Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.80K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2023-04-14 20:04:34
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት በጋራ ስምምነት ተለያያ

@fastmereja
2.7K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 19:00:17
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በድሬደዋ ከተማ ተገናኝተው መክረዋል።

@fastmereja
3.7K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:43:54
የዘንድሮ የትንሳኤ በዓል ላለፉት ሁለት እና ከዛ በላይ ዓመታት በመከራ ውስጥ ያለውን የትግራይ ህዝብ ከስቃዩ የሚወጣበት በዓል ይሆን ዘንድ ሁላችንም መጸለይ አለብን። የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ከመኖርያ ቤታቸው ተፈናቅለው አስከፊ ህይወት እያሳለፉ ያሉትን ወገኖቻችን በማሰብ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

በዓዲግራት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የመቐለ ልደታ ማርያም ቆሞስ አባ ጥዑም በርሀ ለድምፂ ወያኔ

@fastmereja
3.6K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 13:33:50 ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት 2 ቢሊየን ዶላር ብድር ለማግኘት መጠየቋ ተዘገበ

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ቢያንስ የ2 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ከተቋሙ ጋር እየተነጋገረች መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።

በጦርነት እና በዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች የተዳከመውን ምጣኔ ሃብቷን ለማነቃቃት ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ከፍተኛ መጠን ያለውን ብድር ለማግኘት እየሞከረች መሆኑን የዜና ወኪሉ ጉዳዩን የሚያውቁ አራት ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ባለፉት ሳምንታት ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለሥልጣናት በአዲስ አበባ እና ዋሽንግተን ውስጥ ውይይት ሲያደርጉ እንደነበር ይታወቃል።

አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በሚችለው ድጋፍ ዙሪያ አስፈላጊውን “ቴክኒካዊ ሥራ ለማከናወን” የድርጅቱ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ውስጥ ከአንድ ሳምንት በላይ መቆየታቸውን ብሉምበርግ ዘግቦ ነበር።

ይህ የተቋሙ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ያደርጉት ቆይታ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተካሄደው ጦርነት ካበቃ ከወራት በኋላ ሲሆን፣ አገሪቱም በግጭት እና በድርቅ የተጎዳውን ምጣኔ ሃብቷን እንዲያገግም ለማድረግ ጥረት በጀመረችበት ወቅት ነው።

ለሁለት ዓመታት በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ኢትዮጵያ አይኤምኤፍን ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር የነበራት ግንኙነት ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወቃል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ከኢትዮጵያ የቀረበለትን ከፍተኛ መጠን ያለውን የብድር ጥያቄን በተመለከተ አገሪቱ ካለባት ዕዳ አንጻር እየገመገመው መሆኑን፣ ንግግሩ በአይኤምኤፍ እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ብቻ እየተካሄደ በመሆኑ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ንግግሩ አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ የጋራ ስብሰባ በሚደረግበት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር የምታደርገው ንግግር አሁንም ዋሽንግትን ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው።

“ኢትዮጵያ ከተቋሙ የምታገኘው ድጋፍን በተመለከተ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም፤ ሁለቱም ወገኖች የብድር ዘላቂነት ላይ የበኩላቸውን እየሰሩ ይገኛሉ” ብሏል አንድ የሮይተርስ ምንጭ።

የዜና ወኪሉ ይህንን ጉዳይ በሚመለከት ከአይኤምኤፍ፣ ከኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር እና ከብሔራዊ ባንክ ባለሥልጣናት ተጨማሪ መረጃ ቢጠይቅም ምላሽ አላገኝም።

ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት አይኤምኤፍ ባለው አሰራር መሠረት ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምራ የዕዳ ማሸጋሸግ እንዲደረግላት ስትጠይቅ ቆይታለች። ነገር ግን በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ጦርነት ሂደቱን አወሳስቦት ቆይቷል።

በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም መካከል ሲካሄድ የነበረው የድጋፍ፣ የብድር ስረዛ እና ሽግሽግ ንግግር በከፊል በትግራይ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ ነበር።

ከአንድ ሳምንት በፊት የአይኤምኤፍ ልዑካን ወደ አዲስ አበባ በተጓዙበት ጊዜ የተቋሙ ቃል አቀባይ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላት መጠየቋን አመልከተው ነበር።

“ሊሰጥ የሚችለው ድጋፍ አገሪቱ ለምታካሂደው አገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እና ምጣኔ ሀብቷን በማረጋጋት ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለሥራ ፈጠራ እና ለድህነት ቅነሳ የሚውል ይሆናል” ብለዋል ቃል አቀባዩ።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ቡድን፣ በአዲስ አበባ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ተቋሙ ለአገር በቀል የምጣኔ ሃብት ማሻሻያ የሚሰጠውን ድጋፍ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር የተደረገው ውይይት አዎንታዊ ሂደት የታየበት መሆኑን ገልጾ ነበር።

“የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በአገር በቀል ማሻሻያው ድጋፍ ላይ ስለሚኖረው ሽፋን ባደረግነው ውይይት አዎንታዊ ሂደቶችን አይተናል” በማለት የአይኤምኤፍ ልዑክ ቡድን መሪ አልቫሮ ፒሪስ መናገራቸው ተጠቅሷል።

በመቶሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና በቢሊዮን ዶላሮች የሚያወጣ ውድመትን ያስከተለው የእርስ በርስ ጦርነት ኢትዮጵያ ከምዕራባውያን ተቋማት እና አገራት ታገኝ በነበረው ምጣኔ ሀብታዊ ድጋፍ ላይ ከፍተኛ ጫናን አስከትሎ ነበር።

ብሉምበርግ እንዳለው ኢትዮጵያ ጦርነቱ ያስከተለውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እና የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመሸፈን አስፈላጊ ለሆኑ የገቢ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም ድጋፍ ያስፈልጋታል።

ጦርነቱ ካስከተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር በአፍሪካ ካሉ የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች መዳረሻ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን እና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የተነሳ ከዓለም ባንክ አንዲሁም ከአይኤምኤፍ የምታገኘውን ድጋፍ ገትቶት መቆየቱን ብሉምበርግ ዘግቧል።

በጦርነቱ እና በዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር የገጠማት ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከመመዝገቡ በላይ እጥረትም ተከስቷል።

ጥቅምት መጨረሻ ላይ ደቡብ አፍሪካ ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተፈረመውን ዘላቂ ግጭትን የማቆም ስምምነትን ተከትሎ ጦርነቱ ቆሞ በሰሜን ኢትዮጵያ የሕዝቡን ሕይወት ወደ መደበኛው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው።

በጦርነቱ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት 20 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፍልግ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በቅርቡ ተናግረዋል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው!!

@fastmereja
4.3K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 09:12:44
መንግስት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን እስር እና እንግልት ያቁም !

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ወገንተኝነታቸው ለህዝብና ለእውነት መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በስራቸው ላይ ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ደግሞ በህግ አግባብ መጠየቅ እንዳለባቸው እና የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበት ማህበራችን በፅኑ ያምናል።

ይሁን እንጅ " ከለውጡ በኋላ " በሀገራችን የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት እንዲረጋገጥ ማህበራችን ብዙ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለሙያዎች የሚሰሩበት አውድ እየጠበበ ጋዜጠኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ በመንግስት የፀጥታ አካላት እየተሸማቀቁ እና እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ማህበራችን እየታዘበ ነው።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የማህበራችን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን ጨምሮ አራጋው ሲሳይ ፣ ገነት አስማማው ፣ ጌትነት አሻግሬ ፣ በየነ ወልዴና ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት ሀይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ። አንዳንዶቹም ያሉበት ቦታ እና ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን ቤተሰቦቻቸውም በቂ መረጃ ሳይኖራቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።

ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ እየታሰሩ፣ እየታፈኑና ቤታቸውና ቢሯቸው እየተበረበረ መሆኑ ባለሞያዎች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ፤ የፕረስ _ ምህዳሩ _ የበለጠ እንዲጠብ እያደረገ ነው። ማህበራችንም የተቋቋመው እንደዚህ አይነት ሙያውን የሚያቀጭጩ ጫናዎችን ለመታገል በመሆኑ እርምጃዎችን በፅኑ ያወግዛል።

ሙሉ መግለጫው ተያይዟል…

@fastmereja
4.4K views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 18:10:20 በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

እራሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባል እንደሆነ በማስመሰል እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አራራት ሆቴል አካባቢ ያለው አምስት ሺህ ካሬ ሜትር ባዶ ቦታ በከተማው ካቢኔ በምደባ አስወስንልሀለሁ በማለት የማታለል ወንጀል የፈጸመው አቶ ፍቅረስላሴ ታደሰ እና ግብራአበሮቹ በቁጥጥር ስል ውለዋል::

ግለሰቡ 30,000,000/ሰላሳ ሚሊዮን ብር/ ቅድመ ክፍያ ትከፍላለህ ብሎ በማሳመን የግል ተበዳይ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዳያድርበት ለማድረግ በተለያየ ጊዜ የተፈረሙ ሰነድ በማስመሰል እና ራሱን የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና የመልካም አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ በማድረግ ሀሰተኛ ቲተርና ክብ ማህተሞችን በማዘጋጀት የተለያዩ ደብዳቤዎች ላይ በመፈረም ደብዳቤዎች ለግል ተበዳዩ በማሳየት የማሳመን ስራ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

በጋራ በጥቅም በመመሳጠር 1ኛ ተጠርጣሪ የግል ተበዳይ አቶ ፍቅሬ በየነ የተባሉትን መሬት መግዛት እንደሚፈልግ ካረጋገጠ በኋላ እራሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባል እንደሆነ እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አራራት ሆቴል አካባቢ ያለው አምስት ሺህ ካሬ ሜትር ባዶ ቦታ በከተማው ካቢኔ በምደባ አስወስንልሀለሁ በማለት ለዚህም 30,000,000/ሰላሳ ሚሊዮን ብር/ ቅድመ ክፍያ ትከፍላለህ ብሎ በማሳመን የግል ተበዳይ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዳያድርበት ለማድረግ በተለያየ ጊዜ ካቢኔዎች የፈረሙመበት ሰነድ በማስመሰል እና ራሱን የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና የመልካም አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ በማድረግ ሀሰተኛ ቲተር እና ክብ ማህተቦችን በማዘጋጀት የተለያዩ ደብዳቤዎች ላይ በመፈረም፤ ደብዳቤዎቹን ለግል ተበዳዩ በማሳየት፤
2ኛ ተጠርጣሪ ታምራት እስጢፋኖስ ወደ ሚሰራበት ቢሮ ይዞት በመሄድ ከሁለተኛ ተጠርጣሪ ጋር በማስተዋወቅ ሁለተኛ ተጠርጣሪም በሀሳቡ ሙሉ በሙሉ በመስማማት የግል ተበዳይን ጉዳዩ ቀላል እንደሆነና በቀላሉ ሊያስወስኑለት እንደሚችሉ በማሳመን የግል ተበዳይን የተለያዩ ሰነዶች እንዲያቀርብ ካደረገ በኋላ 1ኛ ተጠርጣሪ ፍቅረስላሴ ታደሰ የበለጠ የግል ተበዳዩ ላይ እምነት እንዲያድርበት በማሰብ ወደ 3ኛ ተጠርጣሪ ዘውዱ ደገፋ የተባለው ግለሰብ ወደ ሚሰራበት የካ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ በማገናፕት
3ኛ ተጠርጣሪም በተመሳሳይ በጉዳዩ በመስማማት ቦታው ድረስ ሂዳ ልኬት እንድትፈጽም 4ኛ ተጠርጣሪ የሆነችውን ቃልኪዳን አክሊሉ የተባለቸዋን መሀንዲስ በመመደብ እና ልኬት እንዲወሰድ በማድረግ ጉዳዩን በቀላሉ ማስወሰን እንደሚችሉ በቀጥታ ለግል ተበዳይ በመናገር ከፍተኛ እምነት እንዲያድርባቸው ያደረጉ ሲሆን 1ኛ ተጠርጣሪ በስምምነታቸው መሰረት በተለያየ ቀን የ8,250,000/ ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ ብር/ ቼክ በመቀበል ተጠርጣሪዎች በጋራ በመሆን ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ምክንያት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

መረጃው የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ነው።

@fastmereja
3.2K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 18:04:23 ወቅታዊ መረጃ ከዩቲዩብ በስፒከር ሰምተሃል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በመተከል ዞን በድባጤ ወረዳ በርበር ቀበሌ በሞባይል መሸጫ ሱቅ ውስጥ የሚሰራ ግለሰብ ወቅታዊ መረጃ ከዩቲዩብ በስፒከር ሰምተሃል የተባለ ግለሰብ መታሰሩ ተሰምቷል ። አ/ቶ ኦላኔ ጉሲ የተባለን ግለሰብ በዛሬው ዕለት ከረፋዱ አራት ሰዓት ገደማ ፖሊስ እና የበርበር ቀበሌ ሊቀ መንበር ከስራ ቦታው ትፈለጋለህ በሚል ወደ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን ድርጊቱን የተመለከቱ የአይን እማኞች ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ። ግለሰቡ በስፒከር ሲከታተል የነበረው መረጃ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር የተያያዘ እንደነበር ተገልጿል ።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ብስራት ራዲዮ የበርበር ቀበሌ ምክትል ሊቀ መንበር የጠየቀ ሲሆን ግለሰቡ እንዲታሰር የተደረገው ሲሰማው በተገኘው መረጃ ነው ብለዋል ። ነገር ግን ጉዳዩን በተመለከተ ከእኛ ጋር መነጋገር ሲገባ ወደ መገናኛ ብዙሃን መውሰድ አግባብ አይደለም ሲሉ አክለዋል።

Via: ዳጉ ጆርናል!

@fastmereja
3.2K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 17:35:34
ኢሳት ቴሌቪዥን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለስልጣን ለኢሳት ቴሌቪዥን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል፡፡ ጣቢያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሚዛናዊነት የጎደላቸው፤ በተጨባጭ መረጃ ያልተደገፉ፤ የህዝቦች መተማመንና አንድነትን ሊሸረሽሩ ሚችሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ ማቅረቡ ማጠንቀቂያው መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ጣቢያው ሚዛናዊነት የጎደላቸውን ሀሰተኛ ዘገባዎችን በማሰራጨት በህዝቦች አብሮበነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ መረጃዎችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠብ ይህ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑን እናሳስባለን ማለቱን ዋልታ ነው የዘገበው።

@fastmereja
3.3K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 14:14:47
የጸሎተ ሐሙስ "ሕጽበተ እግር" በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ ካህናት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።

@fastmereja
3.8K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 09:09:27 በሁለት ታዳጊ ሴት ልጆቹ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል የፈፀመው ወላጅ አባት በ20 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እና የአባትነት መብቱ እንዲታገድ በፍርድ ቤት ውሳኔ መተላለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ኮተቤ ቦኖ ውሃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከልጆቹ ጋር ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ ነው። ግለሰቡ እና የልጆቹ እናት ከሆነችው ባለቤቱ ጋር በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ተለያይተዋል። የ9 እና የ10 አመት ዕድሜ ያላቸው ታዳጊዎቹ የ2015 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት አድርገው ወደ አጎታቸው ቤት በሄዱበት አጋጣሚ ተመልሰው ወደ አባታቸው ቤት መሄድ እንደማይፈልጉ እና ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ በመግለፃቸው ጉዳዩ ወደ የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሴቶች እና ህፃናት ወንጀል ምርመራ ክፍል መምጣቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሷል ።

ተከሳሹ ልጆቹን በፒንሳ እየቆነጠጠና እያስፈራራ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ሲፈፅምባቸው መቆየቱ በምርመራ መረጋገጡን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በአስር አመቷ ታዳጊ ላይ የክብረ ንፅህና መገርሰስ ጉዳት እንደደረሰባት፣ በ9 አመቷ ህፃን ግን ምንም እንኳ የክብረ ንፅህና መገርሰስ ባይደርስባትም ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈፀመባት የህክምና ማስረጃው ያሳያል ብሏል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ከተጣራበት እና በዓቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተበት በኋላ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ወንጀል ችሎት ሰሞኑን በዋለው ችሎት በ20 ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እና ከቤተዘመድ ስልጣን እንዲሁም ከአባትነት መብቱ እንዲታገድ ውሳኔ ያስተላለፈበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከአካላዊ ጉዳት ባሻገር በስነልቦና ላይ ዘላቂ ጉዳትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጭምር በመሆናቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

@FastMereja
1.9K views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ