Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በተደረገ የሂሳ | FastMereja.com

በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በተደረገ የሂሳብና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ውድድር የኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 1ኛ እና 2ኛ መውጣታቸውን የኦሮሚያ ልማት ማኀበር ገለፀ።
#FastMereja
በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፉት የኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት አዳማ ቅርንጫፍ ተማሪዎች ውድድሩን አሸንፏል። ውድድሩን አንደኛ በመውጣት በበላይነት ያጠናቀቀችው ተማሪ ሙፈሪያት ታደሰ ስትሆን ሁለተኛ ተማሪ ፊጣ አለማየሁ ሆኗል።
1ኛ ለወጣ 50ሺ ብር 2ኛ ለወጣ 30ሺ ብር 3ኛ ለወጣ 20ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል። ከ4ኛ እስከ 16ኛ ለወጡ ተማሪዎች 10ሺ ብር ተበርክቷል።

@fastmereja