Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-05-12 14:54:47
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኜ በዛሬው ዕለት በቢሮ ስራ ላይ እያሉ ከአንድ ተገልጋይ በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል።

ጥቃት ያደረሰው ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ተገቢውን ሂደት ተከትሎ ተጠያቂነት የማስፈን ስራ የሚሰራ ይሆናል ሲል የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ዘግበዋል።

@fastmereja
3.7K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 19:49:50 በሞዛምቢክ የሌላ ሰው መራቢያ አካል ይዞ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ተጠርጣሪ ተያዘ

በአፍሪካዊቷ ሞዛምቢክ አንድ ግለሰብ በፕላስቲክ ውስጥ የሰው ልጅ ጭንቅላት እና የወንድ ሰው መራቢያ አካል ይዞ ሲንቀሳቀስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ውስጥ በምትገኘው ናማታንዳ ከተማ ጎዳናዎች ላይ የነበሩ ህጻናት አንድ ግለሰብ የሰው ልጅ ጭንቅላት እና የወንድ መራቢያ አካል በፕላስቲክ ውስጥ አድርጎ ሲጓዝ በማየታቸው ጉዳዩን ለፖሊስ መጠቆማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፖሊስም በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ባደረገው ማጣራት ግለሰቡ ሰውን በመግደል የሰውነት ክፍሉን በመቁረጥ ይዞ በመጓዝ ላይ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ ምርመራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን ተጠርጣሪው የያዛቸውን የሰውነት አካሎች ለመሸጥ ማሰቡ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ተጠርጣሪው ለፖሊስ ከዚህ በፊት ሶስት ሰዎችን እንደገደለ ማረጋገጡ የተነገረ ሲሆን የሰውነት ክፍላቸውንም እንደሸጠ ተገልጿል፡፡

የተገደሉ የሰውነት ክፍሎችን ማን እንደሚገዛ እና ስለ ግድያዎቹ አመቻቾች ተጨማሪ ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑን የግዛቲቱ ፖሊስ ቃል አቀባይ ተናግሯል ተብሏል፡፡

በሞዛምቢክ የሞቱ ሰዎች የሰውነት አካልን መጠቀም ጽኑ ህመሞችን ይፈውሳል፣ ረጅም ጊዜ በህይወት ለመኖር ያግዛል እና ሌሎች በረከቶችን ያስገኛል የሚል ዕምነት እንዳለ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ዘገባው የአል አይን ነው!

@fastmereja
6.0K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:56:52
ከጤፍ ዱቄት ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮችንና የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ) በመቀላቀል ለህብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦችን በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ህገ-ወጥ ተግባሩ ሲፈፀም የነበረው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አጠራሩ ቆሼ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መጋዘን ውስጥ ነው።

በመጋዘኑ ውስጥ 47 ኩንታል ምንነታቸው ያልታወቀ ስራ ስርና የእንጨት ፍቅፋቂ ሰጋ ቱራ 167 ኩንታል የጤፍ ዱቄት ተከማችቶ የተገኘ ሲሆን ባዕድ ነገሩን ከዱቄቱ ጋር የሚደባልቅ መጋዘኑ ውስጥ እንዳይወጣ የተቆለፈበት ሠራተኛ በፍተሻ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል ። ከአካባቢው ማህበረሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የጅማ በር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በህግ አግባብ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በስራ ላይ የነበረውን ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎ ባደረግው ተጨማሪ ምርመራ የንብረቱን ባለቤትን አፈላልጎ በመያዝ ተገቢው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል ።

በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩትን ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ህብረተሰቡ ሲመለከት ለፖሊስ አጋልጦ በመስጠት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

@fastmereja
6.3K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:25:30 #ማስጠንቀቂያ
የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች የኢትዮጵ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ ተመርተው እየቀረቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል፡፡

91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ምርቶቹ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የመጠቀሚያ ጊዜ፣የአምራች ድርጅታቸው ስም ፣አስገዳጅ ደረጃ ምልክት፣መለያ ቁጥርም ሆነ አድራሻቸው ምርቱ ላይ የልተገለጸና የሌላቸው ሲሆን ምርቱ ሊይዛቸው የሚገቡ ንጥረ ነገሮች በውል ለማይታወቅ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ የሌላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

ለጥንቃቄ የምርቱ ዓይነትና የተገኙትን ክፍተቶች ከዚህ ዜና ጋር አባሪ የተደረጉ ፎቶችን ህብረተሰባችን በትኩረት ተመልክቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ይጠይቃል፡፡

46፤ ዓይነት አይኦዳይዝድ ጨው
27፤ ዓይነት የምግብ ዘይት
10፤ ዓይነት ከረሜላ
5፤ ዓይነት አቼቶ
2፤ ዓይነት የለውዝ ቅቤ
1፤ ዓይነት የቫኔላ ፍሌቨር ምርቶችን

የምርት ዓይነቶች እና ብራንድ ስማቸው

የምግብ ጨዉ
1. ሳባ የገበታ ጨው(Saba IODIZED Salt)
2. ንጋት የገበታ ጨው(Nigat IODIZED SALT)
3. አዲስ ብርሃን የገበታ ጨው ADDIS BERHAN IODIZED SALT
4. ሙና የገበታ ጨው(MUNA TABLE SALT)
5. ቤዝ የገበታ ጨው/BASE IODIZED SALT
6. ጉስቶ የገበታ ጨው/GUSTO IODIZED SALT
7. ማክ የገበታ ጨው/MAK IODIZED SALT
8. አባይ የገበታ ጨው/ABAY TABLE SALT
9. መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFINED & IODIZED SALT
10. መነስ ጨው /MENES IODIZED SALT
11. ሙሉ የገበታ ጨው /Mulu Table Salt
12. ኢርኮ አዮዳይዝድ ጨው ERKO IODIZED SALT
13. አርዲ የገበታ ጨው/ARDI IODIZED SALT
14. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
15. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
16. ጨረቃ የገበታ ጨው/IODIZED SALT
17. ፋና የገበታጨው/Fana Table Salt
18. ዳናት የገበታጨው
19. ሶም የገበታጨው/som iodized salt
20. ጉግሳ በአዮዲን የበለፀገ የገበታጨው/GUGSA Iodised Salt
21. ሸጋ ጨው/SHEGA Iodized SALT
22. ፍዳክ የገበታ ጨው/FDAK IODIZED SALT
23. ኡሚ የገበታ ጨው/UMI IODIZED SALT
24. ጊዜ አዮዳይዝድ ጨው/GIZE IODIZED SALT
25. ባማክ የገበታ ጨው/bamak Iodized Salt
26. ማዚ የገበታ ጨዉ/MAZI IODIZED SALT
27. አዲስ የገበታ ጨዉ/ADDIS Iodized Salt
28. የገበታ ጨው/Iodized salt
29. TANA TABLE SALT/ጣና የገበታ ጨው
30. ጣና የገበታ ጨው
31. ማኢዳ የገበታ ጨው/MAEEDA IODIZED SALT
32. አሚን ጨው/Amin iodized salt
33. ሆም የገበታ ጨው/HOME IODIZED SALT
34. ጂኤም የገበታ ጨው/GM IODIZED SALT
35. ገዳ አዮዳይዝድ የታጠበ የገበታ ጨው/ GEDA IODIZED SALT
36. ዛማ አዮዳይዝድ የታጠበ ባለ አዮዲን ጨው /ZAMA SALT
37. ሶሲ የአዮዲን ጨው/Sosi Iodized Salt
38. ብቁ የገበታ ጨው/Biku iodized salt
39. H.T.F TABLE SALT /ኤች.ቲ.ኤፍ
40. AFRAN Iodized Salt
41. ኤምሬት ጨው/Emirate IODIZED SALT
42. ስፔሻል የገበታ ጨው/Special Iodized Salt
43. ሊያ የገበታ ጨው/ LIYA IODIZED SALT
44. አፊ ጨው/AFI IODIZED SALT
45. ዩስራ ጨው/ YUSERA SALT
46. ቡዜ የገበታጨው/BUZE IODIZED SALT

የምግብ ዘይት
1. ነጃ ንጹህ የምግብ ዘይት/ NEJA Pure Edible Oil
2. ረና ንጹህ የምግብ ዘይት/ Rina Edible Pure Food Oil
3. የኛ ንጹህ የምግብ ዘይት/Yegna Pure Edible Oil
4. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት /Nura Pure Edible oil
5. ሕይወት ንጹህ የምግብ ዘይት /HIWOT Edible Cooking Oil
6. ሚድ ንጹህ የምግብ ዘይት /MID Pure Edible Oil
7. ጉና ንጹህ የኑግ የምግብ ዘይት/GUNA Pure Niger Edible Oil
8. አዲስ ንጹህ የምግብ ዘይት
9. ኑር ንጹህ የምግብ ዘይት/Nur Pure Edible Oil
10. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት/NuraPure Edible Oil
11. ሶፊ ንጹህ የምግብ ዘይት/Sofi Pure Edible Oil
12. ደሴት ንጹህ የምግብ ዘይት/Deset Pure Food Oil
13. HADI COOKING OIL
14. Arif cooking oil
15. ሰነዓ ንፁህ የምግብ ዘይት /Senea pure food oil
16. ቃል ንፁህ የምግብ ዘይት/Kale Pure Food Oil
17. ናዲ የተጣራ ንጹህ የምግብ ዘይት/ Nadi pure food oil
18. ሰላም ንፁህ የምግብ ዘይት/Selam pure food oil
19. ኑኑ ንፁህ የምግብ ዘይት /Nunu pure food oil
20. MIFTAH pure food oil
21. ቤላ የተጣራ የኑግ ዘይት/BELLA Pure Niger Oil
22. ጣዝማ ንፁህ የምግብ ዘይት
23. ሚና ንፁህ የምግብ ዘይት
24. ብሌን ንፁህ የምግብ ዘይት/Blen Pure Edible Oil
25. ደስታ የተጣራ የኑግ ዘይት
26. ሐዲ የተጣራ የምግብ ዘይት
27. ሳራ የኑግ የምግብ ዘይት/Sara Niger Oil

የከረሚላ ምርቶች
1. ማሂ ከረሚላ/Mahi candy
2. ኢላላ ጣፋጭ ከረሚላ/Elaala sweet candy
3. ፋፊ ሎሊፖፐ/Fafi lolipop
4. ኢላላ ሎሊፖፕ ቢግ ጃር/Elaala lolypop big jar
5. ኮከብ ከረሚላ/KOKEB candy
6. ከረሚላ
7. ከረሚላ
8. ኤም ቲ ሎሊፖፕ/MT Loliipop
9. ኤ.ኤ ከረሚላ/A.A candy
10. ምንም ገለጭ ፁሑፍ የሌለው ከረሜላ

የአቼቶ ምርቶች
1. ሮያል አቼቶ/Royal VINEGAR
2. ዋልታ አቼቶ
3. ሮያል አቼቶ/ROYAL Vinegar
4. ሌመን አቼቶ/LEMEN ACETO
5. ሸገር አቼቶ/SHEGER ACETO

የለዉዝ ቅቤ
1. በእምነት ኦቾሎኒ ቅቤ/BEMNET PEANUT BUTTER
2. ናይስ/Nice peanut butter

የቫኔላ ፍሌቨር
1. ምንም ገላጭ ጽሑፍ የሌለው የቫኔላ ፍሌቨር

@fastmereja
6.1K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 12:23:41
ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ የሚያሰራው 51 ወለሎች ያሉት ህንፃ ዲዛይን ይፋ ተደረገ

ባንኩ በሰንጋ ተራ አካባቢ በተረከበው 5 ሺ 400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ህንፃ MAE ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ በተባለው ድርጅት የቀረበው ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል።

በተመረጠው ዲዛይን መሠረት የሚገነባው የባንኩ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ከ 51 በላይ ወለሎች እንደሚኖሩት ሪፖርተር ነው የዘገበው።

@fastmereja
5.7K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:18:33
ኤቢሴ አዱኛ (PHD) ትባላለች የተወለደችው ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ወለጋ ነቀምት ነው!!

የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ትምህርት ዋንጫ ተሸልማ አጠናቃለች! 2ኛ ዲግሪዋን በአፕላይድ ማትስ ሁሉም A በማምጣት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አጠናቃለች። ሶሰተኛ ዲግሪዋን ወደ አውሮፓ በማቅናት በዴንማርክ ሁሉንም ኮርስ «A» በማምጣት መጨረሳን ፋስት መረጃ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

እነሆ ሰሞኑን ደግሞ 4ኛ ዲግሪዋን በአሜሪካ አጠናቃ ተመርቃለች!! ሂሳብ ትምህርትን እስከ 4ኛ ዲግሪ በአስገራሚ ውጤት በብቃት ጨርሳለች ኤቢሴ አዱኛ

@fastmereja
5.9K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 08:43:59
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል መኒ (MPESA) ፈቃድ አገኘ

በኢትዮ ጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ዛሬ አንድ ዓመት የሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል መኒ (MPESA) ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ።

የሳፋሪኮም ኬንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ፒተር ንዴግዋ ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ ም ንጋት ላይ የተቋማቸውን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አንድ ዓመት የሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የድጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ሞባይል መኒ ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማግኘቱን አስታውቀወል። በሚቀጥሉት ሳምንታት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ጠቁመዋል።

ምንጭ ሪፖርተር
@fastmereja
6.1K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 18:54:20 ት/ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረሱ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ::

የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ት/ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ገልጿል::

በከተማችን አንዳንድ ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ያልተደረሰ መሆኑን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን የገለፀው ባለሥልጣኑ የክፍያ ጭማሪውን ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለ ሥልጣን መሰሪያ ቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ የጋራ አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።

@fastmereja
8.0K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 16:47:27
«በትግራይና በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል፡፡በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል፡፡

እኛ ያጐደልነው፣ የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል፡፡ ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም፡፡ የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡
በሌላ በኩል በሀገራችን ያለው የሰላም ሁኔታ በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ይህም ሂዶ ሂዶ ቤተክርስቲያንንና ሕዝብን፣ ሀገርን ልማትን መጕዳቱ የማይቀር ነው፡፡
በመሆኑም ቤተክርስቲያን ያለ ሀገርና ያለ ሕዝብ ህልውና የላትምና ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት፣ የሕዝቦቿን አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ፣ በሃይማኖታዊ መርሕና መንፈስ፣በገለልተኛ አቋምና በሁሉም ዓቃፊነት ስልት ለሰላም ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡»

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

@fastmereja
7.4K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 17:45:29 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናት ይፋ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ 8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተናግረዋል::

አያይዘውም ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ አሳስበዋል ::

በ 2015 ዓ. ም 75,100 የ8ኛ እንዲሁም 75,078 የ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::

@fastmereja
7.9K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ