Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የሕዝብ አምቡላንሶች ላልተገባ አገልግሎት እየዋሉ እንደሆነ ነዋሪዎች ተናገሩ። አስተ | FastMereja.com

በትግራይ ክልል የሕዝብ አምቡላንሶች ላልተገባ አገልግሎት እየዋሉ እንደሆነ ነዋሪዎች ተናገሩ። አስተያየት ሰጪዎቹ ለዶይቼ ቨለ እንዳሉት ከጦርነቱ ውድመትና ዝርፊያ የቀሩት አምቡላንሶች ወላድንና ሕሙማንን ወደ ሆስፒታል ከመውሰድ ይልቅ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ለግልና ለድርጅት ሥራ ሲጠቀሙባቸው ማየት እጅግ ይዘገንናል ብለዋል።

አቶ ሐዱሽ ካሕሳይ የመቐለ ከተማ ነዋሪ ናቸው። እሳቸው ለDW በሰጡት አስተያየት "የህዝብ መገልገያ አምቡላንሶች በየመጠጥ ቤቱ ቆመው የወረዳ ባለስልጣናት የሚዝናኑበባቸው መሆኑን ከማየት የከፋ ንቅዘት በህይወቴ አይቼ አላውቅም" ሲሉ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

ወጣት አጀቡ ገብረመስቀል የተባለች ሌላዋ የመቐለ ከተማ ነዋሪ "የሐብት እጥረት ባለበት ክልል እንዲህ አይነት አባካኝ አጠቃቀም ተገቢ አይደለም፤ የአቶ ጌታቸው ረዳ አስተዳደር በአስቸኳይ እነዚህ በየመጠጥ ቤቱ ተገትረው የሚያድሩ አምቡላንሶችን ሰብስበው ወደ ሕዝብ አገልግሎት እንዲመልሷቸው እንፈልጋልን" ስትል አስተያየትዋን ገልጻለች።

የህወሀት ባለስልጣናት አምቡላንሶችን በየመጠጥ ቤቱ ጭምር አቁመው ሲዝናኑ የሚያሳዩ ምስሎች በማሕበራዊ ድረገጻች እየተሰራጩ መነጋገሪያ ርእስ ሆነዋል ሲል ዶይቼ ቬለ ነው የዘገበው።

@fastmereja