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረን የ50 ዓመት ጎልማሳ በመግጨቱ ሕይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ትናንት ምሽት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጣፎ 2ኛ በር አካባቢ መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረ የ44 ዓመት ጎልማሳ እንዲሁም በ “ሲኖ ትራክ” የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ተገጭቶ ሕይወቱ ማለፉን ፋና ነው የዘገበው።

@fastmereja
10.3K views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 14:31:13
ኤርትራዊያንን በህገወጥ መንገድ ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተሽከርካሪ አደጋ ደረሰበት
#FastMereja
በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ በቀን 23/10/2015 አንድ የህዝብ መጫኛ መለስተኛ ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ የመንቀሳቀስ ፈቃድ የሌላቸውን 19 ኤርትራዊያን በመጫን በፍጥነትና ህጋዊነት በጎደለው መንገድ በማሽከርከሩ የመገልበጥ አደጋ የደረሰ ሲሆን በአደጋው አንድ የሞት፣ አንድ ከባድ ጉዳትና ስድስት ሰው ቀላል ጉዳት ሊደርስ ችሏል።

መረጃዉ የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ ነው

@fastmereja
8.9K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 20:54:48 የወረዳ ዋና ስራ አስፈጻሚና ምክትላቸው የሙስና ጉቦ ሲቀበሉ በዛሬው ዕለት እጅ ከፍንጅ ተያዙ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 ዋና ስራ አስፈጻሚና ምክትላቸው በመስሪያ ቦታ አሰጣጥ ተደራድረው የሙስና ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፈንጅ መያዙን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረ/ኮሚሽነር ፋሲካ ፈንታ እንደገለጹት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ከስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ብሎክን መሰረት በማድረግ የተፈጠረ የስራ እድል ላይ ከተጠቃሚ ወላጅ ጋር የተሻለ የመስሪያ ቦታ በጉንድሽ የመስሪያ ቦታ እናሰጣለን በማለት የተጠቃሚዋን ወላጅ አባት ብር ካልሰጠኸን ልጅህን ከስልጠና እናወጣታለን፣ የስራ እድልም አይፈጠርላትም በማለት ወላጅ አባቷን በማስፈራራት ልዩ ስሙ 6 ኪሎ አከባቢ ልዩ አዲስ ሆቴል 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

እጅ ከፍንጅ የተያዙት ግለሰቦች 1ኛ የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አያናው አስራት እና 2ኛ የወረዳው ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እዮብ አፈወርቅ 5000 ብር በዛሬ እለት ከቀኑ 10:30 ሰዓት ሲቀበሉ ክትትል በማድረግ በጸጥታ ሃይሎች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ገብተው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

የክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ ይህንን አይነት ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ተግባር ኮንነው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የከተማችን ነዋሪ በየትኛውም የመንግስት ተቋም ለሚሰጡ አገልግሎቶች ሙስና ለመቀበል የሚጠይቁና የሚቀበሉ ማናቸውንም አካላት በመጠቆም ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈዋል።

የከተማችን ነዋሪ በዚህ አጊጣሚ መሰል ነገር በሚገጥመው ወቅት ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ለህግ አስከባሪ አካላት የተለመደ ትበብሩን እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

አዲስ አበባ ፖሊስ

@fastmereja
10.1K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 17:21:41
በሲዳማ ክልል በጤጢቻ ወረዳ ልዩ ቦታ ሀንጋኤ ከሚባል ቀበሌ አንድ ላም ሁለት አንገት፤ አራት ዓይን፤ ሁለት ፊትና አራት ጆር ያለዉ ጥጃ ወልዳለች በማለት ግርማ ካሳ ለፋስት መረጃ መረጃውን አድርሷል።

@fastmereja
9.8K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 11:53:21
የጣሊያን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ በ86 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

@fastmereja
3.0K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 11:28:13
ባለመነፅር ስናይፐር የሰራው ወጣት!!!
#FastMereja
አማኑኤል አንዱአለም ይባላል የዳንግላ ከተማ ተወላጅ ነው። አማኑኤል ከድሮ ጀምሮ ከትምህርቱ ጎን ለጎን የፈጠራ ስራ በመስራት እያደገ የመጣ ታታሪ ልጅ ነው ታዲያ ይህን ልዩ ተሰጥኦውን በትምህርት እና በሳይንስ የተደገፈ አድርጎ ወደፊት ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ወደ ዳንግላ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋም በመቀላቀል ያለውን ተሰጥኦ እንዲጎለብት በማድረግ ትምህርቱን አጠናቋል። ወጣት አማኑኤል ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ብዙ የፈጠራ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ታዲያ በቅርቡ ደግሞ በአይነቱ ለየት ያለ ባለመነፀር ስናይፐር ሰርቶ ብቅ ብሏል:: ከዚህ ቀደም በዳንግላ ከተማ ተማሪ ሀብታሙ ድሽቃ እና ላውንቸር ሰርቶ እንደነበር ይታወሳል።

@fastmereja
3.4K views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:33:48
ፌስቡክ ገፃችን ላይ ያያችሁት ምስል የልጁ ቪዲዮ እና አድራሻው!!
6.4K viewsedited  15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 17:42:56
ኮሜዲያን ክበበው ገዳ ከዘጠኝ አመታት በኋላ ከቤተሰቡ ጋር ተገናኝቷል። ኮሜዲያኑ ኑሮውን አሜሪካ በማድረጉ ለዘጠኝ አመታት ከቤተሰቡ ጋር ሳይገናኝ ቆይቶ የነበረ ሲሆን አሁን ባለቤቱ እና ልጆቹ ወደ አሜሪካ በመሄዳቸው ከ9 አመታት በኋላ ለመገናኘት በቅቷል።

@fastmereja
6.8K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 15:49:16
"ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው" አቶ ጌታቸው ረዳ

" ልዩነቶችን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር መፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት አለው " ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

ባህር ዳር የሚገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር እንዲሁም ከህብረተሰቡ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

@fastmereja
6.9K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ