Get Mystery Box with random crypto!

ለመግደል የመጣዉን የገደለዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ #FastMereja ተከሳሽ ምትኩ ፋጅዬን የእ | FastMereja.com

ለመግደል የመጣዉን የገደለዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
#FastMereja
ተከሳሽ ምትኩ ፋጅዬን የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለዉ ያለበቂ ምክንያት ሊገለዉ የመጣዉን በመግደሉ ነዉ።

ነገሩ እንዲህ ነው ተከሳሹ ምክንያቱን በማያዉቀዉ ጉዳይ ጦርና ገጀራ ይዞ እየዛተበት ሲመጣ እግሬ አዉጪኝ በማለት ከአከባቢዉ ይሸሻል። ከጥቂት ሰዓታት ቆይታ በኃላ ወደ መኖሪያ ቤቱ ተመልሶ እያለ አሁንም ለመግደል ሲያሳድደዉ ሊገለዉ የመጣዉ በያዘዉ ገጀራ ይገለዋል።

የመኤንት ወረዳ ፖሊስ የወንጀል ግድያ የፈፀመዉን በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ አጣርቶበት ለዐቃቤ ህክ የምርመራ መዝገቡን ይልካል።

ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ የደረሰዉ የምርመራ መዝገብ መሠረት በማድረግ ተጨማሪ ምስክሮችን አስቀርቦ ችሎት በማሰማት እዉነቱ እንዲወጣ በማድረግ በከባድ የሰዉ መግደል ወንጀል ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት አቅርቦታል።

የሜኤኒት አከባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽ እራሱን ለመከላከል ሲል በፈፀመዉ ግድያ የህግ አንቀፅ ጠቅሶ ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

በዚሁ መሠረት የሜኤኒት አከባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ምትኩ ፋጅዩ እጁ በፖሊስ ከተያዘበት ጀምሮ የሚታሰብ በሁለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት ከምዕራብ ኦሞ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትን ጠቅሶ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽ ነው የዘገበው።

@fastmereja