Get Mystery Box with random crypto!

ት/ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረሱ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድ | FastMereja.com

ት/ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረሱ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ::

የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ት/ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ገልጿል::

በከተማችን አንዳንድ ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ያልተደረሰ መሆኑን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን የገለፀው ባለሥልጣኑ የክፍያ ጭማሪውን ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለ ሥልጣን መሰሪያ ቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ የጋራ አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።

@fastmereja