Get Mystery Box with random crypto!

የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የትምህርት ሚኒስቴርን ውሳኔ ተቋወመ #FastMereja የግል | FastMereja.com

የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የትምህርት ሚኒስቴርን ውሳኔ ተቋወመ
#FastMereja

የግል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ስለመውጫ ፈተና ከጅምሩ ጀምሮ ሲከታተል እና ተማሪዎችም ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሲያደርግ እና ከነብዙ ችግሮቹ ሲደግፍ ቆይቷል ያለው ህብረቱ ነገር ግን በቀን ግንቦት 23,2015 ዓ.ም፡ በክቡር ሚኒስተር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ ላይ እጅግ ትልቅ ቅሬታ እንዳላቸው ነው የገለፁት።

ተማሪዎች ተምረው ለመመረቅ ውላቸው ካሉበት ዩኒቨርሲቲ ጋር እንጂ ከትምህርት ሚኒስተር ጋር አይደለም ያሉት ተማሪዎቹ በአዋጅ የትምህርት ሚኒስተር ዘንድሮ የመውጫ ፈተና አጸድቋል፣ እኛም ደግፈነዋል! ነገር ግን የምርቃት ዝግጅት እና መውጫ ፈተናን ማያያዝ የተማሪውን እና የወላጅን psychology ያላገናዘበ፣ በዘፈቀደ የተወሰነ irrational decision ነው ብለን ነው ምናምነው ብለዋል። ስለዚህ የትኛውም ተማሪ መብቱን መጠየቅ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል፡፡ የሚመለከትው አካልም ድጋሚ አጢኖ ምላሽ ይሰጠናል ብለን አንጠብቃለን ሲሉ ጠይቀዋል።

ሃገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረትም ይህ ውሳኔ ሲወስን እንደተወያየ ይፋ ተደርጓል፡፡ ነግር ግን የግል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረቶች ሳያውቁት ይህ አይነት ውሳኔ መወሰኑ እንዲሁም የብዙ ተማሪዎችን ህልም እና ተስፋ የሚያጨልም ሆኖ ሳለ ተስማምተው መምጣታቸው እጅግ አሳዝኖናል ብለዋል።

@fastmereja