Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ፒያሳ በዕድሳት ላይ የነበረ ቤት ተደርምሶ በሰዉ ላይ ጉዳት ደረሰ ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 20 | FastMereja.com

ዛሬ ፒያሳ በዕድሳት ላይ የነበረ ቤት ተደርምሶ በሰዉ ላይ ጉዳት ደረሰ

ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋድ 4 ሰዓት በእድሳት ላይ የነበረ ቤት ተደርምሶ በሰዉ ላይ ጉዳት ደርሷል። በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ ደሀብ ሆቴል አጠገብ በእድሳት ላይ የነበረዉ አንድ ካፌ ተደርምሶ በዚያዉ ስፍራ በመንገድ ላይ ሻይ ከሚሸጡት መካከል 5 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷባቸዋል።

ጉዳት ከደረሰባቸዉ ተጎጂዎች ዉስጥ ሶስቱ በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንቡላንስ ወደ ጤና ጣቢያ ተወስደዋል ። የእድሳትና የግንባታ ስራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ መሰል አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊዉን የደህንነት መስፈርቶችን አሟልቶና ጠብቆ መስራት አስፈላጊና ግዴታም ጭምር ያለበት በመሆኑ ልዩ ትኩረትም እንዲሰጠዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

@fastmereja