Get Mystery Box with random crypto!

ማኀበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ፍቃድ በጊዜያዊነት ታገደ!! #FastMereja የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃ | FastMereja.com

ማኀበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ፍቃድ በጊዜያዊነት ታገደ!!
#FastMereja
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያወጣውን ደብዳቤ ፋስት መረጃ ተመልክቷል በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው «ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ሰበር ዜና በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ውጪ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት ማሰራጨቱ ተረጋግጧል፡፡ ይህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በህገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ነው፡፡

በመሆኑም ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንፃር በቀጣይ በባለሥልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡»

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን
@fastmereja