Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2023-04-17 19:40:18
ተጠባቂው የቦስተን ማራቶን በወንዶች የ2022 አሸናፊው ኬኒያዊው ኢቫንስ ቼቤት ዘንድሮም 2:05:54 በአንደኝነት ሲያሸንፍ፣ በሴቶች ከኬኒያ ሄለን ኦቢሪ አሸናፊ ሆናለች፣ ኪፕቾጌ 6ኛ ሆኖ አጠናቋል።

@fastmereja
4.7K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:10:51
1.4K views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:10:49 የእግር ኳስ ወጎች….
የኤቡዌ ሚሊዮን ፓውንዶች የት ደረሱ?

(በምስጋናው ታደሰ)

ኢማኑኤል ኤቡዌ በአንድ ወቅት የአውሮፓ እግር ኳስ ድምቀቶች ከነበሩ አፍሪካውያን ከዋክብቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡ በአይቮሪኮስት መዲና አቢጃን የተወለደውና ከዝነኛው የአሴክ ሚሞሳስ አካዳሚ ተገኘው ኤቡዌ በተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈ ቢሆንም በተለይም ግን በአርሰናል በነበረው የሰባት ዓመታት ቆይታ በእጅጉ ጎልቶ መውጣት ችሏል፡፡ ከመድፈኞቹ ከተለያየ በኋላ በጋላታሳራይና ሰንደርላንድ ቆይታ አድርጎ በ2016 ጫማውን ሰቅሏል፡፡ ለሀገሩ ብ/ቡድን 79 ጨዋታዎችን አድርጎ 3 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

አሁን 39ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው ኢማኑኤል ኤቡዌ በተጨዋችነት ዘመኑ ከሀብትና ንብረቱ ባሻገር ከ20 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ጥሬ ገንዘብ ነበረው፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ያንን ሁሉ አጥቶ ባዶ እጁን ቀርቷል፡፡ በአንድ ወቅትም ጎዳና እስከመውደቅ ደርሶ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ቤልጄማዊቷ የቀድሞ ባለቤቱና የሶስት ልጆቹ እናት አውሬሊዬ በፈጠረችበት ክህደት መሆኑን ነው የሚናገረው፡፡ አይቮሪኮስታዊው በቀለም ትምህርቱ የገፋ ባለመሆኑ በአንድ ወቅት ባለቤቱ የሆነ ፅሁፍ አምጥታ እንዲፈርም ሰጠችው፡፡ ሳያነበው ፈረመ፡፡ ሙሉ ለሙሉ ሀብቱንና ኢንቨስትመንቶቹን በስሟ እንዳዞረላት የሚያረጋግጥ ሰነድ ነበር ያስፈረመችው፡፡ ከዛ በኋላ ፈታችው፤ ከቤቱም አስወጣችው፡፡ በሰሜን ለንደን የገዛውንና አብረው ይኖሩበት የነበረውን ግዙፍ ቪላ በስሟ ካዞረችው በኋላ ሸጠችው፡፡ ጎዳና ወደቀ፡፡ ራሱን ጣለ፡፡ የመንፈስ መረበሽ አጋጠመው፡፡ በተደጋጋሚ ራሱን ለማጥፋት ሞክሮ ተረፈ፡፡ አሁንም አልፎ አልፎ ይሄንኑ እንደሚያሳብ ይናገራል፡፡

“እግዚያብሔር ይሄንን መጥፎ መንፈስ እንዲያርቅልኝ እፈልጋለሁ” የሚለው ኤቡዌ “ሀብትና ንብረቴን ተከራክሬ ለማስመለስ ብፈልግም ለጠበቃ የምከፍለው ገንዘብ የለኝም፡፡ ቤቴን ለቅቄ ከመውጣቴ በፊት አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከውስጥ መኖሬን እንዳያውቁ ስለምፈልግ መብራቱን አጠፋ ነበር፡፡ ይሄም ለበለጠ ጭንቀት ዳርጎኛል” ይላል፡፡

ኤቡዌ በአርሰናል ቆይታው በርካታ ሚሊዮን ፓውንዶችን ሰርቷል፡፡ በቱርኩ ጋላታሳራይ ደግሞ ዓመታዊ 1.5 ሚሊዮን ፓውንድ (2.35 ሚሊዮን ዩሮ) ደመወዝ ያገኝ ነበር፡፡ ተጨማሪ የቦነስ ክፍያም ነበረው፡፡ ያ ሁሉ ገንዘብ ግን አሁን እጁ ላይ የለም፡፡ “ዛሬ ላይ ሆኜ ያለፈውን ጊዜ ሳስበው ራሴን በራሴ 'ኢማኑኤል፤ ምን ዓይነት ቂልና የዋህ ነበርክ? እንዴት ስለመጪው ጊዜ አታስብም?' ስል እጠይቃለሁ፡፡ በጋላታሳራይ ሳለሁ ስምንት ሚሊዮን ዩሮ አገኘሁ፤ ሰባት ሚሊዮኑን ለእሷ ላኩላት፡፡ ግን ካደችኝ፡፡ ቲዬሪ ሆንሪ በአርሰናል ቤት አብሮኝ ተጫውቷል፡፡ ዛሬ የቴሌቪዥን ተንታኝ ሆኖ ስመለከተው በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ ግን ደግሞ በራሴ አፍራለሁ፡፡ አብሬያቸው የተጫወትኳቸውንም ሆነ በተቃራኒ የገጠምኳቸውን ተጨዋቾች በቴሌቪዥን ስመለከታቸው 'ይሄን ጊዜ የእኔም ቦታ እዚህ ነበር' እያልኩኝ በእነሱ ብደሰትም በራሴ ግን አፍራለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ራስህን አጥፋ አጥፋ የሚል ስሜት ይፈጠርብኛል” ይላል፡፡

እጅግ በጣም ውድ የሆኑ መኪኖችን ያሽከረክር የነበረው አይቮሪኮስታዊው ኮከብ ዛሬ ለንደን ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት ነው የሚጠቀመው፡፡ የሀገሩ ልጅ የሆነችውና እሱ “እህቴ” ሲል የሚጠራት ያስሚን ራዛክ እዛው ለንደን ውስጥ ኢንፊልድ ተብሎ በሚጠራው መንደር ከመኖሪያ ቤቷ ሰርቪስ ክፍሎች አንዷን ሰጥታው በዛ ጎኑን ያሳርፋል፡፡ ሲያልቅ አያምር ይሏል ይህ ነው…

@FastMereja
1.4K viewsedited  14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 22:57:14
የፍቅር ጓደኛዬ ፂሜን አይቶ ነው የወደደኝ

አያንቱ አድማሱ ትባላለች ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ በእንስሳት ህክምና ተመርቃለች። ተወልዳ ያደገችው በቄለም ወለጋ በዳምቢ ዶሎ ነው። አያንቱ ወደ ጉርምስና ከገባችበት ጊዜ ጀምሮ ከልጃገረዶች የተለየ ነገር ማየት ጀመረች፣ እንደ ወንድ ፂም ማብቀል ጀመረች።

ሳይንሳዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሴቶች እንደ ወንድ ጢም ማብቀል የተለመደ ባይሆንም አልፎ አልፎ እንደሚከሰት ይገለፃል።

አያንቱ በልጅነቷ መላ ሰውነቷ በፀጉር ተሸፍኖ እንደነበር እና ካደገች በኋላ እንደጠፋላት ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልፃለች። "ቤተሰቦቼ በልጅነቴ በሰውነቴ ላይ ብዙ ፀጉር ነበረኝ ይላሉ፣ በኋላ ላይ ጠፋ እና ወደ ጉርምስና ስገባ ፂም መብቀል ጀመረ" ብላለች።

መጀመሪያ ላይ ፊቷ ላይ ፂም ሲወጣ ስታይ ተናዳ እራሷን ጠልታ እንደነበር ገልፃለች።

የፍቅር ጓደኛዋ ፂሟን ወዶላት ለፍቅር እንደጠየቃት ትናገራለች "ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ እንዳልቆረጥ ያበረታታኛል" ስትል ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ሃሳቧን አካፍላለች።

@fastmereja
4.6K views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 15:54:53
ራሱን ሴት አስመስሎ ሲያታልል የተያዘው ወጣት
#FastMereja
ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ ሸበራ ጥላሁን የተባለ ወጣት ራሱን ሴት በማስመሰል ህዝቡን ሲያታልል ከምሽቱ 3፡30 ላይ በቦረና ሆቴል በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዟል።

@fastmereja
5.7K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 18:52:58
በሱዳን ያለው ውጥረት የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሷል

በሱዳን ጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻ አባላት መካከል እየተደረገ ያለው የተኩስ ልውውጥ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በካርቱም ሰማይ ላይ የጦር ጀቶች ሲበሩ ታይተዋል።

ሄምቲ በሚለው ቅጽል ስማቸው በሚታወቁት በጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል፣ ወደ አገሪቱ ጦር ስለሚቀላቀልበት ሁኔታ አንዲሁም ኃይሉን ማን ይመረዋል በሚለው አለመግባባት ተፈጥሮ ባለፉት ቀናት ውጥረት በአገሪቱ ውስጥ ሰፍኖ ነበር።

ዛሬ ቅዳሜ ከረፋድ ጀምሮ የተኩስ እና የፍንዳታ ድምጽ በመዲናዋ ካርቱም እየተሰማ ነው። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የካርቱም ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ተቆጣጥሪያለሁ ብሏል።

የአገሪቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ለመቆጣጠር የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑም ተዘግቧል።

በዚህ መካከል የሱዳን ሠራዊት ናቸው የተባሉ የጦር ጀቶች በካርቱም ሰማይ ላይ ሲበሩ ታይቷል።

ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በሱዳን የተከሰው ውጥረት እና ግጭት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ነው ታስነበበው።

@fastmereja
3.1K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 18:32:00
ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት የመከላከያ ሠራዊቱንና የሠራዊቱን አመራሮች ስም የሚያጎድፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አሳሰበ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፤ የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ አንዳንድ አካላት ሆን ብለውና በተቀናጀ አግባብ በሀሰተኛ መረጃ የመከላከያ ሰራዊትን እና የአመራሮቹን ስም እያጎደፉ መሆኑን ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

@fastmereja
3.2K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 18:16:28
የሱዳን ወንድማማች ፓርቲዎች ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ፣ ትግላቸውን እንዲያቆሙ እና ወደ ውይይት መንገድ እንዲመለሱ እንጠይቃለን ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

@fastmereja
3.2K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 12:42:36
ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የክልል ልዩ ሃይሎችን በፌዴራልና የክልል የጸጥታ ተቋማት መልሶ የማደራጀት ስራ የመከላከያ ጀነራሎች፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የክልል የስራ ኃላፊዎች በተገኙ ተገምግሟል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የክልል ልዩ ሃይሎች እንደገና በመደራጀታቸው ህብረ ብሄራዊ ጠንካራ የጸጥታ ተቋም ይገነባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከነበረችበት የጸጥታ ችግር በፍጥነት መውጣቷን የገለፁት ፊልድ ማርሻሉ፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑንም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የክልል ልዩ ኃይሎች አደረጃጀት ህጋዊ አለመሆን፣ በክልሎች መካከል እንደ ስጋት መተያየት እንዲሁም ችግሮችን በሃይል ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ አደረጃጀቱን ለመቀየር አስገድዷል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በሁሉም ክልሎች መልሶ የማደራጀት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው "ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀትና መዋቅር የለም" ብለዋል።

በመሆኑም የጸጥታ መዋቅሩ መከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ ሲሆን በክልል ልዩ ኃይሎች ስም ተልዕኮም ሆነ ግዳጅ የሚቀበል ኃይል አይኖርም ሲሉ አረጋግጠዋል።

ከዚህ በኋላ በመረጡት አደረጃጀት መሰረት ሁሉንም ወደ ተመደቡበት የማጓጓዝና ወደ ስልጠና የማስገባት ስራ ይከናወናል ብለዋል።

@fastmereja
4.3K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 09:53:07 በሚዲያ ጥፋት የተጠረጠሩ ታሳሪዎች በሙሉ፤ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ከእስር እንዲለቀቁ ኢሰመኮ አሳሰበ

በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል የተጠረጠሩ ታሳሪዎች “በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ከእስር እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ። የመንግስት የጸጥታ አካላት በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላት እንዲሁም በማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ካተኮረ “እስር እና ማዋከብ” እንዲቆጠቡም ኮሚሽኑ ጠይቋል።

ኢሰመኮ ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችን እና አባላትን “ዒላማ በማድረግ” እየተፈጸመ ያለን “እስር እና ወከባ” አስመልክቶ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 7፤ 2015 ባወጣው መግለጫ ነው። በእነዚህ አካላት ላይ እየተፈጸመ ያለው “እስር እና ወከባ በእጅጉ አሳሳቢ” መሆኑን በገለጸው ኮሚሽኑ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ስምንት ጋዜጠኞች እና አንድ የማህበረሰብ አንቂ ለእስር መዳረጋቸውን በመግለጫው አስታውቋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

@fastmereja
4.4K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ