Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2023-04-13 08:43:46
"ከፈጣሪ በታች መከላከያ ሰራዊት ዋስ ጠበቃችን ነው፣ ለተፈጠረው ነገር ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን" ምስራቅ አማራ ፋኖ

"በጊዜያዊ አለመግባባት የፈጠረ ነገር ነው፣ በግጭቱ የተተረፈ ነገር የለም፣ የሀገር ሽማግሌዎች ያለንበት ቦታ መጥተው ከመከላከያ ጋር አቀራርበውን የተፈጠረውን ችግር በሽምግልና ቀርፏል፣ በዚህ አጋጣሚ ከፈጣሪ በታች መከላከያ ሰራዊት የሁላችንም ዋስ ጠበቃ ነው በተፈጠረው ነገር በግራም በቀኝም ብዙ ልጆችን አጥተናል እንደተቋም መከላከያ ሰራዊትን ትልቅ ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን" ሲሉ የምስራቅ አማራ ፋኖ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልፇል።

@fastmereja
2.1K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:24:41
ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ዞን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት መፈታቱ ተገለፀ

ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር በሐይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌዎች እና በዘወልድ ሽምግልና ስርዓት የሠላም ስምምነት ተደረገ። በሰላም ስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል፣ የዞን፣ የምስራቅ አማራ ፉኖ አመራሮች እና የአገር ሽማግሌዎች የሰላም ስምምነቱን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም በግጭት የሚፈታ አጀንዳ እንደሌለና ሁሉም ጉዳይ በሰላምና በመወያየት መፍታት እንደሚቻልና በተፈጠረው የፀጥታ ችግር በማዘናቸው ይቅርታም ጠይቀዋል ።

የፋኖ አደረጃጀት ህዝባዊና ከመንግሥት አደረጃጀት ውጭ በመሆኑ መንግሥት ባስቀመጠለት አማራጭ በመጠቀም ህጋዊ ወደሆነው መንግስታዊ መዋቅር እንዲገባ ምቹ ሁኔታ በመንግስት እንደተፈጠረም በመግለጫው ተገልፇል ሲል የሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።

@fastmereja
3.9K viewsedited  18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 20:52:27
በቦሌ ዩጎ ፓርክ ተመረቀ!!

ዩጎ ሲቲ ቤተክርስቲያን ለአንድ አመት ተኩል ለሚያህል ጊዜ በመፍጀት ቦሌ ድልድይ ስር ፓርክ ገንብቶ ለህዝብ ጥቅም እንዲሆን አበርክቷል። ፓርኩ በ 3/8/2015 ተመርቆ ለህዝብ ይፋ ሆኗል።

@fastmereja
4.0K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:27:20
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በስጦታ የተሰጣቸውን ልጅ በጽ/ቤታቸው አገኙ

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በምስራቅ አፍሪካ የኬንያ የኡጋንዳ የታንዛኒያ የሩዋንዳ አህጉረ ስብከት በአዲስ አበባ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሀገረ ስብከታቸው ጽ/ቤት ሚያዝያ 02/2015 ዓ/ም በስጦታ የተሰጣቸውን የሁለት ዓመት ልጅ ከወላጅ እናቱ ጋር በማግኘት ልጁ በአግባቡ ማደግ እንዳለበት በማሳሰብ ለወደፊቱ ለልጁ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ እና እድሜው ለትምህርት ሲደርስ ትምህርቱን በአግባቡ መማር እንዳለበት አሳስበዋል ሲል የዘገበው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ነው።

@fastmereja
1.5K viewsedited  11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:09:48
ዝነኛው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ማይክል ጆርዳን በአንድ ወቅት ተጫምቶት የተጫወተበት ጫማ በ2.2 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ።

@fastmereja
1.8K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 09:49:31
በደቡብ ወሎ በአልብኮ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች ላይ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ከባድ ዝናብ ጉዳት አደረሰ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ በ16 ሀሮና በ03 ፈላና ቀበሌዎች ሚያዝያ 2/2015 ምሽት ላይ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ጉዳት አድርሷል:: የአልብኮ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ይልማዘር አሊ እንደገለጹት በወረዳው ከዚህ በፊት በሌሎች ቀበሌዎች ጉዳት ደረሶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በ016ና በ03 ቀበሌዎች በሰብል፤ በአትክልት፤ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል የደረሰውን ጉዳት መጠን በተመለከተ በዝርዝር በባለሙያ እየተጠና መሆኑ አልብኮ ኮሙንኬሽን ነው የዘገበው።

@fastmereja
3.5K views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 09:03:21
የኢትዮ 360 ሚዲያ መስራች ኤርሚያስ ለገሰ ራሱን ከሚዲያው ማግለሉን ገለፀ

ባለፉት 3 አመታት ኢትዮ 360 የተባለ የዩቲዩብ ቻናል መስራች እና አቅራቢ የሆነው ኤርሚያ ለገሰ ከቅርብ ጊዚ ወዲህ በሚዲያ በተለይ "ዛሬ ምን አለ?" በተባለው ከእነ ሀብታሙ አያሌው ጋር በሚደረገው የውይይት ፕሮግራም እንዳልናገር የመገደብ፣ ልዩነትን የሚያስተናግዱበት አግባብ፣ ከእኔ አልፈው ሀገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቼን የሚረብሹ ሆኖ ስላገኘዋቸው እንዲስተካከሉ ለማናጀር ጭምር ብናገርም ሊስተካከሉ አልቻሉም በዚህ ምክንያት ራሴን ከኢትዮ 360 ሳገል ከከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ሆኜ ነው ሲል ኤርሚያስ ከዩቲዩብ ቻናሉ ራሱን ማግለሉን ገልፇል።

@fastmereja
3.6K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 23:56:07 በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የአርሰናልን ዱካ እየተከተለ ያለው ማንችስተር ሲቲ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ባየር ሙኒክን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
@FastMereja
4.6K views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:35:05 በንግድ አለም ያላችሁ ሰዎች ይኼን የስርቆት ዜዴ ተጠንቀቁ... [በተለያዩ ከተማዎች እየተሰማ ነውና...]

ሌባው ፏ ፈሽ ብሎ ገዢ መስሎ ከች ይልልሀል። ከዛ የሚገዛውን ዕቃ ዋጋ ጠይቆ ይሰማል ፤ ተከራክሮም ሆነ ሳይከራከር በዋጋው ይስማማል። ከዛ የሚፈልገውን ብዛት፣ ዓይነት፣ ቀለም ምናምን ይናገርና ፤ "ግዢውን ከመፈጸሜ በፊት ለአለቃዬ ደውዬ መናገር አለብኝ"... ይልና ስልኩን አውጥቶ ይሞክራል። ከዛ "ስልኬ ዘጋብኝ" ወይ ደግሞ "ስልኬ ብር የለውም" or ሌላም ምክንያት ያቀርብና "ያንተን ስጠኝና ለአለቃዬ ልደውለት" ይላል። አንተ ዕቃውን መሸጡ ላይ ትኩረት ስላደረክ እሺ በማለት ስልክህን ትሰጠዋለህ።

ከዛ ይኼ ሌባ ወድያው ስልክህን ተቀብሎ የሆነ ቁጥር ጽፎ እንደሚደውል በማስመሰል የራሱን ስልክ ቁጥር ይጽፍና CBE ብሎ ሴቭ ያደርጋል። አለቃዬ አላነሳልኝም ወይ ደግሞ ስልኩ አልሰራልኝም ምናምን ይልህና ስልክህን ይመልስልሀል።

ከዛማ ፥ አንተ ላይ በሚፈጥረው ከፍ ያለ ዋቴ የሌለ ይሰካክስህና ፥ "በቃ እንደውም የባንክ ቁጥርህን ፃፍልኝና አለቃዬ ብሩን በአካውንትህ ሲያስገባ ዕቃውን እወስደዋለሁ" ይልሀል። አንተ ሀሳብህ ዕቃውን መሸጥ ስለሆነ ፤ እሺ ትለውና የባንክ አካውንትህን ትነግረዋለህ። ሌባው ካንተ ከተለየ ካንድ ከ10 ደቂቃ በኋላ CBE ተብሎ ሴቭ በተደረገው ቁጥር ከባንክ እንደተላከ አስመስሎ ዕቃው የሚያወጣውን ያህል ገንዘብ ሜሴጅ ይልክልሃል። ከዛ በደቂቃዎች ልዩነት ተመልሶ ይመጣል ወይ ሌላ ሰው ይልክና "ገንዘቡ ደረሰህ ኣ?" ምናምን ብሎህ ፤ በጣም አጠዳድፎህ ዕቃውን በመኪና ወይ በባጃጅ ጭኖ ላሽ ይላል!

ድንገት ባንነህ text በተደረገልህ ቁጥር መልሰህ ስትደውል ሲም ካርዱ አይሰራም

ከዚህ ዓይነት ሌብነት ራሳችሁን ጠብቁ! ተጠንቀቁ! ጽሑፉ ጠቃሚ ከሆነ ለሌሎችም #share አድርጉ
በንግድ አለም ያላችሁ ሰዎች ይኼን የስርቆት ዜዴ ተጠንቀቁ... [በተለያዩ ከተማዎች እየተሰማ ነውና...]

አስፋወሰን አዳዬ (ቻፒ) ነኝ

@Fastmereja
5.6K viewsedited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 17:09:08
ወላጅ አባቱን በአሳቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት ተቀጣ፡፡

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ወላጅ አባቱን የገደለው አቶ መሐሩ ዮሐንስ የተባለ ግለሰብ ነው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ የወሰነው፡፡

ተከሳሽ መሐሩ የሐንስ የተባለ በከምባታ ጠምባሮ ዞን በሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሌሾ ማዞሪያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጉንጃ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ሟች ዮሐንስ ኬዕሚሶ የተባለ አባቱን የሰበሰብከውን ንብረት አትበላም ብሎ ስዝት ቆይቶ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ሟች ተኝቶ ባለበት በዘነዘና ጭንቅላቱን በመቀጥቀጥ ገድሏል ተብሎ በወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ላይ የቀረበበትን ክስ አቃቤ ህግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ ተከሳሽ ክሱን እንዲያስተባብል ታዞ መከላከያ ማስረጃ የሌለው መሆኑን በጽሑፍና በቃል ማስረጃ የለኝም ብሎ በማረጋገጡ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት 03/08/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ከምባታ ጠምባሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

@fastmereja
5.5K views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ