Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-06-06 23:06:34
በሽሬ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በተፈናቃዮች መጠለያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
#FastMereja
በሽሬ ከተማ 18 መጠለያዎች ያሉ ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በማዕከሉ ውስጥ እንደሚገኙ ፋስት መረጃ ከትግራይ ቴሌቪዥን ሰምቷል።
በሰብአዊ እርዳታና በመድሃኒት እጦት በረሃብና በበሽታ እየተሰቃዩ ያሉት አሁን ደግሞ በከተማው በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት መጠለያው እየፈራረሰ በመሆኑ ለተጨማሪ ችግር ተዳርገዋል።

ተፈናቃዮቹ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በመጠለያ ውስጥ ከሁለት አመት በላይ ኖረዋል።

@fastmereja
9.0K views20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 21:55:59
በስህተት የተላከላትን 97 ሺህ ብር ለባለቤቱ መለሰች
#FastMereja
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አዲስ ቅዳም ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው እና የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ ብርሃኑ ግንቦት 16/2015 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ነዋሪ የሆነው አቶ ታምራት አለማየሁ ሴዳ የተባለ ግለሰብ በስህተት 97 ሺህ ብር ይልክላታል።

ግለሰቡም በመደናገጥ ብሩን ትመልስለት ዘንድ በስልክ ይደውልላታል። ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ የተላከላትን ገንዘብ ምንም ሳታወላውል ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ቅዳም ቅርንጫፍ በመሄድ የመለሰችለት መሆኑን አብራርታልናለች ሲል ፋግታ ኮሙኔኬሽን ዘግቧል።

ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ አያይዛም ያለፋበትን የሰው ገንዘብ መውሰድና መጠቀም በምድርም በፈጣሪም ያስጠይቃል እኔ ደግሞ የህግ አካል ነኝ ከኔ ማህበረሰቡ ብዙ ይማራል ስትል ገልፃለች።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ቅዳም ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ቻሌ እንየው በበኩላቸው ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ የራሷ ያልሆነን ገንዘብ መጠቀም ነውር መሆኑን ስለሚያምኑ እና የተሰማሩበት የሙያ ዘርፍም ስርቆትንና ወንጀልን በጅጉ የሚፀየፍ ተቋም መሆኑን በመረዳት የገባላቸውን 97 ሺህ ብር የእርሳቸው አለመሆኑን በመረዳት ወደ ቅርጫፋችን በመምጣት ገንዘቡን ለባለቤቱ ወዲያውኑ የመለሱለት መሆኑን ገልፀዋል።

@fastmereja
9.2K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 21:35:37
ቃልዬ መኮንን ይባላል የምስራቅ ሐረርጌ የደደር ልጅ ነው በስራ ላይ እያለ በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወቱ አልፏል።
#FastMereja
የሆነ እንደዚህ ነው ትናንት ምሽት በጣለው ከባድ ዝናብ ከሐረር ከተማ ወደ ኮምቦልቻ ከተማ የሚሄደው ትልቁ የኃይል መስመር ይቋረጣል ይህን መስመር ጠግኖ ስራ ለማስጀመር ፖሉ ላይ ይወጣል። በስራ ላይ እያለ ሌላኛው መስመር በመነካካቱ ቃልዬ መኮንን በስራ ላይ እያለ ህይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ ፋስት መረጃ ከሐረርጌ ፒክቸርስ መረጃውን አግኝቷል።

ለወዳጅ ዘመድ ቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለን!

@fastmereja
8.5K views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 20:54:08 "ቡዳ ይሉናል፤ ጅብ ይሉናል፤ሌሊት ሌሊት ወደ ጅብነት የሚቀየሩ ይሉናል። 3,000 ዓመታት በኖርንበት አገር ውስጥ ፈላሻ የሚለው ስም መሬት አልባ ለማለት ነው። እዚህ አገር ላይ መሬት የላችሁም ፈልሳችሁ ነው የመጣችሁት የሚል ነው። ይህ ስም ማጠልሸት የስንቱን ትዳር ያናጋና ብዙ ማሕበራዊ ቀውስ ያመጣ ነው።"

በሰሜን ሽዋ በተለያዩ ወረዳዎች ተበትነው እምሮአዊና አካላዊ የጤና ችግር ላለባቸዉ ቤተእስራኤላውያን ጤናማ የሰፈራ መንደር ለመመስረት የተጀመረው ፕሮጀክት። ቤተ-እስራኤላውያን ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በ3 ዙሮች እንደሆኑ በጉዳዩ ላይ ሁለት መጽሐፎችን ያሳተሙት የቤተእስራኤላውያን የኦሪት እምነት ማሕበረሰብ ስራ አስኪያጅና እና የሰሜን ሽዋ የቤተእስራኤላውያን የሰፈራ መንደር ፕሮጀክት ፕረዚደንት መምህር በላይነህ ታዘብኩ ይገልጻሉ።

ጎንደር ደምቢያ ማዕከል አድርገውም ወደ ተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንደ ተንቀሳቀሱም አክለዋል። ቤተ እስራኤላውያኑ በአገሪቱ ታሪክ የራሳቸውን አሻራ እንዳኖሩም ያስረዳሉ።

«ወርቅ ላበደረ ጠጠር ሆነና ነገሩ» ይላሉ መምህር በላይነህ በአገሪቱ ግንባታ የራሳቸውን ሚና ለተጫወቱት እና በመጫወት ላይ የሚገኙት ሕዝቦች የተሰጣቸው ስምና መገለል ግን ሥነ አእምሮዊ እና አካላዊ የጤና ችግር እንዳስከተለባቸው የገለጹት መምህር በላይነህ ማብራሪያቸውን ሲቀጥሉ።

"ቡዳ ይሉናል፤ ጅብ ይሉናል፤ ሌሊት ሌሊት ወደ ጅብነት የሚቀየሩ ይሉናል። ካይላት፣ ቂሌ የተለያዩ ስሞች አሉ የተሰጡን። 3,000 ዓመታት በኖርንበት አገር ውስጥ ፈላሻ የሚለው ስም መሬት አልባ ለማለት ነው። እዚህ አገር ላይ መሬት የላችሁም ፈልሳችሁ ነው የመጣችሁት የሚል ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ የምትኮራባቸው ሦስቱ ሐይማኖቶች ኦሪት፣ ከዛ ክርስኅና ከዛ ክርስትና እነዚህ ሐይማኖቶች ከውጭ እንደመጡ ይታወቃል። የኛን ብቻ ነው ፈልሶ እንደመጣ ተደርጎ የሚወሰደው። ማምለኪያ ቦታዎች፣ የቀብር ቦታዎች እንዳይኖረው ማድረግ፤ ይህ ስም ማጠልሸት የስንቱን ትዳር ያናጋና ብዙ ማሕበራዊ ቀውስ ያመጣ ነው።"

የሚገርመው የአፍሪቃ መዲና በምትባለው አዲስ አበባ የሚኖሩ ቤተእስራኤላውያን እስከዛሬዋ ድረስ ሞተው የሚቀበሩበት ቦታ እንኳን የላቸውም። ሞተው እንደሰው የመቀበር ዕድልን ለማግኘት ከሚኖሩበት አካባቢ ሐይማኖት ጋር ተመሳስለው እና ማንነታቸውን አጥፍተው ጭምር እንደሆነ መምህር በላይነህ በምሬት አጫውተውናል።

ቤተ እስራኤላውያን በማሕበረሰቡ በሚደርስባቸው አድልኦ እና መገለል ምክንያት፤ ተከትሎ የመጣውን የሥነ አዕምሮአዊና አካላዊ ችግሮች በመቅረፍ ፈር ቀዳጅ ይሆናል የተባለለት ፕሮጀክት በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ደብረብርሐን አካባቢ እውን ሊሆን ጫፍ የደረሰ ይመስላል። የሰሜን ሽዋ ቤተእስራኤላውያን የመንደር ምስረታ። የፕሮጀክቱ ሰብሳቢ ዶክተር አክሊሉ ተፈራ።

"የፕሮጀቱ ዓላማ ቤተ እስራኤላውያን በመንደር ተሰባስበው ጤናቸው ተጠብቆ፤ ጽዱና ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት እና ትምህርት ቤት በመገንባት የተሻለ ኑሩ እንዲኖሩ ማስል ነው። "

የቤተ እስራኤላውያን አንዱና ትልቁ ችግር ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት ነው። በዚሁ ምክንያት ሕይወቷን ያጣች ወላጅ እናት፤ ሕጻን አዛውንቱ ቤት ይቁጠረው ብሎ ማለፍ ሳይሻል አይቀርም። ይህን ችግር ለመቅረፍ ግዙፍ ሆስፒታል መገንባት የፕሮጀክቱ አካል እንደሆነ ዶክተር አክሊሉ ነግረውናል።

ቤተእስራኤላውያን አዲስ አበባን ጨምሮ በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የመጸዳጃና የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚያገኙት ዝቅተኛ ሊባል በሚችል ደረጃ መሆኑን የገለጹት መምህር በላይነህ በደብረብርሃን የሚሰሩ መኖሪያ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁና የነበሩባቸውን ችግሮች የሚፈቱ እንደሚሁኑ ገልጸውልናል።

ትኩረት ተነፍጓቸው በአስከፊ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ተገቢው ትኩረትና ክብር ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ ባለጉዳዮች ያሳስባሉ።

ዘገባው የዶይቼ ቬለ ነው።

@fastmereja
8.6K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 20:53:59
8.2K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 19:48:00
ዛሬ ፒያሳ በዕድሳት ላይ የነበረ ቤት ተደርምሶ በሰዉ ላይ ጉዳት ደረሰ

ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ 4 ሰዓት በእድሳት ላይ የነበረ ቤት ተደርምሶ በሰዉ ላይ ጉዳት ደርሷል። በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ ደሀብ ሆቴል አጠገብ በእድሳት ላይ የነበረዉ አንድ ካፌ ተደርምሶ በዚያዉ ስፍራ በመንገድ ላይ ሻይ ከሚሸጡት መካከል 5 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷባቸዋል።

ጉዳት ከደረሰባቸዉ ተጎጂዎች ዉስጥ ሶስቱ በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንቡላንስ ወደ ጤና ጣቢያ ተወስደዋል ። የእድሳትና የግንባታ ስራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ መሰል አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊዉን የደህንነት መስፈርቶችን አሟልቶና ጠብቆ መስራት አስፈላጊና ግዴታም ጭምር ያለበት በመሆኑ ልዩ ትኩረትም እንዲሰጠዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

@fastmereja
4.9K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 17:32:50
ማኀበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ፍቃድ በጊዜያዊነት ታገደ!!
#FastMereja
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያወጣውን ደብዳቤ ፋስት መረጃ ተመልክቷል በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው «ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ሰበር ዜና በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ውጪ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት ማሰራጨቱ ተረጋግጧል፡፡ ይህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በህገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡

በመሆኑም ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንፃር በቀጣይ በባለሥልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡»

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን
@fastmereja
5.5K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 14:29:06
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ በወረዳ 11 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው የደረሰው በወረዳ 11 አትክልት ተራ አከባቢ ሲሆን የ2 ሰዎች ህይወት አልፈዋል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና መወሰዳቸውን ፋስት መረጃ ከወረዳው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
5.7K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 13:51:39
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አቶ አምሃ ዳኜውን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፣ የፓርቲው መስራች እና ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋ በትናንትና እለት "የአማራ ህዝባዊ ግንባር" የተሰኘ መመስረታቸው ተገልፇል።

@fastmereja
5.4K views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 10:51:11 የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳትና ኪሳራ ማድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ
#FastMereja
በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም ማዕከሉን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳትና ኪሳራ በአገር ላይ መድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ተቋማቸው በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተካሄደው ጦርነት የደረሰውን ጉዳትና የመልሶ ግንባታ ፍላጎት የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት (Damage and Needs Assessment) በማከናወን፣ የጥናት ውጤቱን ለመንግሥት እንዳቀረበ ተናግረዋል።

በጥናት ግኝቱ መሠረትም ያጋጠመው አጠቃላይ ጉዳትና የኢኮኖሚ ኪሳራ በአጠቃላይ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሪፖርታቸው አመላክቷል። ይህም በወቅቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው።
ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ከተቀመጠው መረጃ መረዳት እንደተቻለው፣ ‹‹22 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 20.4 በመቶ የሚገመት ጉዳት›› ደርሷል።

በዚሁ ምክንያት የደረሰው የኢኮኖሚ ኪሳራ ደግሞ፣ ‹‹ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 5.5 በመቶ የሚገመት የኢኮኖሚ ኪሳራ (Economic Loss)›› መድረሱን ሪፖርቱ ያመለክታል።
ግጭትና ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች ከሚገኙ ጠቅላላ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት በጦርነቱ በቀጥታ የተጎዱ መሆናቸውን፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ሦስት ሚሊዮን የሚሆኑት የአገሪቱ ዜጎች በጦርነቱ ምክንያት የከፋ ድህነት ውስጥ መግባታቸውንም አስረድተዋል።

ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት የተቀመጠው የጉዳት መጠን፣ ኢትዮጵያ ባለፉት በርካታ ዓመታት ከውጭ አበዳሪዎች ለኢኮኖሚ ልማት ተበድራ ካልመለሰችው አጠቃላይ የውጭ ዕዳ ጋር እኩል መሆኑን መረዳት ይቻላል። የገንዘብ ሚኒስቴር በየሩብ ዓመቱ ይፋ በሚያደርገው የዕዳ ሁኔታ መግለጫ መሠረት፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያለባት አጠቃላይ የውጭ ዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር ነው።

ዘገባው የሪፖርተር ነው

@fastmereja
5.7K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ