Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-20 21:39:27
አርሰናል ማል ታቴ? ሲቲ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ሻምፒዮን መሆኑ ታወቀ!
#FastMereja
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ለረጅም ጊዜ ሲመራ የነበረው አርሰናል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሪነቱን ለማንችስተር ሲቲ አስረክቦ ከዋንጫ መሸሹ በርካቶችን አስገርሟል። ከብራይተን ሽንፈት ማገገም ያልቻሉት አርሰናሎች ዛሬም በኖቲንግሃም ፎረስት 1 ለ 0 ተሸንፏል። ማንችስተር ሲቲ ነገ ሳይጫወት የዋንጫው ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።

@fastmereja
6.4K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:24:53 በቀን እስከ 35ሺ ብር የሚቆጥቡ ሿሿ ሰሪዎች
#FastMereja
ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎቹ በቀን እስከ 35ሺ ብር ተቀማጭ  እንደሚያደርጉ በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብን ለምሬት ከዳረጉ የወንጀል ድርጊቶች መካከል በተለምዶ ሿሿ የሚባለው ወንጀል አንዱ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀሉን ለመከላከል እና ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ በጥናት ላይ ተመስርቶ ባከናወነው ተግባር በተለያዬ ክፍለ ከተሞች ወንጀሉን ሲፈፅሙ የነበሩ 25 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ አያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ኃይል በመጠቀም ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንበሳ ጋራዥ አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦሮ 86853 ነጭ ሚኒባስ በመጠቀም ከአንድ ግለሰብ ላይ 10ሺ ብርና ግምቱ 14 ሺብር የሚወጣ ሞባይል ስልክ ሰርቀው ይሰወራሉ፡፡ ፖሊስ ጠንካራ  ክትትል  በማድረግ ወንጀል ፈፃሚዎቹን ከእነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር በማዋልና ምርመራ በማስፋት ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ 14 ወንጀል ፈፃሚዎችን እና  የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ኦሮ 79184 ሚኒባስ ተሽከርካሪን ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ /ም ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ረዳት ኮሚሽነር ፋሲካ ፋንታ አስታውቀዋል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ግለሰቦች በቦሌ ክፍለ ከተማ 6 ቦታዎች ፣ በየካ ክፍለ ከተማ 3 ቦታዎች እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 3 ቦታዎች ላይ ወንጀሉን መፈፀማቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

አቶ በሪሁን ካሳው ይባላሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ዘሪሁን ህንፃ አከባቢ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ግምቱ 10ሺ ብር የሚያወጣ  ሞባይል ስልክ በወንጀል ፈፃሚዎች  የተሰረቀባቸው  ቢሆንም ፖሊስ ንብረተቻውን ማስመለሱን ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ አቶ አበበ በቀለ ወደ ስራ በመሄድ ላይ እያሉ በእነዚሁ ወንጀል ፈፃሚዎች ግምቱ 10ሺ ብር የሚያወጣ ስልክ መሰረቃቸውን እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል በተሰረቁ ጥቂት ሰዓት ውስጥ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ተይዘው  ንብረታቸው መገኘቱን አስረድተዋል፡፡

በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያላቸው 19 ወንዶችና 6 ሴቶች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ሁለት ሚኒ-ባስ መኪናዎች እንዲሁም ግለሰቦቹ ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው 4 ልዩ ልዩ ተሸከርካሪዎች ፣ 82 ሺ 680  ጥሬ ብር ፣ 14 ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ስማርት ስልኮች እና የቀን ተቀማጭ የሚያስቀምጡበት ደብተር በኤግዚቢትነት እንደተያዘ ረዳት ኮሚሽነር ፋሲካ ፋንታ አስረድተዋል፡፡

ግለሰቦች ምንም አይነት ህጋዊ ገቢ የሚያገኙበት ስራ የሌላቸው ቢሆንም ከፍተኛው በቀን 35 ሺ ብር አነስተኛው 5ሺ ብር የቀን ተቀመጭ ሲያደርጉ እንደነበር  በኤግዚቢትነት ከተያዘው ሰነድ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተፈፀመባቸው ግለቦች አዲስ አበባ ፖሊስ  ጉለሌ ክፍለ በመቅረብ በኤግዚቢትነት ከተያዙ ስልኮች መካከል መምረጥ እንደሚችሉ ረዳት ኮሚሽነር ፋሲካ አስታውቀዋል፡፡

በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ ወንጀለኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው ወንጀሉን እንደሚፈፅሙ እና መነሻና መድረሻ የሌላቸው ሲሆኑ  ተሳፋሪውን የትነው የምትሄደው የሚል ጥያቄ እንዲሚያቀርቡ ህብተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደለበት ኃላፊው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፇል።

@fastmereja
6.3K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:24:26
5.4K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:05:19
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ተወሰደ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ግንቦት 12፤ 2015 ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ተመስገንን የወሰዱት በሁለት ፒክ አፕ ተጨነው የመጡ እና የፖሊስ ደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እስከ ምሽት ድረስ ከቅርብ ጓደኞቹ የነበረው ተመስገን፤ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በሚገባበት ወቅት፤ የግቢ ዙሪያው በጸጥታ ኃይሎች ተከብቦ ማግኘቱን የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል።

ምንጭ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@fastmereja
6.1K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 14:40:14
የሟቾች ቁጥር 20 ደረሰ!!
#FastMereja
የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው መኪና በደረሰበት አደጋ በአሁኑ ወቅት የሟቾች ቁጥር 20 መድረሱ ተገለፀ። አደጋው የደረሰው መምህራኑ ሻሸመኔ ካምፓስ ለማስተማር ወደ ዶዶላ እየተጓዙ እያሉ በም/አርሲ ዋሻ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መኪናው መንገድ ስቶ ገደል ውስጥ በመግባቱ መሆኑን ለፋስት መረጃ የደረሰው መልዕክት ያመላክታል። የቀሩት አዳባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

@fastmereja
6.8K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 12:20:49 15 የዩንቨርሲቲ መምህራን በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ
#FastMereja
የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን ህይወት ማለፉን ገልፀዋል ሲል ኦቢኤን ነው የዘገበው።

@fastmereja
6.9K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 14:34:40
የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ከየካቲት 5/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ይህ አዋጅ የታክሱን መሰረት በማስፋት እና የታክሱን አስተዳደር ስርዓት በመቀየር ከፍተኛ ጠቀሜታን አስገኝቷል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባኤው በአዋጁ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ታሳቢ በማድረግ የአዋጁ ማሻሻያ ተደርጓል።

የአዋጁ ማሻሻያ ታሰቢ ያደረገው ተደራራቢ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ምርቶች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል ለማድረግ፣ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩት አንዳንድ ምርቶች ላይ ታክሱን ለማንሳት፣ እንዲሁም በአስተዳደር ምክንያት የተደረጉ ማስተካከያዎችን እና የማሻሻያውን ዋና ዋና ምክንያቶችን ከመረመረ በኋላ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1287/2015 እንዲጸድቅ አድርጓል።
መረጃው የEBC ነው

@fastmereja
7.8K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 18:44:44
ለመግደል የመጣዉን የገደለዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
#FastMereja
ተከሳሽ ምትኩ ፋጅዬን የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለዉ ያለበቂ ምክንያት ሊገለዉ የመጣዉን በመግደሉ ነዉ።

ነገሩ እንዲህ ነው ተከሳሹ ምክንያቱን በማያዉቀዉ ጉዳይ ጦርና ገጀራ ይዞ እየዛተበት ሲመጣ እግሬ አዉጪኝ በማለት ከአከባቢዉ ይሸሻል። ከጥቂት ሰዓታት ቆይታ በኃላ ወደ መኖሪያ ቤቱ ተመልሶ እያለ አሁንም ለመግደል ሲያሳድደዉ ሊገለዉ የመጣዉ በያዘዉ ገጀራ ይገለዋል።

የመኤንት ወረዳ ፖሊስ የወንጀል ግድያ የፈፀመዉን በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ አጣርቶበት ለዐቃቤ ህክ የምርመራ መዝገቡን ይልካል።

ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ የደረሰዉ የምርመራ መዝገብ መሠረት በማድረግ ተጨማሪ ምስክሮችን አስቀርቦ ችሎት በማሰማት እዉነቱ እንዲወጣ በማድረግ በከባድ የሰዉ መግደል ወንጀል ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት አቅርቦታል።

የሜኤኒት አከባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽ እራሱን ለመከላከል ሲል በፈፀመዉ ግድያ የህግ አንቀፅ ጠቅሶ ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

በዚሁ መሠረት የሜኤኒት አከባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ምትኩ ፋጅዩ እጁ በፖሊስ ከተያዘበት ጀምሮ የሚታሰብ በሁለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት ከምዕራብ ኦሞ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትን ጠቅሶ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽ ነው የዘገበው።

@fastmereja
3.9K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 18:37:59
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እግር ኳስን በታማኝነት ላገለገለው አንጋፋው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ (ጎራዴው) ለሕክምና ወጪ የሚውል የ250ሺ ብር ድጋፍ አደረጉ።

በአስራት ኃይሌ መኖርያ ቤት በተደረገው ጥየቃ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባስተላለፉት መልዕክት በሴካፋ ያመጣው ድል በእግር ኳስ ፌድሬሽን በሰጠው አመራርነት በርካታ አሰልጣኞችን በማፍራት የሚታወቀውን አስራት ኃይሌ በማገዛችን ትልቅ ክብር ይሰማናል ብለዋል።

@fastmereja
3.8K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 08:39:06 «ዲቪ 2023 የደረሰን ሰዎች ሊቃጠልብን ነው» ባለ እድለኞች
«ዲቪ ለደረሳቸው ሁላ ቪዛ አልሰጥም» አሜሪካ ኤምባሲ
#FastMereja

የ2023 የዲቪ ሎተሪ ባለዕድል ከሆኑት መካከል እስካሁን ኤምባሲው ለ123 ሰዎች ሂደቱን ጨርሶ ቪዛ እንደሰጠ፣ የ130 ሰዎች የቪዛ ጥያቄያቸው እየታየ መሆኑን እንዲሁም ሌሎች 130 ባለዕድሎች ደግሞ ሂደቱን መጀመራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

“. . .ስለዚህ ከ2761 ዕድለኞች ውስጥ ለ383 ሰዎች ብቻ ነው ሂደቱ የተጀመረላቸው ወይንም ያለቀላቸው። ኤምባሲው በወር ውስጥ እያስተናገደ ባለው የሰው ቁጥር መሰረት 2200 የሚሆኑት ሰዎች ዕድላቸው ወደ መቃጠል እየሄደ ነው” ይላል አቶ አያና የዲቪ 2023 እድለኛ ስጋቱን ሲገልፅ።

አቶ ሙሉቀን ጣሰው በበኩሉ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኛ መሆኑን ባወቀ ጊዜ እርሱም ሆነ ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸው እነደነበር ያስታውሳል።

የባንክ ማናጀር የነበረው ሙሉቀን የዲቪ እንደደረሰው ካወቀ በኋላ “ወደ አሜሪካ በቅርቡ እሄዳለሁ በሚል ተስፋ ሥራዬን ለቅቄ በግል ሥራ ላይ አትኩሬ ነበር” በማለት አሁን ግን ይህ ዕድል ወደ ሊቃጠል ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ መሆኑን ተናግሯል።

“አሁን አሁን ሳስበው ምናለበት የዲቪው ሎተሪው ባይወጣልኝ ብዬ እያሰብኩ ነው። ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ መቼ ነው የምትሄደው እያሉ ይጠይቁኛል። ይህ ዕድሌ ከተቃጠለ እዚህ ከተማ ውስጥ መኖር አልችልም” ይላል ሙሉቀን።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት በኮቪድ እና በሌሎች ችግሮች ምክንያት በርካታ ውዝፍ ሥራዎች ስለነበሩበት በሚፈለገው ሁኔታ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞችን ለማስተናገድ እንዳልቻለ ገልጿል።

ለዲቪ ዕድለኞች የቪዛ መስጠት ሂደት “በአጭር ጊዜ ውስጥ በአስቸኳይ የሚከናወን ሥራ ስላልሆነ” በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ሁሉንም የዲቪ ዕድል አሸናፊዎች ማስተናገድ እንደማይቻልም ገልጿል።

@fastmereja
6.0K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ