Get Mystery Box with random crypto!

በስህተት የተላከላትን 97 ሺህ ብር ለባለቤቱ መለሰች #FastMereja በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደ | FastMereja.com

በስህተት የተላከላትን 97 ሺህ ብር ለባለቤቱ መለሰች
#FastMereja
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አዲስ ቅዳም ከተማ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው እና የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ ብርሃኑ ግንቦት 16/2015 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ነዋሪ የሆነው አቶ ታምራት አለማየሁ ሴዳ የተባለ ግለሰብ በስህተት 97 ሺህ ብር ይልክላታል።

ግለሰቡም በመደናገጥ ብሩን ትመልስለት ዘንድ በስልክ ይደውልላታል። ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ የተላከላትን ገንዘብ ምንም ሳታወላውል ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ቅዳም ቅርንጫፍ በመሄድ የመለሰችለት መሆኑን አብራርታልናለች ሲል ፋግታ ኮሙኔኬሽን ዘግቧል።

ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ አያይዛም ያለፋበትን የሰው ገንዘብ መውሰድና መጠቀም በምድርም በፈጣሪም ያስጠይቃል እኔ ደግሞ የህግ አካል ነኝ ከኔ ማህበረሰቡ ብዙ ይማራል ስትል ገልፃለች።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ቅዳም ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ቻሌ እንየው በበኩላቸው ዋና ሳጅን ይዛኑ ሙጨ የራሷ ያልሆነን ገንዘብ መጠቀም ነውር መሆኑን ስለሚያምኑ እና የተሰማሩበት የሙያ ዘርፍም ስርቆትንና ወንጀልን በጅጉ የሚፀየፍ ተቋም መሆኑን በመረዳት የገባላቸውን 97 ሺህ ብር የእርሳቸው አለመሆኑን በመረዳት ወደ ቅርጫፋችን በመምጣት ገንዘቡን ለባለቤቱ ወዲያውኑ የመለሱለት መሆኑን ገልፀዋል።

@fastmereja