Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-06-11 14:01:28 የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የትምህርት ሚኒስቴርን ውሳኔ ተቋወመ
#FastMereja

የግል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ስለመውጫ ፈተና ከጅምሩ ጀምሮ ሲከታተል እና ተማሪዎችም ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሲያደርግ እና ከነብዙ ችግሮቹ ሲደግፍ ቆይቷል ያለው ህብረቱ ነገር ግን በቀን ግንቦት 23,2015 ዓ.ም፡ በክቡር ሚኒስተር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ ላይ እጅግ ትልቅ ቅሬታ እንዳላቸው ነው የገለፁት።

ተማሪዎች ተምረው ለመመረቅ ውላቸው ካሉበት ዩኒቨርሲቲ ጋር እንጂ ከትምህርት ሚኒስተር ጋር አይደለም ያሉት ተማሪዎቹ በአዋጅ የትምህርት ሚኒስተር ዘንድሮ የመውጫ ፈተና አጸድቋል፣ እኛም ደግፈነዋል! ነገር ግን የምርቃት ዝግጅት እና መውጫ ፈተናን ማያያዝ የተማሪውን እና የወላጅን psychology ያላገናዘበ፣ በዘፈቀደ የተወሰነ irrational decision ነው ብለን ነው ምናምነው ብለዋል። ስለዚህ የትኛውም ተማሪ መብቱን መጠየቅ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል፡፡ የሚመለከትው አካልም ድጋሚ አጢኖ ምላሽ ይሰጠናል ብለን አንጠብቃለን ሲሉ ጠይቀዋል።

ሃገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረትም ይህ ውሳኔ ሲወስን እንደተወያየ ይፋ ተደርጓል፡፡ ነግር ግን የግል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረቶች ሳያውቁት ይህ አይነት ውሳኔ መወሰኑ እንዲሁም የብዙ ተማሪዎችን ህልም እና ተስፋ የሚያጨልም ሆኖ ሳለ ተስማምተው መምጣታቸው እጅግ አሳዝኖናል ብለዋል።

@fastmereja
7.6K views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 11:49:57
በትግራይ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ የተመራ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ ባሕር ዳር ገብቷል።

@fastmereja
7.2K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 10:56:06
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 510 ሚሊዮን ብር በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አስረከቡ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት ከድጋፉ ውስጥ የምግብ እቃዎች፣ አልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁስና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና 218 ሚሊየን በጥሬ ገንዘብ አቶ ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል።

@fastmereja
7.2K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:02:56 በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር ውይይት ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ወር ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
ባካሔደው የርክበ ካህናት ጉባኤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ቀደም ሲል በቋሚ ሲኖዶስ በተሰየመው የልዑካን ቡድን አማካኝነት በአስቸኳይ እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ኮሚቴው ውይይቱን በተሳካ ሁኔታ ለማካሔድ የሚያስችለውን በእቅድ ላይ የተመሰረተ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውይይቱ በተሳካ ሆኔታ መካሔድ የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያመቻች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተጻፈ ደብዳቤ ጥያቄውን አቅርቧል።የልዑካን ቡድኑ አባላትም ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተጻፈውን ደብዳቤ በአካል በመገኘት ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በማቅረብ ከሚመለከታቸው የክልሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የክልሉ ጊዚያዊ መንግስት ለውይይቱ መሳካት በሚያደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ተመልሷል።

ስለሆነም ለክልሉ መንግስት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ሁለቱም አካላት በሚያመቻቹት ጊዜና ቦታ ውይይቱ የሚካሔድ ይሆናል።

በዚህም መሰረት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካን ቡድን ውይይቱን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ እስከ አሁን ያከናወናቸውን ተግባራትና ወደፊት ውይይቱን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማካሔድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሰኞ ሰኔ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል።መግለጫውን ተከትሎም ጉዳዩ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባት በሒደቱ የሚመዘገቡ ለውጦችን ሁሉ በመገናኛ ብዙሃን የሚያሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሕዝቅ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

@fastmereja
8.1K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 15:45:34 ትረፊ ያላት ነብስ አውሮፕላን ተከስክሶ ተርፈው፣ አደገኛው ጫካ ውስጥ 40 ቀን የቆዩት ህፃናት ጉዳይ እያነጋገረ ነው
#FastMereja
ተሳፍረውበት የነበረው አውሮፕላን በኮሎምቢያ አማዞን ጫካ ውስጥ ተከስክሶ ከአንድ ወር በላይ ጠፍተው የቆዩት አራት ሕጻናት በሕይወት ተገኙ።

ለ40 ቀናት ያህል ጠፍተው የነበሩት የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ የ13፣ የዘጠኝ፣ የአራት እና የአንድ ዓመት ልጆች ናቸው።

አውሮፕላኑን የተሳፈሩት ከእናታቸው ጋር ሲሆን እአአ በግንቦት 1 ነበር የተከሰከሰው።

እናታቸው እንዲሁም አብራሪውና አጋር አብራሪው በአደጋው ምክንያት ሞተዋል።

የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ጉዝታቮ ፔትሮ እንዳሉት ልጆቹ ለሳምንታት ከተፈለጉ በኋላ መገኘታቸው መላ አገሪቱን ያስደሰተ ነው።

“ተዓምራዊ ቀን ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ብቻቸውን ነበሩ። ራሳቸውን በሕይወት ያቆዩት በራሳቸው ጥረት ነው። ታሪክ ይዘክራቸዋል” ሲሉም አክለዋል።

“እነዚህ ልጆች የሰላም ልጆች ናቸው። የኮሎምቢያ ልጆች ናቸው” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

የአገሪቱ ወታደሮችና ቀደምት ማኅበረሰቦች ልጆቹን ለማዳን ሲረባረቡ የሚያሳዩ ፎቶዎች ወጥተዋል።

ልጆቹ ለ40 ቀናት ጠፍተው ነበር። ሕክምናም እየተሰጣቸው ነው።

ፕሬዝዳንቱ ከልጆቹ አያት ጋር መነጋገራቸውንና አያትየው የልጅ ልጆቻቸውን “እናት የሆነችው ደን እንደመለሰቻቸው” መናገራቸው ተገልጿል።

ወደ መዲናዋ ቦጎታ ሲወሰዱ አምቡላንስ እየጠበቃቸው ነበር።

ሴስና የበረራ ቁጥር 206 ከአማዞን፣ አራራኩራ ተነስቶ ወደ ሳን ሆሴ ዴል ጉዋቫሪ እየተጓዘ ሳለ ነው የሞተር ችግር የገጠመነው።

በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡት ሦስት ሰዎች አስክሬን አውሮፕላኑ የተከሰከሰበት ቦታ ተገኝቷል።

ከሲቪል አቪዬሽን የወጣው ቅድመ መረጃ እንደሚጠቁመው፣ ሕጻናቱ ከአደጋው ተርፈው ጫካ ውስጥ ሲኳትኑ ከርመው ነው የተገኙት።

ፍለጋው ከተጀመረ ሳምንታት ተቆጥሯል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ልጆቹ ጥለዋቸው የሄዱ እቃዎች እያገኙ ነበር።

የውሃ ጠርሙስ፣ መቀስ፣ ፀጉር ማስያዣ እና ጊዜያዊ መጠለያ ተገኝተዋል።

ትንንሽ የእግር ዱካዎችም መገኘታቸው ተገልጿል።

እነዚህን መነሻ አድርገው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ልጆቹ በሕይወት እንዳሉ አውቀው ፍለጋው ተካሂዷል።

ጫካ ውስጥ ጃጓር፣ እባብና ሌሎችም እንስሳት ይገኛሉ።

ልጆቹ ሆቶቶ የተባለ ቀደም ማኅበረሰብ አባላት ናቸው።

ማኅበረሰቡ እንደሚለው ልጆቹ በሕይወት እንዲገኙ የረዳቸው ስለ ፍራፍሬ ያላቸው ዕውቀትና ጫካ ውስጥ ራስን የማዳን ክህሎታቸው ነው።

ቀደምት ማኅበረሰቦችም ልጆችን ሲፈልጉ ቆይተዋል። በሄሊኮፕተር የሴት አያቸው ድምጽ ሲተላለፍም ነበር።

በሆቶቶ ቋንቋ ልጆቹ በቀላሉ እንዲገኙ አንድ ቦታ እንዲቆዩ ነበር አያትየው ተናግረው የነበረው።

ባለፈው ወር ልጆቹ መገኘታቸውን ፕሬዝዳንቱ ትዊት አድርገው መረጃው ስህተት ነው የሚል ትችት ተሰንዝሮባቸው ቆይተው ኋላ ላይ ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የተሰጠው መረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው

@fastmereja
8.1K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 15:45:30
7.1K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 14:19:46
ባልታወቁ ሰዎች በመኖሪያ ቤቱ የተገደለው የአደዓ በርጋ ም/አስተዳዳሪ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ
#FastMereja
ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓም በቤካቲ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች የተገደሉት የአዳአ በርጋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብዲሳ ቀነኒ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ሰኔ 3/2015 ዓም በትውልድ ቦታቸው የስራ ባልደረቦቻቸው፣ ወዳጅ፣ ዘመድ በተገኙበት ተፈፅሟል።

@fastmereja
7.5K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 11:20:22
አምቡላንስ ላይ በተከፈተ ተኩስ የሰው ህይወት አለፈ
#FastMereja
አቶ ገመቹ ጀቤሣ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ  አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ  ሆስፒታል  ጤና ባለሙያ ሲሆኑ ትናንት (02/10/2015 ዓ.ም) ከአዲስ አበባ  ወደ ደምቢዶሎ በመመለስ  ላይ እያሉ እናንጎ አከባቢ በአምቡላንስ ላይ በተከፈተው  ተኩስ ሕይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ ፋስት መረጃ ከዩኒቨርሲቲው የሀዘን መግለጫ ተመልክቷል።

@fastmereja
8.3K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 11:03:48 ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ በማዕከላዊ ሲስተሙ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ገለፀ።
#FastMereja
ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ሰኔ 3/2015 ዓም በማዕከላዊ ሲስተሙ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ገለፀ። በተወሰኑ አካባቢዎች የዳታ እና የድምጽ አገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ችግሩ የተፈታና አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ የተመለሰ መሆኑን እየገለጽን፤ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።

@fastmereja
8.0K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 18:15:31 የታገቱ 28 የመንግስት ሠራተኞች ዛሬም የደረሱበት አይታወቅም

ከምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ወደ ሳሲጋ ወረዳ ሲያቀኑ ባለፈው ዓመት ጥቅምት 18 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ከመንገድ በታጣቂዎች የታገቱ 28 የመንግስት ሠራተኞች ከዓመት ከመንፈቅ በኋላም ደብዛቸው ጠፍቶ መቅረቱን የታጋቾቹ ቤተሰቦች ለዶቼቬለ ተናገሩ ። የአራት ልጆት እናት መሆናቸውን እና ባለፈው ዓመት ባለቤታቸው እንደታገቱባቸው የተናገሩ አንዲት የነቀምቴ ከተማ ነዋሪ ከወረዳ እስከ ዞን አስተዳደር አቤት ቢሉም እስካሁን ምንም መፍትሄ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል ።

«ጥቅምት 18 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ለሥራ በጠዋት እየሄዱ ነበር ። ከባለቤተ ጋር የሄዱ ሌሎች ሰዎች 3 ሰዓት አካባቢ ተመለሱ ። በመንገድ ላይ የታጠቁ ሰዎች የመንገሥት ሠራተኞችን ለይተው ለይተው ማስቀረታቸውን ሌሎችን ደግሞ ወደቤታቹ ሂዱ ብለው እንደመለሷቸው ነገሩን ። በዕለቱ ነው እንግዲህ ታግተው የተወሰዱ ስልክም አልደወሉም በዛው ነው የቀሩት ። ምንም የፖለቲካ ተሳትፎ ያልነበረው የግብርና ባለሞያ ነበር ። አራት ልጆች አሉን አሁን ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል» ብለዋል።
ዘገባው የዶቼ ቬለ ነው።

@fastmereja
4.9K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ