Get Mystery Box with random crypto!

በፖሊስ ስትፈለግ የቆየችው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች፡፡ | FastMereja.com

በፖሊስ ስትፈለግ የቆየችው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች፡፡
#FastMereja
በምዕራብ ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ በተለምዶው ሚካዔል ቁጥር 1 (150 ሰፈር) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወረቀት አደመ አመራ የተባለች ግለሰብ ግንቦት 02/2015 ዓ.ም እንደጠፋች ከሟች ዘመድ ለፖሊስ ጥቆማ ይደረሳል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ግንቦት 06/2015 ዓ.ም በቤቷ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተቀብራ ተገኝታለች፡፡

የሟች አስከሬን ቤተሰቦቿ ፤በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ አባላት ተቆፍሮ ወጥቶ መርዓዊ ከተማ የመጀመሪያ ሆስፒታል ምርመራ የተደረገ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል አስታውቋል ሲል ከመርዓዊ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja