Get Mystery Box with random crypto!

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደረገ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎ | FastMereja.com

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ከየካቲት 5/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ይህ አዋጅ የታክሱን መሰረት በማስፋት እና የታክሱን አስተዳደር ስርዓት በመቀየር ከፍተኛ ጠቀሜታን አስገኝቷል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባኤው በአዋጁ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ታሳቢ በማድረግ የአዋጁ ማሻሻያ ተደርጓል።

የአዋጁ ማሻሻያ ታሰቢ ያደረገው ተደራራቢ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ምርቶች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል ለማድረግ፣ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩት አንዳንድ ምርቶች ላይ ታክሱን ለማንሳት፣ እንዲሁም በአስተዳደር ምክንያት የተደረጉ ማስተካከያዎችን እና የማሻሻያውን ዋና ዋና ምክንያቶችን ከመረመረ በኋላ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1287/2015 እንዲጸድቅ አድርጓል።
መረጃው የEBC ነው

@fastmereja