Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.72K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-17 17:26:45
"ዛሬ በአዲስ አበባ ያስጀመርነው የቤተመንግስት ግንባታ የኦሮሞ ህዝብ የትግል ፍሬ ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ" ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ

"የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ቤተመንግስት ገንቡልኝ አይደለም! ወጥቶ መግባት ለከበደው ኑሩ ለከበደው ህዝብ በአዲስ አበባ ቤተመንግስት ገንብቻለሁ አጨብጭብ ማለት ለህዝብ ንቀት ይመስላል" አቶ ታዬ ደንደዓ

@fastmereja
7.3K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:26:14
በአዲስ አበባ ቦሌ የሚገነባው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቤተ መንግስት ዲዛይን።

@fastmereja
6.8K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 21:59:16
ህወሓት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን አስመልክቶ ያስተላለፈው ውሳኔ የሰለም ስምምነቱን ትግበራ ባለቤት አልባ የሚያደርግ ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል
#FastMereja
"የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት የማይቀበል፣ እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ያለውን የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ባለቤት አልባ የሚያደርግ፣ ከጦርነቱ ወደ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ለሚገቡ ሃይሎች መደገፍ እና ማበረታታት ሲገባ ድርጅቶችን በማፍረስ ቀጣይ ሰላም እንዳይረጋገጥ የሚያደርግ መሆኑ፣ ለህዝቦቻችን የማይመች እና ለሌሎች ሃይሎችም ተስፋ የማይሰጥ ነው ብሎ ድርጅታችን ህወሓት ያምናል።" ብሎዋል።

ሙሉ መግለጫው ተያይዟል

@fastmereja
8.3K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 15:50:06 በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ህይወታቸው አለፈ
#FastMereja
በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡

ታዲያ በዕለተ እሁድ ከሩቁ ከቅርብ የተጠራው ቤተዘመዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሙሽራው መምጫ ሰዓት ደረሰ ሙሽራው ከነሚዜወቹ ደረሱ የሙሽሪት ቤተሰቦች በጣም ደስ አላቸው እልልታውን አቀለጡት ሙሽራው ሙሽሪትን በቤተሰብ አስመርቆ ወደቤቱ ሊመለስ ሲል ሞቅ ያለ ጭፈራ ሆታ ተነሳ በጭፈራው መሃል ቅልጥ ያለ የጥይት ተኩስም ተተኮሰ በድንገት ጭፈራ ሲጨፈር የነበረው ሰው ፀጥ አለ በጭፈራው መሃል በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ያልፋል፣ አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰወች በድምሩ አምስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በተደረገላቸው ህክምና ህይወታቸው መትረፉን የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረ/ኢ/ር ተመስገን ሙሉነህ ተናግረዋለወ። የወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል። መረጃው የምዕ/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

@fastmereja
10.1K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 14:42:34
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ተፈፀመ

የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት ተፈፅሟል። ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ በአለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።

ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት እንደነበረች የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው የዘገበው።

@fastmereja
9.1K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 13:12:46 በትግራይ ክልል የሕዝብ አምቡላንሶች ላልተገባ አገልግሎት እየዋሉ እንደሆነ ነዋሪዎች ተናገሩ። አስተያየት ሰጪዎቹ ለዶይቼ ቨለ እንዳሉት ከጦርነቱ ውድመትና ዝርፊያ የቀሩት አምቡላንሶች ወላድንና ሕሙማንን ወደ ሆስፒታል ከመውሰድ ይልቅ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ለግልና ለድርጅት ሥራ ሲጠቀሙባቸው ማየት እጅግ ይዘገንናል ብለዋል።

አቶ ሐዱሽ ካሕሳይ የመቐለ ከተማ ነዋሪ ናቸው። እሳቸው ለDW በሰጡት አስተያየት "የህዝብ መገልገያ አምቡላንሶች በየመጠጥ ቤቱ ቆመው የወረዳ ባለስልጣናት የሚዝናኑበባቸው መሆኑን ከማየት የከፋ ንቅዘት በህይወቴ አይቼ አላውቅም" ሲሉ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

ወጣት አጀቡ ገብረመስቀል የተባለች ሌላዋ የመቐለ ከተማ ነዋሪ "የሐብት እጥረት ባለበት ክልል እንዲህ አይነት አባካኝ አጠቃቀም ተገቢ አይደለም፤ የአቶ ጌታቸው ረዳ አስተዳደር በአስቸኳይ እነዚህ በየመጠጥ ቤቱ ተገትረው የሚያድሩ አምቡላንሶችን ሰብስበው ወደ ሕዝብ አገልግሎት እንዲመልሷቸው እንፈልጋልን" ስትል አስተያየትዋን ገልጻለች።

የህወሀት ባለስልጣናት አምቡላንሶችን በየመጠጥ ቤቱ ጭምር አቁመው ሲዝናኑ የሚያሳዩ ምስሎች በማሕበራዊ ድረገጻች እየተሰራጩ መነጋገሪያ ርእስ ሆነዋል ሲል ዶይቼ ቬለ ነው የዘገበው።

@fastmereja
8.0K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 13:06:35
በፖሊስ ስትፈለግ የቆየችው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች፡፡
#FastMereja
በምዕራብ ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ በተለምዶው ሚካዔል ቁጥር 1 (150 ሰፈር) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወረቀት አደመ አመራ የተባለች ግለሰብ ግንቦት 02/2015 ዓ.ም እንደጠፋች ከሟች ዘመድ ለፖሊስ ጥቆማ ይደረሳል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ግንቦት 06/2015 ዓ.ም በቤቷ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተቀብራ ተገኝታለች፡፡

የሟች አስከሬን ቤተሰቦቿ ፤በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ አባላት ተቆፍሮ ወጥቶ መርዓዊ ከተማ የመጀመሪያ ሆስፒታል ምርመራ የተደረገ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል አስታውቋል ሲል ከመርዓዊ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
6.9K views10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 13:05:54
በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በተደረገ የሂሳብና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ውድድር የኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 1ኛ እና 2ኛ መውጣታቸውን የኦሮሚያ ልማት ማኀበር ገለፀ።
#FastMereja
በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፉት የኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ተማሪዎች ውድድሩን አሸንፏል። ውድድሩን አንደኛ በመውጣት በበላይነት ያጠናቀቀችው ተማሪ ሙፈሪያት ታደሰ ስትሆን ሁለተኛ ተማሪ ፊጣ አለማየሁ ሆኗል።
1ኛ ለወጣ 50ሺ ብር 2ኛ ለወጣ 30ሺ ብር 3ኛ ለወጣ 20ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል። ከ4ኛ እስከ 16ኛ ለወጡ ተማሪዎች 10ሺ ብር ተበርክቷል።

@fastmereja
6.6K views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 13:31:58
7.9K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 13:31:58 የ22 ዓመቱ ማሌዥያዊ የ48 ዓመቷን የቀድሞ መምህሩን አግብቷል

የቋንቋ መምህሩ ለተማሪዎች የምታሳየው ፍቅር የማረከው ወጣት “እድሜ ቁጥር ብቻ ነው” ብሎ ከብዙ ድካም በኋላ ምኞቱን ማሳካቱን ገልጿል። የ26 ዓመት የእድሜ ልዩነት ያልገደባቸው ተማሪና የቀድሞ መምህሩ በቅርቡ ተሞሽረዋል።

ሙሃመድ ዳኔል አህመድ አሊ በፈረንጆቹ 2016 የማሌዥያ ቋንቋ አስተማሪውን ጀሚላህ ሞህድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከት የ15 አመት ታዳጊ ነበር።
በወቅቱ ምንም የተለየ የፍቅር ስሜት እንዳልተሰማው የሚያነሳው ሙሀመድ ዳኔል፥ ታዳጊም ቢሆን ጀሚላ ለተማሪዎች የምታሳየው ፍቅርና እንክብካቤ እየረሳኝም ይላል።

ከክፍል ክፍል ሲዛወር የቋንቋ አስተማሪውን ያጣው ሙሃመድ፥ በ2017 በአጋጣሚ ወደ መምህራን ቢሮ ሲያመራ ጀሚላን ያገኛትና ሰላምታ ሰጥቶ ያልፋል።

ከዚህ በኋላ ስለጀሚላ ማሰብ ማንሰላሰል ጀመርኩ የሚለው ሙሀመድ፥ የልደት መልካም ምኞት ከጀሚላ ሲደርሰው ነገሮች ሁሉ በፍጥነት መልካቸውን መቀየራቸውን ያስታውሳል።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክቱ የተጀመረው ንግግርም እያደገ ሄዶ የታዳጊነት ስሜቱን ሳይደብቅ በ26 አመት ለምትበልጠው የቀድሞ መምህሩ የፍቅር ጥያቄ ማቅረቡን ለማሌዥያው ኒው ስትሬት ታይምስ ይናገራል።
ጀሚላም የእድሜ ልዩነታቸውን በመጥቀስ በፍጹም የማይሆን ነገር ነው የሚል ምላሽ ትሰጣለች።

“አድራሻዋን አላውቅም ነበር፤ እድል ቤቷ ድረስ ወሰደኝ” የሚለው ሙሀመድ፥ ቤት ውስጥ ሁሉንም ነገር በግልጽነት እንዳወሩም ነው የሚገልጸው።
ያም ሆኖ ጀሚላ በአቋሟ መጽናቷን ተከትሎ ወጣቱ ሙሀመድ ለረጅም ጊዜ መወትወቱንና ለማሳመን መጣሩን ይገፋበታል።

መምህርት ጀሚላ የቀድሞ ተማሪዋ ወይ ፍንክች የአባ ቢለዋ ልጅ ማለቱን ስትመለከት ከሁሉ ነገር ቀድሞ የሚመጣው የእድሜ ልዩነታቸው ጉዳይ እየደበዘዘ ይሄዳል።

“ወደኔ ሲመጣ በሙሉ መተማመን ነው፤ ለቤተሰቦቹም ሲያሳውቅ አላፈረም፤ ይህ ይበልጥ እንድተማመንበት አድርጎኛል” የምትለው ጀሚላ፥ ለጉዳዩ የሰጠው ትኩረት አቋሟን እንድለውጥ እንዳደረጋትም ትናገራለች።
እናም ለቤተሰቦቻቸው አሳውቀው ጋብቻቸውን ለመፈጸም መስማማታቸውን ታስታውሳለች።

በ2021 በጋብቻ ለመጣመር የያዙት እቅድም በኮሮና ምክንያት ተራዝሞ ከሰሞኑ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው በተገኙበት በመጠነኛ ሰርግ ተሞሽረው የማሌዥያ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስበው ሰንብተዋል።
“እድሜ ቁጥር ብቻ ነው፤ እንደ ባል የሚጣልብኝን ሃላፊነት ለመወጣት ተዘጋጅቻለሁ” ብሏል የ22 አመቱ ወጣት።

በፈረንጆቹ 2007 የመጀመሪያ ባሏን የፈታችው ጀሚላም ስራዋ ላይ ትኩረት አድርጋ ለወንዶች ሁሉ ዘግታው የነበረውን ልቧን ለባለቤቷ ሙሀመድ ዳኔል ክፍት ማድረጓን መናገሯ ተዘግቧል።

ዘገባው የዐል ዐይን ነው።

@fastmereja
7.7K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ