Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2023-04-20 18:42:17 ዒድ ሙባረክ! የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረበያ በመታየቷ የኢድ አል ፊጥር በዓል በነገው ዕለት ጁምዓ ሚያዝያ 13/ April 21/2023 መሆኑ ታውቋል።

@fastmereja
6.8K viewsedited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 14:09:16 1.5 ቢሊዮን ብር የፈጀው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ስራ ሊጀምር ነው
#FastMereja

በባለፉት ስምንት አመታት በግንባታ ላይ የነበረው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል እነሆ ግንባታውን አጠናቆ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አሚር ሰዒድ ዛሬ በሆቴሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግሯል።

ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል (Stay Easy plus) በጥንዶቹ በአቶ ዳግማዊ መኮንን እና በወ/ሮ ህይወት አየለ ባለቤትነት የተገነባ ሲሆን፣ ሆቴሉ ለግንባታ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ፈጅቷል። ምድሩን ጨምሮ ዘጠኝ ወለሎች አሉት። ባለ አምሰት ኮከብ ደረጃ ለማግኘት ያመለከተው ሆቴሉ በአጠቃላይ 103 ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከ15 እስከ 1,5ዐዐ ሰው ማስተናገድ የሚችሉ ስድስት የስብስባና፣ የሰርግ አዳራሾች እንዲሁም የጥበብና ቲያተሪካል አርት እና ሌሎች ዝግጅቶችን ማቅረብ ለሚፈልጉ ምቹ አዳራሾች አሉት።

ሶስት ባር እና አንድ መመገቢያ አዳራሾች ያለው እራሱን የቻለ የዳቦና የኬክ መጋገሪያ ኪችን ያለው በሰዓት ከ3ዐ,ዐዐዐ ዳቦ በላይ ማምረት የሚችል ማሽን ያሉት ሲሆን ኦፕን ኪችን እንዲሁም ግዙፍ የላውንደሪ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ማሽኖች አሉት፡፡

"ከደቡብ አፍሪካ ከስደት ስንመጣ የመጀመሪያው ባለ 3 ኮኮብ ስቴይ ኢዚ ሆቴል በ22 አካባቢ ገንበተን ስራ የጀመርነው አሁን እሱ አድጎ ነው ትልቁን ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል የገነባው" ያሉት የሆቴሉ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት አየለ ናቸው በተጨማሪም በበጎ አድራጎት ለስምነት አመታት ለበዓል ሁለት ሰንጋዎችን በማረድ አቅመ ደካማ ለሆኑ ሰዎች እየለገሰን ነው ብለዋል።

ሆቴሉ በአጠቃላይ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል። በእንጦጦ እና ሱልልታ የሩጫ ከእንጦጦ ፓርክና ቦታኒክ ጋርደን ልምምድ ለሚያደርጉ አትሌቶች በቅርብ የሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል ከመሆኑ ባሻገር መኝታ ክፍል ለያዘ እንግዳ ሙሉ በሙሉ አዲስ አበባን ከአራቱም አቅጣጫ መመልከት የሚያስችል ልዩ እይታ ያለው ሆቴል ነው ተብሏል።

ሆቴሉ የከርሰ ምድር ውሃ ያለው ሲሆን በሰከንድ አምስት ሊትር ውሃ ማመንጨት የሚችል ሲሆን ለማህበረሰቡም ለ24 ሰዓት በነፃ እንዲጠቀሙ ፈቅዷል።

ሆቴሉ በአጠቃላይ የያዘው ስፍራ 2,250 ሜትር ስኵር ሲሆን በ 1,7ዐዐ ሰኵር ላይ ሆቴሉ ተገንብቷል። የኤሌትሪክ መኪና ይዘው ለሚመጡ ደንበኞቹ ኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ቦታ ያለው ሲሆን በቅርቡ በሚጠናቀቁት የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ሰፖርት መስሪያ ጂም ፣ሳውና እና ስቲም ባዝ ፣ መዋኛ ገንዳ፣ የዮጋ አዳራሽ በተጨማሪም የባህል ሬስቶራንትና የሙዚቃ አዳራሽ ይኖረዋል፡፡

ከመሀል ከተማ ፒያሳ በመኪና አስር ደቂቃ ብቻ የሚወስድ አዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ቶታል አጠገብ የሚገኝ ሲሆን ፀጥ ያለ እና ነፋሻማ ስፍራ ላይ የሚገኝ ሆቴል ነው።

@fastmereja
7.8K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 14:09:12
5.6K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 18:45:04
በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ

በምስራቅ አርሲ ለትንሳኤ በዓል የገዙት በሬ ለእርድ በሚቀርበበት ሰዓት በሀሞቱ ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ መገኘቱን የጢዮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ግረማ ጣፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦቹ ኩማ ተሰማ እና ንጉሴ ዲንቃ የተባሉ ሲሆን ለበዓል ቅርጫ በ38ሺህ ብር በሬ ገዝተው በሚያርዱበት ወቅት በበሬው ሃሙት ውስጥ 7.5 ኪሎግራም የሚመዝን ወርቅ አግኝተዋል። ወርቁ ሃያ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር መሸጡ ተሰምቷል።

ከቀናት በፊትም በዚሁ አካባቢ 18.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ በበሬ ሀሞት ላይ ስለመገኘቱ እና ወርቁን 53ሺብር ስለመሸጡ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው እንዳሁኑ ይፋ የወጣ ነገር ባይኖርም በተደጋጋሚ በበሬዎች ሃሞት ላይ ወርቅ ስለመገኘቱም ኮማንደር ግርማ ጣፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Via: ዳጉ ጆርናል

@fastmereja
7.1K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:02:25
የሶደሬ አንቀጸ ሰላም መድኃኔዓለም ገዳም ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ከፍተኛ ጥቃት ተፈፀመበት

በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከአዳማ/ናዝሬት ከተማ በ25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ረጅም ዘመን ያስቆጠረው ጥንታዊው የሶደሬ አንቀጸ ሰላም መድኃኔዓለም ገዳም ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ሚያዚያ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከፍተኛ ጥቃት እንደተፈጸመበት ገልጾ ዝርዝር መረጃውን እንደደረሰን እናቀርባለን ሲል የሀገረ ስብከቱ ህዝብ ግንኙነት ዘግቧል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

@fastmereja
6.3K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:42:54
አቶ አንዱዓለም አራጌ ከኢዜማ አባልነቴ መልቀቃቸውን ገለፁ

@fastmereja
6.3K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:27:00 ለቅርጫ ካረዱት በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ያገኙት ዕድለኞች

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎች ከበሬው ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል። በሬውን በ40 ሺህ ብር የገዙት ተቃራጮቹ፣ ከበሬው ሆድ ውስጥ ያገኙትን ወርቅ በ53 ሺህ ብር በመሸጥ የበሬውን ሥጋ በነፃ በልተው 13 ሺህ ብር ማትረፍ ችለዋል።

ነገር ግን ተቃራጮቹ ሌላ በሬ ለመግዛት ወስነዋል፤ የተቃራጮቹ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በቀለ ቀነኒ እንዳሉት፣ ከወርቁ ሽያጭ በተገኘው ገንዘብ ሌላ በሬ ለመግዛት ቀጠሮ ይዘዋል።

ከበሬው ሆድ ውስጥ እንዴት ወርቅ ተገኘ? ሳይንሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የአሰላ የእንስሳት ጤና ማዕከል የላቦራቶሪ ባለሙያ ዶ/ር አብዲሳ ለማ፣ በበረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ጥቃቅን ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች እየተመገቡ በጊዜ ሂደት ማዕድናቱ በሐሞት ውስጥ እየተጣሩ ወደ ወርቅነት (በተለምዶ ‘የሐሞት ወርቅ’ ወደሚባለው) እንደሚቀየሩ ተናግረዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

ንጥረ ነገሩ በከብቶቹ ሆድ ውስጥ እየቆየ ሲሄድ የሐሞት ፍሳሽን ስለሚመጥጥ ከብቶቹ እንዳይደልቡ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

@fastmereja
3.4K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 16:02:43 ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ያኮረፈዉ ወጣት እራሱን አጠፋ
#FastMereja
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ከቤተሰቦቹ ተጨቃጭቆ መግባባት ያልቻለዉ ወጣት በገመድ እራሱን ሰቅሎ ህይወቱን ማጥፋቱ ፖሊስ አስታዉቋል።

በደቡብ አሪ ወረዳ ባላመር ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ ይህ ወጣት ለ2015 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ልብስ እንዲገዛለት ለወላጆቹ ጥያቄ ማቅረቡ ተከትሎ ወላጆቹም ቀደም ሲል የሚለብሳቸዉን ልቦሶች አፅድቶ በመልበስ የዘንድሮዉን በዓል አክብሮ እንዲዉልና በሱ ጥያቂነት ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቤተሰብ አልባሳት ይገዛልሀል የሚል ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ ይሰጠዋል። ወጣቱ በወላጆቹ እምቢታ ተናዶ እራሱን እንደሚያጠፋ ዝቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ከስምምነት ሳይደርስ መለያየቱ ነዉ ከፖሊስ በደረሰን መረጃ ለመረዳት የተቻለዉ።

ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት ቢዝትም ቤተሰብ እንዲህ አይነቱ እኩይ ተግባር ሊፈፅም ይችላል የሚል ጥርጣሬ አልነበረዉም ተብሏል።ነገር ግን ሚያዝያ 08 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት ላይ ወጣቱ እራሱን በገመድ ሰቅሎ በድን ገላዉ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ እንደተገኘና የወጣቱ አድራጎት ቤተሰቡን በእጅጉ ያስደነገጠና ያሳዘነ ሆኖ ማለፉ ነዉ ፖሊስ ያስታወቀዉ።

ሁለት ወራትን በፆም በፀሎት የከረሙት የሟች ቤተሰቦች የፋሲካን በዓል ለማክበር ያልታደሉ ሆነዉ ድንኳን ቀስተዉ የልጃቸዉ ሀዘን ለመቀመጥ ተገደዋል ሲል ከደቡብ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
4.4K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 20:12:19
24 ሰዓት ሞቅ ደመቅ ብላ የምትውለው የኢትዮጵያ ከተማ አወዳይ
#FastMereja
ከአዲስ አበባ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፣ በአወዳይ ከተማ ቀንም ምሽትም አንድ ነው ፀሐይ አትጠልቅም ይባላል። በአንድ ቀን ብቻ በጫት ግብይት በዚህ ከተማ ከ20 እስከ 30 ሚሊዮን ብር ይብይት ይፈፀማል ተብሎ እንደሚገመት የከተማው መስተዳደር ይገልፃል።

@fastmereja
5.8K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 19:41:21
የጎዳና ላይ ኢፍጣር በሰሜናዊት ኮኮብ መቐለ ከተማ

@fastmereja
5.7K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ