Get Mystery Box with random crypto!

የታገቱ 28 የመንግስት ሠራተኞች ዛሬም የደረሱበት አይታወቅም ከምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ወደ | FastMereja.com

የታገቱ 28 የመንግስት ሠራተኞች ዛሬም የደረሱበት አይታወቅም

ከምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ወደ ሳሲጋ ወረዳ ሲያቀኑ ባለፈው ዓመት ጥቅምት 18 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ከመንገድ በታጣቂዎች የታገቱ 28 የመንግስት ሠራተኞች ከዓመት ከመንፈቅ በኋላም ደብዛቸው ጠፍቶ መቅረቱን የታጋቾቹ ቤተሰቦች ለዶቼቬለ ተናገሩ ። የአራት ልጆት እናት መሆናቸውን እና ባለፈው ዓመት ባለቤታቸው እንደታገቱባቸው የተናገሩ አንዲት የነቀምቴ ከተማ ነዋሪ ከወረዳ እስከ ዞን አስተዳደር አቤት ቢሉም እስካሁን ምንም መፍትሄ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል ።

«ጥቅምት 18 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ለሥራ በጠዋት እየሄዱ ነበር ። ከባለቤተ ጋር የሄዱ ሌሎች ሰዎች 3 ሰዓት አካባቢ ተመለሱ ። በመንገድ ላይ የታጠቁ ሰዎች የመንገሥት ሠራተኞችን ለይተው ለይተው ማስቀረታቸውን ሌሎችን ደግሞ ወደቤታቹ ሂዱ ብለው እንደመለሷቸው ነገሩን ። በዕለቱ ነው እንግዲህ ታግተው የተወሰዱ ስልክም አልደወሉም በዛው ነው የቀሩት ። ምንም የፖለቲካ ተሳትፎ ያልነበረው የግብርና ባለሞያ ነበር ። አራት ልጆች አሉን አሁን ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል» ብለዋል።
ዘገባው የዶቼ ቬለ ነው።

@fastmereja